መጽሐፋችንን እንወቅ
ቁርአን ግልፅ የሆነ ልንስራራበት እና ልናስተነትንበት የሚገባ ሲሆን ለሰው ልጆች በረካ የሆነ መለኮታዊ መጽሐፍ ነው። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ቁርአንን ታዓምር ፣ በረካ ፣ አዳኝ ፣ አስታዋሽ በሚሉ ባህሪያት ጠርቶታል
ቁርአን ግልፅ የሆነ ልንስራራበት እና ልናስተነትንበት የሚገባ ሲሆን ለሰው ልጆች በረካ የሆነ መለኮታዊ መጽሐፍ ነው። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ቁርአንን ታዓምር ፣ በረካ ፣ አዳኝ ፣ አስታዋሽ በሚሉ ባህሪያት ጠርቶታል
የሰው ልጅ ለአለማዊ ትምህርቱ ይደክማል፤ ለዱንያዊ እውቀቱ ይጠበባል፤ ይፅፋል ፣ ያነባል ፣ ይማራል ፣ ይመራመራል። ጀነት ለማያደርሰው ሲራጥንም ለማያሻግረው ከንቱ እውቀት ያለ እንቅልፍ ያድራል። ይህ ሁሉ ሲሆን አይደክምም አይሰለችም። እኔጋ ሲደርስ ግን የሆነ ነገር እጁን ይይዘዋል፤ ፍላጎቱን ያስረዋል። በብዙ ሙስሊሞች ቤት በሳጥናቸው ታሽጌ በግድግዳቸው ተንጠልጥሌ አለሁ።
አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ቁርአንን ታዓምር ፣ በረካ ፣ አዳኝ ፣ አስታዋሽ በሚሉ ባህሪያት ጠርቶታል። በሙስሊም እንደተዘገበው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: “ከአሏህ ቤት የአሏህን መጽሐፍ ለመቅራትና በአንድላይ ሊያጠኑት የሚሰባሰቡ ሰዎች የሉም የመንፈስ እርጋታና ምህረት አካቧቸው ፣ መላኢካዎች