አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ

Author picture

Table of Contents

አንደኛ ትምህርት

ፋቲሐ (የመክፈቻይቱ) ምዕራፍ ጨምሮ ከአል-ዙልዚላህ (የእንቅጥቃጤው) ምእራፍ ጀምሮ እስከ አል-ናስ (የሰዎች) ምዕራፍ ድረስ ካሉት አጫጭር ምእራፎች የተቻለውን ያህል ንባባቸውን በማስተካከልና በቃል በማጥናት እንዲሁም ትርጉሙን ማወቅ።

ሁለተኛ ትምህርት

ከአሏህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር፤ ይኽውም ከአንድ አሏህ በስተቀር ሊያመልኩት የሚገባ ጌታ ስላለመኖሩና ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ከነትርጉሙ እንዲሁም የላ ኢሃ ኢለሏህን ቅድመ ሁኔታዎችን (ሹሩጦችን) ከማብራራት ጋር ማስተማር ነው።

ትርጉም: «ላ ኢላሃ» የሚለው ከአሏህ ሌላ አምላክ እንደሌለ የሚያሳይ አሉታዊ ቃል ሲሆን «ኢለሏህ» የሚለው ደግሞ አምልኮ ለአንድ አሏህ ብቻ መሆኑን የሚያረጋግጥ አወንታዊ ቃል ነው።

«የላ ኢላሀ ኢለሏህ» ቅድመ ሁኔታዎች (ሹሩጦች)

  • ላለማወቅ ተፃራሪ የሆነ እውቀት
  • ምንም ጥርጣሬ የሌለበት እርግጠኝነት
  • ማጋራት ያልተጨመረበት ፍጹምነት
  • ውሸት የሌለበት እውነተኝነት
  • ጥላቻ የሌለበት መታዘዝ
  • ተቃውሞ የሌለበት መቀበል
  • ከአሏህ ውጭ ሌላ ያለን አማልክት በሙሉ መካድ ናቸው።

እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በዚህ መንገድ መግለጽ ይቻላልል። ዕውቀት ፣ እርግጠኝነት ፣ ፍፁምነት ፣ እውነተኝነት ፣ ውዴታና መቀበል ፣ ታዛዥነት እንዲሁም ከሏህ ውጭ የሚመለኩ ነገሮችን መካድ ናቸው።

ሦስተኛ ትምህርት

የእምነት መሰረቶች ስድስት ናቸው። አነሱም፦

በአሏህ ማመን ፣ በመላዕኮቹ ፣ በመጸሐፎቹ ፣ በመልክተኞቹ ፣ በመጨረሻውቀን እና በቀደር ጥሩም ሆነ መጥፎ በአሏህ እውቀት ነው ብሎ ማመን ናቸው።

አራተኛ ትምህርት

የተውሂድ ክፍሎች (አሏህን አንድ የማድረግ ክፍሎች) ሶስት ናቸው። እነሱም፦ የጌትነት አንድነት ፣ የአምላክነት አንድነት ፣ የስሞችና የባህርያት አንድነት ናቸው።

የሽርክ የማጋራት ክፍሎችም ሦስት ናቸው። ትልቁ ማጋራት ፣ ትንሹ ማጋራትና ድብቁ ማጋራት ናቸው። ትልቁ ማጋራት የተግባር ክስረትንና በጀሃነም እሳት ውስጥ መዘውተርን ያስከትላል። አሏህ እንዲህ ብሏል፦

“ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበረ ከነሱ በታበሰ ነበር።”

{አል-ቁርአን}
“ለከሃዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሆነው የአሏህን መስጊዶች ሊሰሩ አይገባቸውም። እነዚያ ስራዎቻቸው ተበላሹ እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።”

{አል-ቁርአን}

በዚህም ላይ የሞተ ሰው በምንም አይነት አይማርም። ጀነትም ለሱ እርም ናት።

“አሏህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። ከዚህም ሌላ ያለውን ለሚሻ ይማራል።”

{አል-ቁርአን}
“እነሆ በአሏህ የሚያጋራ ሰው አሏህ በርሱ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያቸው እሳት ናት። በዳዮች ምንም ረዳት የላቸውም።”

{አል-ቁርአን}

በዚህ ክፍል ከሚጠቃለሉት መካከል ሙታንንና ጣኦታትን መጥራት ፣ በነሱ መመጀን ፣ መሳል ፣ ለነሱ ማድና ሌሎችም ይገኙበታል።

ትንሹ ማጋራት ማለት ደግሞ በቁርአን ወይም በሐዲስ ማጋራት ሽርክ ተብሎ ተገልፆ ግን ከትልቁ የማጋራት ዓይነት ያልሆነ ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ነገር ሲፈጸም ለይዩልኝ መፈጸም ፣ ከአሏህ ሌላ ባለ ነገር መማል ፣ አሏህና እገሌ ካሉ ማለትና የመሳሰሉት ናቸው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ: ለእናንተ ከምፈራላችሁ ሁሉ የምፈራው ትንሹን ማጋራት ነው ብለው ሲናገሩ፤ እሱ ምንድ ነው በማለት ተጠይቀው ሲመልሱ፦ ለይዩልኝ መስራት ነው ብለዋል። ይህ ሐዲስ በጥሩ የዘገባ ሰንሰለት ኢማሙ አህመድ ፣ ጦበራኒና በይሐቂ ሙሐመድ ብኑ ለቢድ የተባሉትን ሰሃባ ጠቅሰው ዘግበውታል። ጠበራኒና በሌላ የዘገባ ሰንሰለት እኚህ ሰሃባ ባከራዕብን ከዲጅ የሰሙትን እንደሚከተለው ዘግበውታል፦

“ከአሏህ ሌላ ባለ ነገር የማለ በእርግጥ አሏህን ካደ ወይም በአሏህ አጋራ።”

{አቡዳውድና ቲርሚዚ}
“አሏህና እገሌ ካሹ አትበሉ እንግዲያውስ አሏህ ካሻ ከዚያም እገሌ ከሻህ በሉ”

{አቡ-ዳውድ}

ሶስተኛው ክፍል ድብቁ ማጋራት ነው። ማስረጃው ተከታዩ የነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው።

“አዋጅ! ከደጃል ይበልጥ የምፈራላችሁ ነገር ምን እንደሆነ ልንገራችሁ ሲሏቸው። እሺ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ ይንገሩን አሏቸው። ድብቁ ማጋራት ነው አሉ። እሱ ሰውየው ይቆምና ይሰግዳል፤ ሶላቱን ያሳምራል ሰውየው ወደሱ መመልከቱን ስላየ።”

{ኢማሙ አህመድ}

አምስተኛ ትምህርት

የእስልምና መሰረት አምስት ናቸው። እነሱም፦

  1. ከአሏህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንና ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ(ሱ.ወ.ተ) መልዕክተኛ ናቸው ብሎ በአንደበቱ መመስከር
  2. ሶላትን መስገድ
  3. ዘካን መስጠት
  4. የረመዷንን ወር መፆም
  5. መስፈርቱን ያሟላ ሰው የሐጅ ፀሎት ማድረግ

ስድስተኛ ትምህርት

የሶላት ቅድመ ዝግጅቶች (ሸርጦች) ዘጠኝ ናቸው። እነሱም፦

  1. ሙስሊም መመሆን
  2. የአእምሮ ጤናማነት
  3. ጠቃሚንና ጐጂን፤ጥሩና መጥፎውን ለይቶ የማወቅ ዕድሜ መድረስ
  4. ትልቁንና ትንሹን ሐደስ ማስወገድ
  5. ነጃሳን ነገር ማስወገድ
  6. ሃፍረተ ገላን መሸፈን
  7. የሚሰገደው የሶላት ጊዜ መግባት
  8. ፊትን ወደ ካእባ(ቂብላ) ማዞርና
  9. ኒያ ናቸው።

ትልቁ ሐደስ ማለት ሙሉ ሰውነት መታጠብ የሚያስፈልግበት ማለት ሲሆን ትንሹ ሐደስ ማለት ደግሞ ውዱእ የሚያስፈልግበት ማለት ነው።

ሰባተኛ ትምህርት

የሶላት ማዕዘናት አሥራ አራት ናቸው። እነሱም፦

  • ችሎታ ያለው ሰው መቆም
  • የመግቢያ ተክቢራ አሏሁ አክበር ማለት
  • ፋቲሐን ማንበብ
  • ማጐንበስ(ሩኩዕ)
  • ከአጐነበሱበት ቀጥ ብሎ መቆም
  • በሰባት የሰውነት አካላት ሱጁድ ማድረግ
  • ከመሬት ላይ ግንባርን ማንሳት ከእሱም መነሳት
  • በሁለት ሱጁዶች መካከል ለተወሰነ ጊዜ መቀመጥ
  • በማንኛውም የሶላት ተግባራትና እንቅስቃሴ ውስጥ መረጋጋት
  • በየማዕዘናቱ መካከል ያሉትን ቅደምተከተል መጠበቅ
  • የመጨረሻውን አተሃያቱ ተሸሁድ ማንበብ ለእሱም መቀመጥ

በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰላት ማውረድና በሁለቱም ጎን አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ ማለት ናቸው።

ስምንተኛ ትምህርት

የሶላት ዋጅቦች ስምንት ናቸው። እነሱም፦ ከመጀመሪያው ተክቢራ በስተቀር በሶላት ውስጥ ያሉ ተክቢራዎች በሙሉ ፣ የሚያሰግድው ሰው ኢማም ወይም ብቻውን ሰጋጅ «ሰሚአሏሁ ሊመንሃሚዳህ» (አሏህ አመስጋኙን ሰሚ ነው ማለት) የሚሰግዱት ሁሉ «ረበና ወለከል ሀምድ» ጌታችን ሆይ! ምስጋና ለአንተ ይሁን ማለት ፣ ሲያጐነብሱ(ሩኩእ ሲያደርጐ) «ሱብሀነ ረቢየል አዚም» ታላቁ ጌታ ጥራትና ልእልና ይገባው ማለት ፣ መሬት ላይ ሲደፉ(ሱጁድ) ሲያደርጉ «ሱብሐነ ረቢየል አዕላ» ሀያሉ ጌታ ጥራትና ልዕልና ይገባው ማለት ፣ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል «ረቢ ግፊርሊ» ጌታየ ማረኝ ብሎ የሚጀምረውን ፀሎት ማድረግ ፣ የመጀመሪያውን ተሸሁድና አተህያቱ ለሱም መቀመጥ ናቸው።

ዘጠንኛ ትምህርት

በሶላት ውስጥ የሚገኙ ሱናዎች

  • የመክፈቻ ፀሎት ማንበብ
  • የቀኝ እጅን መዳፍ በግራ እጅ ላይ በማድረግ ከደረት ላይ ማስቀመጥ
  • የእጆቹ ጣት የተጠጋጉ ሲሆኑ ሁለቱንም እጆች ከትከሻ ወይም እጆሮ ድረስ ማድረስ
  • በማጐንበስ ጊዜም ሆነ በሱጁድ ጊዜ ከአንድ ጊዜ በላይ ተስቢህ አሏህን ማጥራት
  • በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ከአንድ ጊዜ በላይ ምህረትን መለመን
  • ሲያጐነብሱ እራስን በጀርባ ትክክል ማድረግ
  • በመሬት ላይ ሲደፍ(በሱጁድ) ወቅት ጡንቻዎችን ከጐኖቹ ሆድን ከጭኖች ማራቅ
  • ሱጁድ ሲደረግ ክንዶችን ከመሬት ማንሳት ማራቅ
  • በመጀመሪያ ውቁጭታና ተሸሁድ በሁለት ሱጁዶች መካከል ባለው ጊዜ የቀኝ እግሩን ጣት ተክሎ በግራ እግር ላይ መቀመጥ
  • በመጨረሻው ቁጭታ ተሸሁድ ጊዜ የቀኝ እግር ጣትን በመትከል መቀመጫን መሬት ማስነካት
  • በመጀመሪያው ቁጭታ ተሸሁድ ሶላትንና ረድኤትንቱን ለነብዩ ሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው፤ ለነቢዩ ኢብራሃምና ለቤተሰቦቻቸው መለመን
  • በመጨረሻው ቁጭታ ተሸሁድ ፀሎት ማድረግ
  • በሱብሂ ሶላት በሁለቱም ረከዓዎች በመግሪብና በኢሻ በሁለቶች የመጀመሪያ ረክዖዎች ድምጽን ከፍ አድርጐ ቁርአንን ማንበብ
  • በዙሁርና በዓሱር በሁሉም ረክአዎች ፣ በመግሪብ በሶስተኛውና በኢሻ በሁለቶች የመጨረሻ ረክዓዎች ድምፅን ዝቅ አድርጐ ሳያሰሙ ማንበብና
  • ከፋቲሃ ሌላ በተቸማሪ የቁርአን ምእራፍ አንቀፅ ማንበብ ነው። ይህም ሌሎችን በዚህ መጽሐፍ ያልጠቀስናቸውን የሶላት ሱናዎች……

አስረኛ ትምህርት

ሶላትን የሚያበላሹ ነገሮች ስምንት ናቸው። እነሱም ሆን ብሎ ማውጋት ፣ ሳቅ ፣ መብላት ፣ መጠጣት ፣ ሐፍረተ ገላ መግለጥ ፣ ከካዕባ(ቂብላ) አቅጣጫ መዞር ፣ በሶላት ውስጥ በተከታታይ ብዙ እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ የውዱእ መበላሸት (ማፍረስ) ናቸው።

አስራ አንደኛ ትምህርት

የውዱእ ቅድመ ሁኔታዎች (ሸርጦች) አስር ናቸው። እነሱም፦ ሙስሊም መሆን ፣ የአእምሮ ጤናማነት ፣ ጠቃሚና ጎጅውን ፤ ጥሩና መጥፎውን ለይቶ የማወቅ እድሜ ላይ መድረስ ፣ መነየት ፣ ውዱእ እስኪያበቃ ላለማቋረጥ መወሰን ፣ ውዱእን የሚያስገድዱ ነገሮች መቋረጥ ፣ አስቀድሞ እስቲንጃ ማድረግ ፣ ውሃው ንፁህና ሊጠቀሙበት የተፈቀደ መሆን ፣ ውሃ ወደ ሰውነት እናዳይደረስ የሚከለክሉ ነገሮችን ማስወገድ ናቸው።

አስራ ሁለተኛ ትምህርት

የውዱእ ግዴታዎች ስድስት ናቸው። ፊትን መታጠብ ፣ አፍን መጉመጥመጥና ፣ በአፍንጫ ውሃን ማስገባትና ማስወጣት ፣ ሁለቱን እጆች ከክርኖች ጋር ማጠብ ፣ ሁሉን የራስ ፀጉርና ጆሮዎችንም ጭምር ማበስ ፣ ሁለቱን እግሮች እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ማጠብ ይገኙበታል።

ውዱእን የሚያበላሹ ነገሮች ስድስት ናቸው። እነሱም፦ በብልቶች የሚወጣ ቆሻሻ ፣ በእንቅልፍም ሆነ በሌላ ነገር አእምሮን መሳት ፣ ሁለቱን የእፍረት ገላ ያለምንም ከለላ በእጅ መንካት ፣ የግመል ስጋ መብላት ወ.ዘ.ተ ናቸው።

አስራ ሶስተኛ ትምህርት

ማንኛውም ሙስሊም እንዲላበሳቸው የተደነገጉ ባህሪያትና ሥነ-ምግባሮች፦ እውነተኝነት ፣ ታማኝነት ፣ ጥብቅነት ፣ እፍረት (ሐያእ) ፣ ጀግንነት ፣ አሏህ ከከለከላቸው ነገሮች ሁሉ መራቅ ፣ ጉርብትናን ማሳመር ፣ በተቻለ አቅም ችግረኞችን መርዳትና ሌሎችም በቁርአንና በሐዲስ የተደነገጉ ባህሪያቶች ይገኙበታል።

አስራ አራተኛ ትምህርት

ኢስላማዊ ስርአቶች ከነዚህም መካከል፦ ሰላምተኝነት ፣ ፈገግተኝነት ፣ በቀኝ መብላት መጠጣት ፣ ወደ መስጊድ ወይም ወደ ቤት ሲገቡና ሲወጡ ፣ መንገድ ሲሄዱ እንዲተገብሩ የተደነገጉትን ስርአቶች መጠበቅ።

አስራ አምስተኛ ትምህርት

ከሚከተሉት ወንጀሎች እንጠንቀቅ። በአሏህ ከማጋራት ፣ ከድግምት ፣ ሰውን ከመግደል ፣ የየቲሞችን ገንዘብ ከመብላት ፣ ወለድ (አራጣ) ከመብላት ፣ የወላጅ ሃቅን ከመርገጥ ፣ ዝምድናን ከማቃረጥ ፣ የሃሰት ምስክርነት ከመስጠት ፣ በሐሰት ከመማል ፣ ጎረቤቶችን ከማስቸገር ወዘተ እንጠንቀቅ!!!

አስራ ስድስተኛ ትምህርት

ስለ ኢስላማዊ ስርአቶች ከነዚህም መካከል ሰላምተኝነት ፣ ፈገግተኝነት ፣ በቀኝ መጠጣትና መብላት ፣ ወደ መስጊድ ወይም ወደ ቤት ሲገቡና ሲወጡ እንዲሁም መንገድ ሲሄዱ እንዲተገበሩ የተደነገጉትን ስርአቶች መጠበቅ ከወላጆች ጋርና ከዘመዶች ፣ ከጎረቤቶች ፣ ከአዋቂዎች እና ከህፃናቶች ጋር ሊኖር የሚገባውን ስርአት መተግበር!

ህፃን ሲወለድ እንኳን ደስ አሏችሁ በማለት የደስታ መግለጫ መስጠት ፣ ሰው ለሞተበት አሏህ ትዕግስቱን ይስጥህ በማለት ማፅናናትና ሌሎች ኢስላማዊ ስርዓቶችን መጠበቅ።

አስራ ሰባተኛ ትምህርት

ከማጋራትና ከወንጀሎች ሁሉ መጠንቀቅ ነው። ከእነዚህም መካከል ሰባቱ የሰው ልጆችን አጥፊዎች በመባል የሚታወቁት ከባድ ሃጢያቶች ይገኙበታል።

እነሱም በአሏህ ማጋራት ፣ ድግምት ፣ አሏህ ክልክል ያደረግልትን ነፍስ ያለ አግባብ ማጥፋት ፣ የየቲሞችን ገንዘብ መብላት ፣ አራጣ ወይም ወለድ መብላት ፣ በጅሃድ ወቅት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ፣ ንፁህ የሆነች ሴትን በዝሙት መወንጀል።

ከዚህም በተጨማሪ የወላጆችን ሐቅ መርገጥ ፣ ዝምድናን መቁረጥ ፣ በሐሰት መመስከር ፣ የሐሰት መሃላ ፣ ጎረቤትን ማስቸገር ፣ ሰዎችን በደም በገንዘብ በገመና መበደል እና ማስቸገር ሌሎችም አሏህ ወይም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የከለከሏቸው ሁሉ ነገሮች ይገኙበታል።

አስራ ስምንተኛ ትምህርት

እሬሳን መሸኘት በእሱ ላይ መስገድ ዝርዝሩ የሚከተለው ነው።

የሬሳ አዘገጃጀት፦

  1. መሞቱ ሲረጋገጥ አይኖቹ ይገጠማሉ መንጋጭላዎቹ ይገጠማሉ።
  2. እሬሳን መገነዝ

አሏህ ሆይ! በህይወት ያለንም የሞተንም በቅርብ ያለውንም በሩቅ ያለውንም ትልቆችንም ትንሾችንም ወንዶችንም ሴቶችንም ማረን። አሏህ ሆይ! ከመካከላችን በህይወት የምታቆየውን ሰው በኢስላም ላይ አቆየው።

ከመካከላችን የምታሳርፈውን በእምነት ላይ እንደሆነ አሳርፈው። አሏህ ሆይ! ምህረት አድርግለት እዘንለትም ጠብቀው ይቅርም በለው መስተንግዶውን አሳምርለት፤ መግቢያውንም አስፋለት ሃጢያቱንም በውሃና በበረዶ እጠብለት ነጭ ልብስ ከቆሻሻ እንደሚፀዳው አፅዳው። ከቤቱ የተሻለ ቤት ከቤተሰቡ የተሻለ ቤተሰብ ቀይርለት።

ወደ ገነትም አስገባው ፤ ከቀብር ውስጥ ቅጣትና ከእሳትም ቅጣት ጠብቀው። መቃብሩንም አስፋለት፤ አብራለትም። አሏህ ሆይ! ምንዳውን አትንፈገን ከእርሱ ብኋላ እጣችነንን ጥመት አታድርግብን።

ከአራተኛው ተክቢራ በኋላ በቀኝ ጎኑ ብቻ ሰላምታ ይባላል በእያንዳንዱ ተክቢራ እጅን ማንሳቱ ይወደዳል።

ኢማሙ ለማሰገድ ሲቆም ሱናው ሟች ወንድ ከሆነ በራሱ አቅጣጫ ሴት ከሆነች በመሐከል ሰውነቷ አቅጣጫ መቆም ነው። ወንድና ሴት ከሆኑ ወንድ ወደ ኢማሙ በኩል ሴቷ ወደ ቂብላ በኩል ነው የሚደረገው።

ህፃን ካለ መጀመሪያ ህፃኑ ቀጥሎ ሲቲ ቀጥሎም ህፃኗ ሆነው የሚቀመጡት። የህፃኑ ራስ በውንድ ራስ አቅጣጫ ሲሆን የሴት መሐል ሰውነት እንደዚሁ በውንዱ ራስ ትይዩ ይሆናል።

እንደዚሁ የህፃኗ ራስ አቅጣጫ የሚሆነው። በሴት ራስ አቅጣጫ የህፃኗ መኸከል ከወንዱ ራስ አቅጣጫ ነው የሚሆነው የሚሰግዱት ሰዎች በሙሉ ከኢማሙ በኋላ ይሆናሉ። አንድ ሰው ብቻ ቦታ ካለገኘ በኢማሙ በቀኝ ጎን ይቆማሉ።

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top