የካንፓስ ከዋክብት
ድቅድቁን ጨለማ ከላይ ሰመለከት፤ከርቀት አየሁኝ የካንፓስ ከዋክብት፤ ብርሃን ጨረሯ ልብን ይማርካል፤አለው ልዩ ውበት ከርቀት ይስባል፤ ውስጤንም ጠየኩት ማናት ያቺ ኮከብ፤በካምፓስ አድማስ ላይ የለበሰች ጅልባብ፤ ብርሃን ጨረሯ ልብን ይማርካል፤አለው ልዩ መስህብ ከርቀት ይስባል፤ በካንፓስ ጎዳና ስመለከት ሂጃብ ፤በእውነት ድንቅነው አለው ልዩ መስህብ፤ የካንፓስ ከዋክብት ሂጃብና ጅልባብ፤ደምቀው ይታያሉ ላስተዋለው ከልብ፤ የከዋክብት ጥቅም በቁርአን ተብራርቷል፤አላማና ጥቅሙ በደምብ ተቀምጧል፤ […]