ኢማሙል ሙርሰሊን | የመልዕክተኞች መሪ |
ኢምላስ | ከሆድ አካባቢ በመመታት ምክኒያት ማስወረድ |
ኢህቲላፍ | አለመግባባት/የሀሳብ ልዩነት/ጭቅጭቅ |
ሂራ | በመካ አቅራቢያ ያለ የቦታ ስም ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) አሏህን በብቸኝነት ለመገዛት ወደዚህ ቦታ ይሄዱ ነበር። እዚህም ቦታ ነበር ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያውን ወህይ(ራዕይ) የተገለፀላቸው። |
ኢላህ | አምላክ/ጌታ |
ኢምሳክ | የፆም ጊዜ መድረስ(መጀመር) |
ኢንጅል | በነብዩ ሏህ ኢሳ(ዐ.ሰ) ዘመን የተላከ ወህይ(ራዕይ) |
ኢንስ ወል ጂን | የሰው ልጅና ጅኒ |
ኢንሳን | ሰው/የሰው ልጅ |
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጅኡን | አንድ ሙስሊም መጥፎ ነገር ሲያጋጥመው ፣ የሚወዳቸውን ሰዎች ሲያጣ ፣ ኪሳራ ሲደርስበት ፣ መሰናክሎች ሲያጋጥሙት ሶብር በማድረግ ይህን አባባል (አረፍተነገር) ሊል ይገገባል። ትርጉሙም እኛ ለአሏህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን |
ኢንሻ አሏህ | አሏህ ከፈቀደ(ካሻ) |
ኢቃመት አሶላት | ትክክለኛና ሙሉ በሆነ መልኩ ሶላትን መስገድ |
ኢስላም | ሲልም ወይም ሰላም ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ሰላም ፣ ታዛዥነት ወይም ለአሏህ ፈቃድ ራስን ማስገዛት ማለት ነው። |
ኢስነድ | የእያንዳንዱ ሐዲስ የዘገባ ሰንሰለት |
ኢስራ | የምሽት ጉዞ |
ኢስቲግፋር | የአሏህን ምህረት መሻት |
ኢስቲኻራ | ሃያሉ አሏህ ቀናውን መንገድ እንዲመራህና ችግሮችህን እንዲያቃልልህ መለመን |
ኢስቲንጃ | የብልት ክፍሎችን በውሃ ማፅዳት |
ኢስቲስቃ | በድርቅ ወቅት አሏህ(ሱ.ወ) ዝናብ ይሰጠን ዘንድ መለመን |
ኢቲሃድ | ማንነት/ህብረት |
ጀመአ | ግሩፕ |
ጃሂልያ | ድንቁርና/በድንቁርና ፅልመት ውስጥ ያለ |
ጃህል | ድንቁርና/እብሪተኝነት |
ጃህሪ | በሶላት ወቅት ድምፅን ከፍ አድርጎ ቁርአን መቅራት |
ጀለሰ | ተቀመጠ |
ጀናዛ | አስክሬን/የቀብር ስነስርአት |
ጀዛከሏህ ኸይር | አሏህ በመልካም ነገር ይመንዳህ |
ጂን | የተሰወረ |
ጁሁድ | መካድ |
ጃሂድ | ከሃዲ |
ካሚል | ፍፁም የተሟላ/ሙሉ |
ከባኢር | ትልቅ |
ከባኢረዙ ኑብ | ትልቅ ሃጢያት ለምሳሌ:- 1) ሽርክ(ማጋራት) 2) ግድያ 3) ስርቆት 4) ዝሙት ዘ.ተ |
ከላም | ንግግር |