በአንድ ወቅት ሴቶች ብቻ ስለትዳር ህወታቸው የሚወያዩበት እና ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ላይ “ምን ያህሎቻችሁ ባላችሁን ትወዳላችሁ?” ተበለው ተጠየቁ። ታዲያ ሁሉም ሚስቶች ባሎቻቸውን የሚወዱ መሆኑን ለማሳየት እጃቸውን ከፍ አድርገው አወጡ።

ከዛም “ባለችሁን እወድሃለሁ ብላችሁ የነገራችሁት መቼ ነው?” ተብለው ተጠየቁ። አንዳንዳቹ ዛሬ ፣ አንዳንዶቹ ትናንት ፣ አንዳንዶቹ ሊያስታውሱት አልቻሉም ነበር። ከዛም ስልካቸውን አውጥተው ለባሎቻቸው “የእኔ ማር እወድሃለሁ” ብለው መልዕክት እንዲልኩ እና ከጎናቸው ካለው ሰው ጋር ስልክ ተለዋውጠው ምላሹን መልዕክት እንዲያነቡ ታዘዙ። ከእነዚህ መልሶች ውስጥ የተወሰኑት እነዚህ ናቸው።

1. እእ…የልጆቼ እናት አመመሽ እንዴ?

2. አሁን ደግሞ ምንድነው? የትኛውን እቃ ሰበርሽ?

3. ምን ማለት ፈልገሽ እንደሆነ አልገባኝም

4. ደግሞ ምን አደረግሽ? አሁን ግን አልምርሽም።

5. ???

6. እሽክትር አትዙሪ፤ ምን ያህል እንደምትፈልጊ ንገሪኝ ገዝቸ እመጣለሁ

7. በህልሜ ነው?

8. ይህ መልዕክት የማን እንደሆነ ካልነገርሽኝ ዛሬ መሞትሽ ነው

9. ማን ልበል?

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top