መረጃ እና አስፈላጊነቱ

Author picture

Table of Contents

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ ጋር ሲዋሀድ እውቀት ይሆናል፡፡

ከግለሰብ አስተሳሰብ ጋር የተዋሀደ ዕውቀት በመጽሐፍ መልክ ሲዘገብ፣ በፋይል ሲቀነባበር፣ እንዲሁም በመረጃ መረብ ሲለቀቅ እንደገና ለሌሎች እንደ መረጃነት ያገለግላል፡፡

  • መረጃን የዕለታዊ ሕይወቱ አካል ያደረገ ማህበረሰብ በመፍጠር፤ ለአንድ አገር ኢኮኖሚ ዕድገት አጋዥነቱን ለማረጋገጥ ያስችላል፣
  • የሀገር ውስጥና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በመሳብ በተለይ ለሴክተሩ መስህቦቻችንና አገ/ሰጪ ተቋማትን በሰፊው በማስተዋወቅ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ያስችላል፡፡

መረጃዎች ተደራጅተው በአግባቡ ከተቀመጡ

  • ለጥናትና ምርምር፣ለቴክኖሎጅ ሽግግር
  • ለመሰረተ ልማት ዕድገት
  • ለሰው ኃይል ሀብት ልማት
  • ለመጪው ትውልድ ታሪክን ለማስተላለፍ፣
  • ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት ከፍተኛ ሀገራዊ ሚና አለው፡፡

መረጃ አሰባሰብ

መረጃ  ማሰባሰብ በባህርይው ውስብስብ ፣ የሰው ጉልበት፣ ጊዜና በጀት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡

የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች

  • በአካል በቦታው በመገኘት
  • ፎርማቶችን በመቅረፅ ለመረጃ መንጮች 
  • በመላክ
  • በመረጃ መረብ/ኢሜል/
  • መጠይቆችን በመሙላት መረጃ ማሰባሰብ እንችላለን፡፡

መረጃ አደረጃጀት

የማደራጀት ዋና ዓላማው

  • ተጠቃሚው የሚፈልገውን መረጃ በቀላሉ ማግኘት እንዲችልና ጊዜውን በፍለጋ እንዳያባክን ለመርዳት፤
  • የሴክተሩን የመረጃ ክምችት መጠን ለማሳደግ እንዲቻል ነው፡፡

መረጃዎችን  ስናደራጅ፡

  • ግልፅ
  • የሚለካ
  • ጥራት ያለው  ዘመናዊና ችግር ፈች በሆነ መልኩ መሆን አለበት፡፡

የመረጃ ደረጃ

  • መረጃ የብቃት ልክ ማለት ነው፡፡ ጥራት የሚረጋገጥበት መስፈርት ነው፡፡
  • የመረጃ ጥራታችን የሚረጋገጠው መረጃችን ከቀን ቀን እየተከታተልን ወቅታዊ በማድረግ  የተጠቃሚውን ፍላጎት ማርካት ስንችል ነው፡፡

የመረጃ ስርአት

የመረጃ ስርአት  የመረጃ ዘርፎች/ክፍሎች/ በኮምፒውተር ይሁን ያለ ኮምፒውተር እርስ በእርስ ተያይዘው ወጥ የስራ ዓላማን ከግብ ለማድረስ  በቅብብሎሽ የሚሰራ ስራ ነው፡-

የተሟላና ጥራት ያለው የመረጃ ስርአት ካለን

  • ሀብት እንዳይባክን/ተደጋጋሚ ስራ እንዳይሰራ/
    • ጠቀሜታ ያለው ውሳኔ ለመስጠት
    • የልማት እድገት ለማፋጠን
    • የመረጃ  ልውውጥ አውታር ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡

የመረጃ ስርጭት

መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች የማድረስ ዘዴ ሲሆን የመረጃ ስርጭቱ በተለያዩ ዘዴዎች ይከናወናል፣

  • የመረጃ ማዕከላትን ማቋቋምና የመረጃ
    • ስርአቱን ሟሟላት
    • የመረጃ ስርጭት ቴክኖሎጅን መጠቀም
  • የመረጃ መረብ/Internet/
  •  ኢሜል
  •   ዌብሳይት
  •  ሬዲዬና ቴሌቪዥን
  •  የወረዳ ኔት/የፌዴራል፣የክልልና የወረዳ አካላትን የሚያገናኝ የቪዲዬ ኮንፈረንስ የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት መጠቀም
  •  ብሮሸሮችን፣ ሊፍሌቶችን፣ መፅሔቶችን  በሲዲ እና በካሴት መረጃዎችን መቅረፅ እንዲሁም በአካል መረጃዎችን በመስጠት
  • በቤተመፃህፍት በኩል መረጃዎችን በሀርድ  ኮፒና በሶፊት ኮፒ  በማደራጀት የመረጃ ስርጭቱን በማሻሻል ለቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚ አጋዥነቱን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
  1. መስህብ ሀብቶችን
  2. የመገናኛና መጓጓዣ አውታሮችን
  3. የመስተንግዶና የመዝናኛ ተቋማትን  ስናስተሳስራቸው ነው፡፡

ከላይ የጠቀስናቸውን 3/ሶስት/ አበይት ጉዳዬች ከመረጃ ስርአቱ ጋር ስናስተሳስራቸው፤  መስህብ ሀብቶች ያሉበት ደረጃና ታሪካቸውን ማስተዋወቅ ከቻልን

ወደመስህቦቹ ቱሪስት እንዴት መድረስ እንደሚገባው መጠቀም ያለበት የትራንስፖርት አማራጮችን ማሳየት ከቻልን

የማረፈያ ሆቴሎችንና የመዝናኛ ተቋማትን መረጃ ለቱሪስቱ ማድረስ ስንችል ነው የቱሪዝምን ዕድገት ማምጣት የሚቻለው፡፡

የመረጃ ስርአትና ችግሮቹ

የመረጃ ስርአት በርካታ ችግሮች አሉበት ከነዚህም ውስጥ

  • የመደበኛ ቴሌኮሙኔኬሽን መሠረተ ልማት ፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና የግንኙነት  መረብ ዝቅተኛና በበቂ ሀኔታ አለመሟላት
  • የተደራጀ ዳታ እና የመረጃ አቅርቦት ማነስ፤ ያሉትንም የማግኘት ችግር
  • ስለመረጃ ጥቅምና ሚና በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን፣
  • መረጃ መስጠት/ከአገር ውስጥ ገቢ ጋር አያይዞ ማየት/፣
  • በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ/ የግሉ ዘርፍ ያለማደግ፣
  • የበጀትና የማቴሪያል አለመሟላት፣
  • በአገሪቱ በመረጃ በኩል የተቀናጀ አሰራር አለመኖር፣ የመረጃ ክምችትን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ስርአት ዝርጋታ አናሳ መሆን
  • ለመረጃ ስርጭት የሚያገለግሎ እንደ ቤተመፅሐፍት የመሳሰሉ በበቂ ሁኔታ አለመሟላታቸው፡፡ ዋና ዋና ችግሮቹ ናቸው

የመፍትሔ ሐሳቦች

በሀገር ደረጃ መረጃን እንደ ልማት መሣሪያ እንዲሁም መረጃና ቴክኖሎጅን እንደ ዘርፍ በማሳደግና በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን አስተዋጽኦ በማጎልበት ሀገሪቱ የፈጣን ልማትና ዕድገት ተጠቃሚ  እንድትሆን ማድረግ ሲሆን፡-

የመረጃና ቴክኒክ መሠረተ ልማት ግንባታ እንዲስፋፋና ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ፣

በአግባቡ ለማልማትና ለመጠቀም የሚያስፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሀብት ማፍራትና የህብረተሰቡ የመረጃ መሠረታዊ ዕውቀትና አጠቃቀም ማስፋፋት፣

የመረጃና ቴክኒክ አጠቃቀምን  በማሳደግ የሀብት ብክነትን ማቀነስ፣

ፈጣን ዕድገት ለማምጣት የግሉን ዘርፍ ድርሻ በሂደት   ማስፋፋትና ማረጋገጥ፣

ለስራው ትኩረት መስጠትና ስራውን በባለቤትነት የሚመራው ባለሙያ እንዲመደብ ጥረት ማድረግ

በቂ በጀትና  የስራ መሳሪያዎች የሚሟሉበትን መንገድ ማመቻቸት፣

የመረጃ ማዕከላትን ማጠናከር፣

ቤተመፃህፍትን ለመረጃ ስርጭት በአጋዥነት መጠቀም፣

ለዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት፤ ህብረተሰቡ ስለመረጃ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፣

የመፍትሔ ሐሳቦች ናቸው ተብለው ይታሰባሉ፡፡

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top