ጀነት ሃያሉ አሏህ ለደጋግ ባሮቹ ያዘጋጀው ዘላለማዊ የደስታ ቤት ነው፡፡ ይህ ዘላለማዊ ደስታ አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ ነው፡፡ ጀነት የሚገቡ ሰዎች የፈለጉትን ፣ የተመኙትን ማንኛውንም ነገር ያገኛሉ፡፡
ጀነት

ጀነት ሃያሉ አሏህ ለደጋግ ባሮቹ ያዘጋጀው ዘላለማዊ የደስታ ቤት ነው፡፡ ይህ ዘላለማዊ ደስታ አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) ስለ ጀነት ሲናገሩ ‹‹አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት ፣ የሰው ልጅ ልብ አስቦት የማያውቅ ነገር አሏህ ለባሮቼ አዘጋጅቻለሁ አለ›› ብለዋል፡፡

ይህን ሐዲስ ያስተላለፉት አቡ ኹረይራ የሚከተለውን የቁርአን አያ አያይዘው ጠቀሱ

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሰጅዳ 32፡17)

“ይሰሩት ለነበረው ምንዳ የአይን መርጊያ (መደሰቻ) የተደበቀላቸውን ፀጋ ማንኛዋም ነፍስ አታውቅም፡፡”

ጀነት የሚገቡ ሰዎች የፈለጉትን ፣ የተመኙትን ማንኛውንም ነገር ያገኛሉ፡፡ ጀነት ስምንት በሮች አሏት፡፡ አንደኛው ረያን ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህ በር ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት ሲሆን ከእነሱ ውጭ ማንም ሰው በእሱ በኩል አይገባም፡፡ “በእሷ በገቡ ጊዜ ይቆለፋል፡፡ በእሷ በኩል ማንም አይገባም” {ቡኻሪ}

አብዛሃኛው የእሷ ህዝቦች ድሆች ናቸው፡፡ እቃዎቿም ከወርቅና ከብር የተሰሩ ናቸው፡፡ በእሷ የሚገቡ ሰዎች ከሃር የተሰሩና የተጠለፉ አረንጓዴ ልብሶች አላቸው፡፡ ከብር በተሰሩ አምባሮች ያጌጣሉ፡፡ ከተንቆጠቆጠ ማረፊያ ይተኛሉ፤ የሚያቃጥል ፀሐይ ወይም የሚቀዘቅዝ ብርድ አይነካቸውም፡፡

ከጥላዎች ፣ ከምንጮች እና ከፍራፍሬዎች መሃል እንዲሁም ከፈለጉት እና ከተመኙት ቦታ ይሆናሉ፡፡ ከጀነት መስህቦች ውስጥ አንዱ የከውሰር ወንዝ ነው፡፡ ውሃው ከወተት የነጣ ፣ ከማር በላይ የሚጣፍጥ እና ዳርቻው (ተረተሩ) ከሉል የተገነባ ነው፡፡

ጀነት የተለያዩ ደረጃዎች አሏት፡፡ በጣም ከፍተኛው ደረጃ ጀነተል ፊርደውስ ተብሎ ይጠራል፡፡ ነብዩ (ﷺ) በአንድ ወቅት ‹‹አሏህን ስጠይቁ፤ ፊርደውስን ጠይቁ›› ብለዋል፡፡ (መጅመእ አዝዋኢድ)

ስለ ጀነት ሰዎች ሃያሉ አሏህ በቁርአኑ ሲናገር እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ረዕድ 13፡22-24)

“እነዚያ የጌታቸውን ፊት (ውዴታ) ፈልገው የታገሱት ፣ ሶላታቸውን የሰገዱ ፣ ባስገኘናቸው ነገር በድብቅም በግልፅም ምፅዋት የሰጡ ፣ ክፋትን በመልካም የመለሱ እነሱ መልካም ፍፃሜ አላቸው፡፡ የአድን ጀነት (ዘላለማዊ የአትክልት ቦታ) ከወላጆቻቸው ፣ ከሚስቶቻቸው እና ከልጆቻቸው መሃል መልካምን የሰሩ ይገባሉ፡፡ መልአክቶችም ወደ እነሱ በእያንዳንዱ በር ይገባሉ፡፡ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን፤ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ በእርግጥ የመጨረሻዋ ቤት ምንኛ ታምር! ይሏቸዋል፡፡

ጀሐነም ተመልከቱ

Related posts

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

Read More »
መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share