ፍጥረታት በሙሉ ከጥንት ጀምሮ፤
መላዕክቶች ሳይቀሩ ኢብሊስን ጨምሮ፤
የሰው ልጅ ሲፈጠር ከአዳም ጀምሮ፤
እንዲኖር ነበር ትዕዛዙን አክብሮ፤
የአሏህን ሃያልነት ባንድነት መስክሮ፤
ፈገግታው ጨረቃ ጅስሙ የሚያሳሳ፤
ድክ ድክ የሚል እንደጨቅላ እንቦሳ፤
በአማር ቁንጅና በልጃቸው ሀሴት፤
“ኡሙን” ሲያስለቅሳት ልቧን ፍቅር ሞልቶት፤
“አቢው” ይቦርቃል የልጅ ደስታ አስክሮት፤
መማር ከቻልክ ችግሮች እና መሰናክሎች የወደ ፊት ስኬትህ በር ከፋቾች ናቸው፡፡
ድቅድቁን ጨለማ ከላይ ሰመለከት፤
ከርቀት አየሁኝ የካንፓስ ከዋክብት፤
ብርሃን ጨረሯ ልብን ይማርካል፤
አለው ልዩ ውበት ከርቀት ይስባል፤
ውበትሽ ነው ላንቺ ክብር መጠበቂያ፤
ወንድ ላይሳሳት ውበት መደበቂያ፤
ቀልቡ እንዳይሰበር ልቡ እንዳይሸፍት፤
እባክሽ ልበሽው ጥቅም አለው እህት፤