እማየ ውለታሽ ብዙ ነው

Author picture

Table of Contents

እናት አለም ክብሬ እማየ አንደቤቴ፤
የመኖሬ ዋስትና የዘጠኝ ወር ቤቴ፤
በደምሽ ታንፃ መልካሟ ህይወቴ፤

እኔ ስስቅ ስቀሽ ስከፋ ተከፍተሽ፤
ሲርበኝ ተርበሽ
ሲጠማኝ ተጠምተሽ፤

በመልካሙ ምኞት መልካሙን አስበሽ፤
የወደፊት ተስፋየን ህይወቴን አብርተሽ፤

ለፍተሽ ጥረሽ ግረሽ ደክመሽ አስተምረሽ፤
ስሳሳትም መክረሽ ሃሳቤን ቀይረሽ፤

ትክክለኛውን መንገድ መስመሩን አስይዘሽ፤
በርካታ ቢሆንም እማየ ውለታሽ፤
ውለታሽን ከፋይ ልሆን ቃል ስገባልሽ፤
የህይወቴ ብርሃን እማየ እንዳይከፋሽ፤

የትላንቱ ህፃን ዛሬ ሰው ሁኛለሁ፤
ክፉና በጎውን ማስታወስ ችያለሁ፤
እናት አለም ክብሬ ሁሌም እወድሻለሁ!!!

“ጌታችሁም ከእሱ በቀር ያለን ነገር እንዳታመልኩ እና ለቤተሰቦቻችሁ ቅን ትሆኑ ዘንድ ደነገገ። በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው የእርጅና እድሜ በደረሱ ጊዜ ኡፉ አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም። መልካምን ቃል ተናገራቸው። ለእነሱ የሽንፈትና የውርደት ክንፍህን በእዝነት ዝቅ አድርግላቸው። እናም «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ ሁሉ ምህረትህን ስጣቸው» በል።”

{አል-ቁርአን 17:23-34}

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top