ከክፉ የራቀ
ለኸይር የታጠቀ
ለአኺራ የሚተጋ
ለኸቲማው የሚሰጋ
በቀደር ያመነ
በአደጋ የሰከነ
የኔ ብቻ የማይል
ድክመቱን የሚቀበል
ታላቁን አክባሪ
ለታናሹ ራሪ
ፈርዱን ቸል ያላለ
ከሱናውም ያለ
ንግግሩ ተግባር
ህይወቱ ቁምነገር
ለእምነቱ ሰሪ
ለዲኑ ተቆርቋሪ
እውቀትን ፈላጊ
ለበጎ ሁሉ ጓጊ
በኑሮው የረጋ
ባለው የተብቃቃ
ስሜቱን የገታ
ነፍስያውን የረታ
ጏደኞቹ ጥሩ
አሏህን የሚፈሩ
መሞቱን ያወቀ
ቀድሞ የሰነቀ
ውሎው ያማረለት
ኸይር የጨመረበት
ለጊዜው የሚሳሳ
ስንፍናን የረሳ
ንዴቱን የያዘ
ለኢብሊስ ያልታዘዘ