ሂጃብ ወይስ ፋሽን

Author picture
ሂጃብ ወይስ ፋሽን

ሂጃቧን ጠቅልላ
ሙሰስሊም ነሽ ተብላ
በስም ተሸንግላ

ኡፍፍ እንዴት ይሞቃል
ሂጃብ ያስወልቃል
ውስጥን ያስጨንቃል

ኡሽ ምን አለ ቢቀር
ፀሃዩ ሲከር
ፊትን ሲያጠቁር
ወደዚያ ነው መወርወር

የምን መጨናነቅ
ወንዶች መጡ መሰቅቅ
በዝግታ መሣቅ
እራስን መደበቅ

ኧረገኝ ምን አጨናነቀኝ
የፈለገውን ያርገኝ

የፀሃዩ ሙቀት
የሰዎቹ ንቀት
የመንግስት ህግጋት

አረ ስንቱ አረስንቱን ልቻል
ሁሉም ያስወልቃል
ልቤም ይፈልጋል

ታዲያ ምን አለፋሽ
ሂጃብሽን ትተሽ
እንደልብ መምነሽነሽ
አረ ሲያምርብሽ
የት ነበር ውበትሽ
በጨርቅ ውስጥ ደብቀሽ

ወንዶቹን አጓግተሽ
ፐ…አሁን ነው መሽቀርቀር
ምድሪቷ ላይ መዞር
ነጠር ነጠር ፈንጠር
ብዙም ሳንደበር
ሙስሊሙን ማሳፈር

ይላል የሰይጣን መካሪ
ተግባር አስነዋሪ
ምክሩን እሰማና
ሂጃብ አወልቅና
ከጥግ አቆምና

ፊቴን በመስታወት
አይና በትኩረት
እንደዚህ ነው ዉበት

እላለሁ ለራሴ
በገዛ ምላሴ
ድምፄ ተመልሶ
ስሰማው ቀንሶ

ልቤ ድንግጥ ይላል
ስቃይ ይታየኛል
ፍርሀት ይሰማኛል

ኧረ ምን ነክቶኝ ነው
ድንብርብር የምለው
መላቅጤን ማጣው

ወይ ስቃይ ወይ ስቃይ
የሰይጣን አታላይ
ጨፍሮ ላዬ ላይ

ሃሳቤን ቀይሬ
ሂጃቤን ወርውሬ
በፋሽን አስርና

ልወጣ ስል ገና
ደግሞ ምን ታይቶሽ ነው
ትላለች እናቴ
ፀጉሬ ከአናቴ
ቲሸርት ከእንብርቴ

ሱሪው ተወጥሮ
ሚንስከርቱም አጥሮ


ወንድሜ ያይና
ወይ ጉድ ወይ ጉድ ወይ ፈተና
ደሞ ምን ሆንሽና
መምሰልሽ ማዶና

በቃ እንደዚህ መሆን ነው
ነፃነትም ይህ ነው

ተይ እንጂ እህት አለም
ጠፊ ናት እቺ አለም
ብዙም አንኖርም

አቦ አትጨቅጭቀኝ
ሰላሜን አትንሳኝ

አስቢ እንጂ ልጄ
በልተሻል በእጄ
ምን አጣሽ ከደጄ

መች ተራብኩ አልኩና
በሰፊው ጎዳና
ልበል እንጂ ዘና

አቦ በቃ ተወኝ
ብዙም አትነዝንዙኝ
እስኪ ዞር በልልኝ


ሞዴሊስት መስዬ
ስሄድ በጎዳና
በሽቶ ሳናጋው

የጎረምሳውን ልብ
ባካሄዴ ስስብ

ፉጨቱ ሲነፋ
ወይ እኔ ከርፋፋ
አካሄዴ ጠፋ

እሙ ልጋብዝሽ
ፍረጂ በራስሽ
እራስሽን አርክሰሽ
ልቤን አሸፍተሽ

ልቀቀኝ እስኪ አንዴ
እውነትሽ ነው እንዴ
ምን ይሰራል ክንዴ
እቢ ካልክ ጮሀለሁ
ብዬ ስናገረው

እያገላበጠኝ
በቦክስ ነረተኝ
አሁን ጉዴ ፈላ

በዝች ጎዳና
ራሴን ሳትኩና

ገባሁ በእጃቸው
ምንም ሳላውቃቸው

የሰው ጫጫታ
የእናቴ ዋይታ

ካለሁበት ሲያነቃኝ
ሰው ከቦ ሲያየኝ

ዶክተሩ መጣና
ሁሉን አስወጣና
ሰዎቹን ታውቂያለሽ ?
ብሎ ሲጠይቀኝ
አሁን ገና ገባኝ

ለካስ ጉድ ሆኛለሁ
ክብሬን አጥቻለሁ

ምነው ባልተፈጠርኩ
በፅንስነት በሞትኩ

ኢንዲማ አይባልም
የከፋ ቢመስልም
ተስፋም አንቆርጥም

ቀድሞ ነበር መሸሽ
አሁንም ጊዜ አለሽ
ተውበትን ካደረግሽ

ያረቢ ማረኝ
ለሥራዬ ይቅር በለኝ
ከእሳት አድነኝ

መሰልጠን ነው ብዬ
በዱንያ ታልዩ

ዋ! ጥፋቴ
ደም ሲፈስ ካናቴ
ከመላ አካላቴ
ምን ይውጠኝ ነበር
ያኔ ቢሆን ሞቴ

እህቶቼ ንቁ
ይብቃ አትሳቁ
ሞትን አትናቁ

አሰላሙ አለይኩም
ወአለይኩም አሰላም
ልቤ ካለው ሠላም

ካልሆነ በሩቁ
እየተጠነቀቁ
ገና መች ያልቅና
የሴት ልጅ ፈተና

ከቤት ይነሳና
አንቺንማ ሳላይ
አልወርድም ከዚህ ላይ
የማነሽ አታላይ

እያለ ሚላከፍ
ሞልቷል መንገድ ጫፍ
ክፍቱን ያደረ አፍ

ታዲያ ምን ይሻል
መፍትሄውም ሞልቷል
ከሁሉም የሚሻል

አደራ ሂጃባችሁን
የክብር ጋሻችሁን
ወርቃማ ውበታችሁን

ጨርቅን በመጠቅለል
ሂጃብ ለማስመሰል
በሱም አንታለል

እውነተኛ ሂጃብ
ራስን የሚያሳድብ

የነ አኢሻ ተምሳሌት
የመስዋዕትነት ውጤት

የነብዩ አደራ
የሴት ልጅ ባንዲራ

ሚጠብቅ ከትንኮሳ
ሊተውት ሚያሳሳ

ኢማን የሚጨምር
ለአላህ ያለን ፍቅር
ሁሌም የምታምር
የነብዩ ተዓምር
ለጤናችን ወታደር
ከአስከፊው የፀሃይ ጨረር

ለራሳችን ክብር

Related posts

ድፈርና ኢማናችን ይሙላ

ድፈርና ኢማናችን ይሙላ

የናትህን ማህፀን ያኔ ባልጋራህ፤ በኖርክበት ቀዬ ባልኖር ካንተ ጋራ፤ እንደ ዕድል ሆኖ ባይወልደኝ አባትህ፤ ድክ ድክ ብዬ ባላድግ ከቤትህ፤ ምንም ባልፈጠር ከመሃከላችሁ፤ በዘርም በቋንቋ ባልገናኛችሁ፤

Read More »

አማር እና አሞራዎቹ

ፈገግታው ጨረቃ ጅስሙ የሚያሳሳ፤
ድክ ድክ የሚል እንደጨቅላ እንቦሳ፤
በአማር ቁንጅና በልጃቸው ሀሴት፤
ኡሙን ሲያስለቅሳት ልቧን ፍቅር ሞልቶት፤
አቢው ይቦርቃል የልጅ

Read More »
ከሙዕሚን ባህሪ

ከሙዕሚን ባህሪ

ታላቁን አክባሪ
ለታናሹ ራሪ

ፈርዱን ቸል ያላለ
ከሱናውም ያለ

ንግግሩ ተግባር
ህይወቱ ቁምነገር

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share