በዌብሳይታችን የወጣቱ ተልዕኮ ለምንሰራው ስራ ሁሉ እንደ መመሪያ ሆኖ የሚያገለግለን ልዩ የሆነ ራዕይ እና ተልዕኮ አለን፡፡ ይህም ተግባራቶቻችን ከእሴቶቻችን እና ከአላማችን ጋር እንዲተሳሰሩ ያደርግልናል፡፡ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የዌብሳይታችነን ራዕይ ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች እናብራራለን፡፡
ራዕይ
ራዕያችን ወጣቶች ዲናቸውን ወይም ሃይማኖታችውን የሚማሩበት ፣ የሚወያዩበት እና መንፈሳዊ ህይወታቸውን የሚያሳድጉበት መድረክ መፍጠር ነው፡፡
ተልዕኮ
ተልዕኳችን ወጣቶች በምንሰጣቸው አጫጭር ኮርሶች ፣ ስልጠኛዎች እና ፅሑፎች ስለ ሃይማኖታቸው እንዲያውቁ እና በእውቀት እና በመረጃ የታጠቀ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ማስቻል ነው፡፡
ይህን ለማሳካት የተለያዩ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ፣ መጽሐፍት ፣ ኮርሶች ጥያቄና መልስ ወ.ዘ.ተ እናቀርባለን፡፡
እሴቶቻችን
እሴቶቻችን ለምንሰራው ስራ ሁሉ እንደ መመሪያ ያገለግሉናል፡፡ ራዕይ እና ተልዕኮችን ለማሳካት የሚረዱን መሳሪያዎችም ናቸው፡፡ እነዚህ እሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፡፡
- እውቀት እና መረጃን እናስቀድማለን
- ሚዛናዊነት
- አሳታፊነት
- አቃፊነት
- ታማኝነትና እውነተኛነት
- ቆራጥነትና ውዴታ
- አገልጋይነት
- መርሃችን ቁርአን እና ሱና ነው
- በመመካከርና በውይይት እናምናለን
- ቀጣይነት ላለው ለውጥ እንተጋለን
በዌብሳየርታችን የተዳሰሱ አርዕስቶች ምን ምን ናቸው?
ዌብሳታችን መጠነ ሰፊ የሆነ አርዕስቶች የሚዳስስ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ኢባዳ አምልኮተ አሏህ ፣ ከታሪክ ማገህደር ፣ መጽሐፍት ፣ ጥያቄና መልስ ፣ ንፅፅረ ሃይማኖት፣ ቤተሰብ ፣ አጫጭር ስልጠኛዎች ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡
እንዴት መሳተፍ እንችላለን?
ከሌሎች ጋር የምትገናኙበትን እና የምትማማሩበትን እድል ፈጥረናል፡፡ እነሱም የመወያያ ፎረም ፣ የቡድን ውይይቶች እና ሁነቶች ናቸው፡፡ አዳዲስ እና ትኩስ መረጃ ፣ መልዕክቶች እንዲደርሳችሁ በኢሜል አድራሻችሁ ተመዝገቡ፡፡