| አደብ | ኢስላማዊ ባህሪ |
| አቂዳ | እምነት |
| አድል | ፍትህ/መልካም ባህሪ |
| አህካም | ህግ/ትዕዛዝ የኢስላምን ህግ መሠረት በማድረግ 5 ትዕዛዞች አሉ 1) ዋጅብግዴታ 2) ሙስተሃብየተወደደ 3) ሐራምየተከለከለ 4) መክሩህየተጠላ 5) ሀላል__የተፈቀደ/ህጋዊ |
| አሂራ | መጭው አለም |
| ቢድአ | ከቁርአን ፣ ከሐዲስ እና ከሸሪአ መሠረት የሌለው እንዲሁም በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እና በነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ዘመን ያልነበረ ማንኛውም የኢባዳ ተብየ አይነቶችን ከራሳችን ስሜትና ፍልስፍና በመነሳት በዲነል ኢስላም ላይ ያልነበሩ ነገሮችን መጨመር ወይም መቀነስ ነው። |
| ዶኢፍ | ደካማ የአንድ ሐዲስ የተላለፈበትን ሰንሰለት እና በእምነቱና በተግባሩ ሙሉ ስምምነት የሌለው ሐዲስ መገለጫ ነው። |
| ፊትና | ፈተና |
| ፊጥራ | ተፈጥሯዊ/ተፈጥሮ/የተፈጥሮ |
| ሐዲያ | ስጦታ |
| ሀጅ | አንዱ የእስልምና ምሰሶ ነው። |
| ሐሰድ | ምቀኝነት |
| ሐያእ | ይሉኝታ |
| ሂጅራ | ስደት |
| ሂክማ | ጥበብ |
| ሁክም/አህካም | ድንጋጌ/ፍርድ |
| ኢባዳ | አሏህን የመገዛት ተግባር/የአምልኮት ተግባር የኢባዳ (የአምልኮት ተግባር) ሁለት ሁኔታዎች አሉት 1) ለአሏህ ቅን መሆን 2) ለአሏህ መልእክተኛ መታዘዝ(ሱናውን መከተል) ከኢባዳዎች መካከል ሶላት ፣ ዘካት ፣ ፆም ወ.ዘ.ተ የአሏህ ፍራቻ በልብ ውስጥ መኖር እርዳታውንና ምህረቱን መሻት |
| ኢህሳን | የአንድ ኢባዳ (ስራ) ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ አንድን ኢባዳ ስትሰራ ወይም አሏህን ስትገዛ አሏህን እንደምታየው ሁነህ መገዛት ይህን ማድረግ ከቻልክ አሏህ እንደሚያይህ ሆነህ መገዛት ወይም መስራት ማለት ነው። |
| ኢጅቲሃድ | የሙስሊም ሊቃውንቶች መንፈሳዊ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያደርጉት አእምሯዊ ጥረት |
| ኢኽላስ | ጥርት ያለ ቅንነት |
| ኢልም | እውቀት |
| ኢሻራት | የመጨረሻው ቀን ምልክቶች |
| ጃሚእ | ሰፋ ያለና ሁሉን አቀፍ የሐዲስ ማጣቀሻ መፅሐፍ |
| ጂሃድ | በአሏህ (ሱ.ወ) መንገድ ጥረት ወይም ትግል ማድረግ |
| ከራም | ለጋስነት/ቸርነት |
| ኪበር/ኪብር | የተሳሳተ(የውሸት) ኩራት |
| ኪታብ | መፅሐፍ |
| ሁጥባ | ስብከት |
| ኩፍር | የአሏህን አምላክነት መካድ |
| ሙጃሂድ | በአሏህ መንገድ ጥረት ወይም ትግል የሚያደርግ |
| መውዱእ | የተፈበረከ በተለይ ለሐዲስ |
| ሙተፈቁን አለይህ | ስምምነት የተደረሰበት/በቡሐሪይ እና በሙስሊም የተላለፈ ማንኛውም ሐዲስ |
| ሙወጢር | ቀጣይነት ያለው/በተለያየ ጊዜ በብዙ ሰዎች የተዘገበ ሐዲስ |
| ቀደር | መጥፎም ሆነ ጥሩ የሚከሰተው አሏህ የደነገገው ነው ብሎ ማመን |
| ረህማ | ምህረት/እዝነት |
| ሪፋቅ | መልካምነት/ደግነት |
| ሶብር | ራስን መቆጣጠር/ታጋሽነት |
| ሶሂህ | ትክክለኛና ምንም እንከን ወይም ደካማ ላልሆነ ሐዲስ የተሰጠ ስም ነው |
| ሰውም | ፆም |
| ሸሂድ | ራሱን በአሏህ መንገድ የሰዋ |
| ሽርክ | ለአሏህ አጋር ወይም ባላንጣን ማበጀት/ማጋራት ሽርክ(ማጋራት) ሶስት ክፍሎች አሉት 1) አሽርኩል አክበርትልቁ ማጋራት 2) አሽርኩል አስገርትንሹ ማጋራት 3) አሽርኩል ኸፊይ__ድብቁ ማጋራት |
| ሽርኩል አክበር | ከአሏህ ውጭ ባለ ነገር ላይ ማመን(ማምለክ) አሏህ በሽርክ ላይ የሞተን ሰው አይምርም መልካም ስራውንም አይቀበለውም እናም ከኢስላም ውጭ ይሆናል |
| ሽርኩል አስገር | ትንሹ ማጋራት አሏህን ለማስደሰት ተብሎ ሳይሆን ዝናን ክብርን እና ምስጋናን ከሰዎች ዘንድ ለማግኘት ተብሎ የሚሰራ የአምልኮት ተግባር ነው። የዚህ አይነቱ ማጋራት አንድን ሰው ከኢስላም ውጭ አያደርገውም |
| ሽርኩልኸፊይ | ይህ ማጋራት አሏህ በደነገጋቸው ሁኔታዎች ላይ አለመርካት ወይም ቅርመሰኘት ነው። |
የአረብኛ መዝገበ ቃላት 1
Send Us A Message
Related Posts
አረብ (ጌታ) ፡ የአለማት ፈጣሪ ፣ ሲሳይ ሰጭና አስተናባሪ ታላቅነት
አረብ የሚለው ታላቅ የአሏህ ስም ምን ጥልቅ ምስጢር አለው? የአለማት ጌታ የሆነውን ፈጣሪያችንን አጠቃላይና ልዩ
አል-ኸላቅ (ፍፁም ፈጣሪው)፡ የአሏህ አስደናቂ የፍጥረት ጥበብ ሚስጥር
አል-ኸላቅ የተሰኘው የአሏህ ውብ ስም ምን ትርጉም አለው? አስደናቂውን የሰው ልጅና የአጽናፈ ዓለም አፈጣጠር በማንበብ
አል-ኸቢር (ውስጥ አዋቂው) ፡ የተደበቀውን የሚያውቀው ጌታ ባህሪ
አላህ “አል-ኸቢር” መሆኑን ማወቅዎ በልብዎ ያለውን ሚስጥር እንደሚያውቅ ያስገነዝቦታል። ይህን የአላህ ስም ማወቅ ለምን አስፈለገ?
1 thought on “የአረብኛ መዝገበ ቃላት 1”
ዓረብኛ አና ኣማርኛ መዝገበ የቃላት