የወጣቱ ተልዕኮ ምንነት

የወጣቱ ተልዕኮ ምንነትበአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ ይገባው። አሏህ የመራውን ማንም አያጠምም፤ አሏህ ያጠመመውንም ማንም አይመራም። የአሏህ (ሱ.ወ.ተ) ሰላምና እዝነት በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ እለተ ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ! ውድ የወጣቱ ተልዕኮ እንግዶች የአሏህ ሰላም ፣ እዝነና በረከት በእናንተ ላይ ይሁን።

“በጊዜያት እምላለሁ። በእርግጥ ሰው ሁሉ በኪሳራ ውስጥ ነው። እነዚያ ያመኑት ፣ መልካም ስራን የሰሩት ፣ በእውነት እና በትዕግስት አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።”

{አል-ቁርአን 113:1-3}

የወጣቱ ተልእኮ ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ ሲሆን የአድራሻውን ስም እንድሰጥ ምክኒያት የሆነኝ የራሴ የእድሜ ክልል እና ሙስሊም ወጣቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን የነቃ ተሳትፎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።

ሌላው ያነሳሳኝ ነገር አብዛሃኛው የማህበረሰባችን ክፍል ከአሊሞች ጋር ቁጭ ብሎ ከመማር እያፈገፈገ ፣ አሊሞችም በየቦታው ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ፣ ወጣቱ ክፍል ከማወቅ ከመማር እየራቀ ፣ የማንበብ ባህሉ እየደከመ ፣ ከእውቀት ይልቅ ጨዋታ አሉቧልታ ያአሉ ወሬ እጥቅቶት የእውቀት ድሃ ሆኖ ሲንከራተት በማየቴ እና ወጣቱ መጽሐፍ ገዝቶ ከሚያነበው ይልቅ በማህበራዊ ድህረገፆች ኦንላይን ላይ የሚያዘወትር ብዙ በመሆኑ እንዲሁም የማህበራዊ ሚድያ ተደራሽነቱ ከህትመት ስራዎች ሁሉ የበለጠ በመሆኑ ኡማውን በድህረገፅ ፣ በማህበራዊ ሚድያ እና በተለያ የህትመት ውጤቶች ማገልገል እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ነው።

የወጣቱ ተልዕኮ ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ መርሆዎችን የሚከተል እና ከማንኛውም አይነት ሃይማኖታዊ ክፍፍል ወይም ከቡድንተኝነት እና ቲፎዞ ፈላጊነት የፀዳ ነው። ለዚህም ቁንርን እና ሱናን ተንተርሶ አሏህ በሰጠን ሙስሊም በሚለው ቁርአናዊ መጠሪያ ብቻ የተብቃቃ ነው።

ዋና አላማችን “ወደ ጌታህ በጥበብና በመልካም ግሳፄ ጥራ” የሚለውን መለኮታዊ ራዕይ እና “ከእኔ የሰማችሁትን አንዲትም አንቀፅ (አረፍተ ነገር) ብትሆን አስተላልፉ” የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ተመርኩዞ የኢስላምን ትክክለኛ መልእክት ለሁሉም የሰው ልጆች ማድረስ ፣ ኡማውን በድህረገፅ ፣ በማህበራዊ ሚድያ ማገልገል ፣ የአንብብ ትውልድ ለንባብ እና ለእውቀት ትኩረት እንዲሰጥ ማገዝ ነው፡፡

በከፊልም ቢሆን ስለዲኑ የሚያውቅ ወጣት ማፍራት ፣ ኡማውን በቁርአን እና በሱና ገመድ ማስተሳሰር ፣ በኢስላም ለሚነሱ ብዥታዎች ምላሽ መስጠት እና ስለ ኢስላም የምንማርባቸውን መንገዶች ማመቻቸት እንዲሁም ህዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር ነው።

የወጣቱ ተልዕኮ የወጣቱን ንቅናቄና ተሳትፎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወጣቱን ማዕከል ያደረገ ስትራቴጅ በመተግበር በወጣቱ ዘርፍ የእውቀትና የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር መስራት ፣ ተግባራዊ ወጣት መፍጠር ፣ የዳዕዋ ስራ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖር ማድረግ እና የልዩነት ሃሳብን ቢኖርም ልዩነቱን ለእራስ ትቶ በዲነል ኢስላም ጥላ ስር ለአንድቱና ለህብረቱ የሚቆም ወጣት መፍጠር ነው፡፡

በአጠቃላይ ህዝበ ሙስሊሙ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን የነቃ ተሳትፎ ማሳደግ ስለሚያስፈልግ ይህን ስትራቴጅ ነድፎ መንቀሳቀስ አስፈልጓል፡፡

የወጣቱ ተልዕኮ የአሰራር ትልም

በዚህ ድህረገፅ የተከለከሉ ነገሮች

  1. አንድን የማይረባ ነገር ፖስትና ኮሜንት መስጠት
  2. የማንንም ይሁን የማን የሰውን ስም ማጉደፍ ፣ ማርከስ ፣ ማዋረድ ፣ ማሾፍ ፣ መዳራት ወዘተ
  3. አሳሳችና ህገወጥ የሆኑ መረጃዎችን ፖስት ማድረግ
  4. የሌሎችን ሃይማኖት ማንኴሰስ
  5. በዚህ የሞባይል ሳይት የተዘጋጁ ነገሮችን ያለ ሊንክ ኮፒ ፔስት ማድረግ

ማንኛውም አይነት አስተያየት ፣ ትችትና ነቀፌታ ካለዎት በኢሜል አድራሻየ youthmission7@gmail.com ላይ ሊፅፍልኝ ወይም ደግሞ +251920170772 ላይ ሊደወሉልኝ ይችላሉ። ተጨማሪ የወጣቱ ተልዕኮ ኢስላማዊ መጣጥፎችን ለማግኘት http://youthmission1.wordpress.com ይጎብኙ። ጀዛኩሙለህ ኸይረን ከሲረን!

አድራሻ

  • Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ
  • Mugad 04
  • Woldia, Amhara, Ethiopia

ስልክ

  • +251927790323

ኢሜል

FB page:

Founder

  • Ahmed Yesuf (የወጣቱ ተልዕኮ)

13/05/2005

Don’t miss these tips!

We don’t spam! Read our privacy policy for more info.

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top