የአረብኛ መዝገበ ቃላት

ቃላትትርጉም
አደብኢስላማዊ ባህሪ
አቂዳእምነት
አድልፍትህ/መልካም ባህሪ
አህካምህግ/ትዕዛዝ
የኢስላምን ህግ መሠረት በማድረግ 5 ትዕዛዞች አሉ
1) ዋጅብ ግዴታ 2) ሙስተሃብ የተወደደ
3) ሐራም የተከለከለ 4) መክሩህ የተጠላ
5) ሀላል__የተፈቀደ/ህጋዊ
አሂራመጭው አለም
ቢድአከቁርአን ፣ ከሐዲስ እና ከሸሪአ መሠረት የሌለው እንዲሁም በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እና በነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ዘመን ያልነበረ ማንኛውም የኢባዳ ተብየ አይነቶችን ከራሳችን ስሜትና ፍልስፍና በመነሳት በዲነል ኢስላም ላይ ያልነበሩ ነገሮችን መጨመር ወይም መቀነስ ነው።
ዶኢፍደካማ የአንድ ሐዲስ የተላለፈበትን ሰንሰለት እና በእምነቱና በተግባሩ ሙሉ ስምምነት የሌለው ሐዲስ መገለጫ ነው።
ፊትናፈተና
ፊጥራተፈጥሯዊ/ተፈጥሮ/የተፈጥሮ
ሐዲያስጦታ
ሀጅአንዱ የእስልምና ምሰሶ ነው።
ሐሰድምቀኝነት
ሐያእይሉኝታ
ሂጅራስደት
ሂክማጥበብ
ሁክም/አህካምድንጋጌ/ፍርድ
ኢባዳ
አሏህን የመገዛት ተግባር/የአምልኮት ተግባር
የኢባዳ (የአምልኮት ተግባር) ሁለት ሁኔታዎች አሉት
1) ለአሏህ ቅን መሆን
2) ለአሏህ መልእክተኛ መታዘዝ(ሱናውን መከተል)
ከኢባዳዎች መካከል ሶላት ፣ ዘካት ፣ ፆም ወ.ዘ.ተ የአሏህ ፍራቻ በልብ ውስጥ መኖር እርዳታውንና ምህረቱን መሻት
ኢህሳንየአንድ ኢባዳ (ስራ) ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ
አንድን ኢባዳ ስትሰራ ወይም አሏህን ስትገዛ አሏህን እንደምታየው ሁነህ መገዛት ይህን ማድረግ ከቻልክ አሏህ እንደሚያይህ ሆነህ መገዛት ወይም መስራት ማለት ነው።
ኢጅቲሃድየሙስሊም ሊቃውንቶች መንፈሳዊ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያደርጉት አእምሯዊ ጥረት
ኢኽላስጥርት ያለ ቅንነት
ኢልምእውቀት
ኢሻራትየመጨረሻው ቀን ምልክቶች
ጃሚእሰፋ ያለና ሁሉን አቀፍ የሐዲስ ማጣቀሻ መፅሐፍ
ጂሃድበአሏህ (ሱ.ወ) መንገድ ጥረት ወይም ትግል ማድረግ
ከራምለጋስነት/ቸርነት
ኪበር/ኪብርየተሳሳተ(የውሸት) ኩራት
ኪታብመፅሐፍ
ሁጥባስብከት
ኩፍርየአሏህን አምላክነት መካድ
ሙጃሂድበአሏህ መንገድ ጥረት ወይም ትግል የሚያደርግ
መውዱእየተፈበረከ በተለይ ለሐዲስ
ሙተፈቁን አለይህስምምነት የተደረሰበት/በቡሐሪይ እና በሙስሊም የተላለፈ ማንኛውም ሐዲስ
ሙወጢርቀጣይነት ያለው/በተለያየ ጊዜ በብዙ ሰዎች የተዘገበ ሐዲስ
ቀደርመጥፎም ሆነ ጥሩ የሚከሰተው አሏህ የደነገገው ነው ብሎ ማመን
ረህማምህረት/እዝነት
ሪፋቅመልካምነት/ደግነት
ሶብርራስን መቆጣጠር/ታጋሽነት
ሶሂህትክክለኛና ምንም እንከን ወይም ደካማ ላልሆነ ሐዲስ የተሰጠ ስም ነው
ሰውምፆም
ሸሂድራሱን በአሏህ መንገድ የሰዋ
ሽርክለአሏህ አጋር ወይም ባላንጣን ማበጀት/ማጋራት
ሽርክ(ማጋራት) ሶስት ክፍሎች አሉት
1) አሽርኩል አክበር ትልቁ ማጋራት 2) አሽርኩል አስገር ትንሹ ማጋራት
3) አሽርኩል ኸፊይ__ ድብቁ ማጋራት
ሽርኩል አክበርከአሏህ ውጭ ባለ ነገር ላይ ማመን(ማምለክ)
አሏህ በሽርክ ላይ የሞተን ሰው አይምርም መልካም ስራውንም አይቀበለውም እናም ከኢስላም ውጭ ይሆናል
ሽርኩል አስገርትንሹ ማጋራት አሏህን ለማስደሰት ተብሎ ሳይሆን ዝናን ክብርን እና ምስጋናን ከሰዎች ዘንድ ለማግኘት ተብሎ የሚሰራ የአምልኮት ተግባር ነው።
የዚህ አይነቱ ማጋራት አንድን ሰው ከኢስላም ውጭ አያደርገውም
ሽርኩልኸፊይይህ ማጋራት አሏህ በደነገጋቸው ሁኔታዎች ላይ አለመርካት ወይም ቅርመሰኘት ነው።
Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top