ሱፍያኑ ሰውሪ(ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡ “የእውቀት ታላቅነት የሚታወቀው አንድን ሰው አሏህን እንዲፈራ እና እንዲታዘዝ የሚያደርገው ከሆነ ነው፡፡ ካለበለዚያ ልክ እንደማንኛውም ነገር ነው፡፡ {ኢብን ረጀብ አስተላልፈውታል}
ኢብን መስኡድ(ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡ “ትክክለኛ እውቀት የሚለየው ምን ያህል እንደሸመደድክ እና ለሰዎች እንደምትተርክ እና እንደምታስረዳ ሳይሆን እውነተኛ እውቀት የቅድስና(አሏህን የመፍራት እና የመታዘዝ) መገለጫ በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም “ባወከው እና ባጠናሃው ነገር ስራበት” ይሉም ነበር፡፡
አሏህ ሆይ እውቀትን ጨምርልን!
ሒላል ሊሚትድ|ገፅ 18|መጠን 649kb
የዚች መጽሐፍ አላማ መሠረታዊ የተውሂድ ፅንሰሃሳቦችን በጥያቄና መልስ መልክ ማስጨበጥ ሲሆን 50 ያህል ጥያቄዎችንና መልሶቻውቸን አካታለች። የቀረቡት ጥያቄዎች እጅግ መሰረታዊ፤ መልሶቹ ደግሞ አጭር ግን አጥጋቢ እንዲሆኑ የሚቻለውን ሁሉ ተደርጎል። መጽሐፏ በየትኛውም የእድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ጠቀሜታ እንደሚኖራት ይታመናል።
በሼህ አብዱል አዚዝ ብኑ ባዝ|ገፅ 22|መጠን 521kb
ይች መጽሐፍ ሙስሊሞች ጠንቅቀው ሊያውቋቸው የሚገቡ አርዕስተ ጉዳዮችን የሚማሩባት ናት። መጽሐፍ 18 ምዕራፎች አሏት። በዚች መጽሐፍ ስለ ላኢላሃ ኢለሏህ ምንነት እና ቅድመ ሁኔታዎቹ ፣ ስለ አርካኑል ኢማን እና ስለ አርካኑል ኢስላም ፣ ስለ ሶላት ፣ ስለ ውዱ ፣ ስለ ተውሂድና ክፍሎቹ ፣ ሙስሊሞች ሊላበሷቸው ስለሚገቡ ባህርያት ፣ ስለ ሽርክና ክፍሎቹ እንዲሁም ሌሎች አርዕስቶች በየምዕራፉ ተዳሰዋል። ለውቀት ጥማታችሁ መሰረት ሊሆን የሚችል እውቀት ለመቅሰም የንባብ ጅማሯችሁ እዚህ ይሁን።
በአብዱ ናስር አብዱሏሂ |ገፅ 42| መጠን 1MB
የእስልምና ሃይማኖት መሠረቱ አቂዳ ነው። ያለ አቂዳ ኢማን ብሎ ነገር የለም። ሆኖም አቂዳችን በቁርአን እና በሐዲስ ላይ የተመሰረተ ፣ የተስተካከለና ያማረ ካልሆነ የምንሰራው ስራ ሁሉ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። አቂዳችነን የምናስተካክለው ደግሞ በቁርአንና በሐዲስ የታዘዙትን በመስራት በመተግበር ሲሆን የተከለከሉትን በመከልከል ጭምር ነው። በዚህ መጽሐፍ ስለ አቂዳ መሰረቶች በጥያቄና መልስ መልክ ከቁርአን እና ከሱና ማስረጃዎችን በማጣቀስ ተዘጋጅቷል።
በሰኢድ ኢብን አሊ ወህ |ገፅ 233| መጠን 3MB
የሰው ልጅ ቀልቡ ይቆሽሻል ፣ ይዝጋል ፣ አለመረጋጋት ይገጥመዋል ፣ ስክነት ይጎለዋል። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ከእንዲህ አይነቱ በሽታ የምንፈወስበትን ስልት “አሏህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ(13:28)” ሲል አሳውቆናል።
ዚክር__አሏህን ማውሳት እና ማወደስ መረጋጋትን ለመጎናፀፍና ቀልብን ከቆሻሻ ለማፅዳት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ዚክር ለሙስሞች እጅግ በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ነው።
በዶ/ር ሙሐመድ አሊ|ገፅ 98|መጠን 3.8MB
የእስልምና እና ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች አንዱ ስለሌላኛው ሃይማኖት የሚያውቁት በጣም ጥቂቱን ብቻ ነው። ይህ መጽሐፍ በሰባት ርዕሰ ጉዳዮች ማለትም ትክክለኛነት ፣ እግዚአብሄር ፣ እየሱስ(ኢሳ) ፣ የእምነት መሰረቶች ፣ አምልኮ ፣ ስነምግባርና ህግ የሚሉ ጽንሰ ሃሳቦች ላይ ያላቸውን አቋም በተመለከተ በንፅፅራዊ መንገድ ለመመልከት የታለመ ነው። ሁሌም እንደሚባለው እውቀት ሃይል ነው። ማወቅ ካለማወቅ የተሻለ ነው። ይህ ንፅፅራዊ እውቀትም አንባቢው ለእራሱ ተስማሚ ሆኖ ሊያገኘው በሚችል መንገድ ሊጠቅመው ይችላል።
እስላማዊ ዳዕዋና እውቀት ማህብር |ገፅ 24| መጠን 405kb
የላኢላሃ ኢለሏህ የምስክርነት ቃል የጀነት ቁልፍ ነው። ታዲያ ይህ የምስክርነት ቃል መሉ ይሆን ዘንድ ቅድመ ሁኔታዎች አሉት። የቁርአን አንቀፅችን እና የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ብናጠና የሸሃዳ ቅድመ ሁኔታዎች በቁጥር ስምንት ወይም ዘጠኝ እንደሆኑ እንረዳለን። ሆኖም ሁላችነም እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በህይወታችን የራሳችነን የእምነት ምስክርነት ያሟላን መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ይህ መጽሐፍ የተረጎምኩት ከኢማም ሙሐመድ ኢብን አብዱልወሃብ “ማዕነቱ ጣኡት” ከሚለው ፅሁፋቸውና ከዶ/ር ሙሐመድ ቢን አብዱ-ረህማን አልኩመይስ ማብራሪያ ሲሆን በውስጧም አራት ምዕራፎች አሏት።
- የጣኡት ትርጉምና ክፍሎቹ
- በሰው ልጆች ላይ የተደነገገው የመጀመሪያው ግዴታ
- በጣኡት መካድ የእምነት መስተካከል መሰረት ነው የሚሉ ሃሳቦች ተዳሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በየምዕራፍ መጨረሻ ማጠቃለያና እራሳችነን የምንፈትንባቸው መልመጃዎች ተካተዋል።
እስላማዊ ዳዕዋና እውቀት ማህብር |ገፅ 24| መጠን 405kb
የሰው ልጅ በእለት ተዕለት ኑሮው በህሊናው ከሚመላለሱ ጥያቄዎች ወይም ማንኛውም ሰው ቆም ብሎ እራሱን ሊጠይቅ ከሚገባው ጥያቄዎች አንዱ የመፈጠሬ አላማ ወይም ምድር ላይ የመኖሬ ሚስጥር ምን ድነው የሚለው ነው።
ለዚህና ከዚህ ጋር ተያያዥ ለሆኑ በርካታ ጥያቄዎችና የጥርጣሬ ምንጮች ዘላለማዊው ተአምር ቁርአን መልሶቻቸውን አስቀምጦልናል።
ይህ መጽሐፍ ስለ ኢስላም ግንዛቤ ለሌላቸው ሰዎች እጥር ምጥን ባለ መልኩ እውቀት የሚያገኙበት እውቀት ያላቸውም ለመሸምደድ የሚያመች በመሆኑ እውቀታቸውን የበለጠ የሚያዳብሩበት ወይም ለማስተማር የሚረዳ ሆኖ ስላገኘሁት ወደ አማርኛ ተርጉሜዋለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ።
በዚህ መፅሐፍ ከተዳሰሱ አርዕስቶች መካከል የኢስላም ምንነት ፍች ፣ አምስቱ የኢስላም ህጎች ፣ ጦሃራ ፣ የቆሻሻ አይነቶችና የማስወገጃ መንገዶቻቸው ፣ ኢስቲንጃ ፣ ውዱዕ ፣ ጉሱል ፣ ተየሙም ፣ ሶላት ፣ አርካኑ ሶላት ፣ የኢድ ሶላቶች ፣ ዘካና ሃጅ ወ.ዘ.ተ አርዕስቶች ተዳሰውበታል። በየምዕራፉ የተነሳውን አርዕስት ምንያህል እንደተረዳነው እራሳችነን ለመፈተሽ ከእያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ ጥያቄዎች ተካተውበታል። አንብበን የምንጠቀምበትና ሌሎች እህት ወንድሞቻችነን የምንጠቅምበት ያድርግልን።
ወጣቶች ደስታን ለማጣጣም ወይም ከጎደኞቻቸው ጋር ላለመለያየት ወይም ደግሞ ዱንያዊ ኑሯቸውን ለማቃናት ሲሉ ከአሏህ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ያቋርጣሉ። አሉ የተባሉ ሃራም ነገሮችንም ይሰራሉ። የሚፈልጉትን ነገር በሃላል መንገድ ማግኘት ሲችሉ አሏህን በማመፅ ላይ ይፈልጋሉ።
ወቅቱ ወጣቱ ክፍል ለወጣትነት ጊዜው ትኩረት የማይሰጥበት ፣ ለዲኑ ግዴለሽ የሆነበት ፣ ከእውቀት ይልቅ አሉቧልታን ያስቀደመበት ፣ ከመስጊድ የራቀበት ፣ አዋዋሉ የማያምርበት ፣ ለጊዜ ዋጋ የማይሰጥበት የድንቁርና ጊዜ በመሆኑ ይችን ፅሁፍ ልፅፍ ወደድኩ አውርደው ያንብቧት!
የሰው ልጅ ያለ መመሪያ ልጓም እንደሌለው ፈረስ በመሆኑ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ የሰው ልጅ መመሪያ ያስፈልገዋል። ሆኖም ፆመኛ ሰው እንደሌሎቹ የእምነቱ ስርአት ሊከተላቸውና ሊተገብራቸው የሚገቡ መመሪያዎች እንደሚከተለው ተብራርተዋል።
ረመዷን 11 ወር ሙሉ ስሜቱንና ተከትሎ ለኖረ ሰው ሁሉ ልጎም ፣ ለመልካም ሰሪዎች በረካ ሲሆን አዲስ የለውጥ ቤዛ ነው። ታዲያ ፆምን ፆም የሚያደርገው የምግብና የመጠጥ ተአቅቦ ብቻ ሳይሆን አሏህ የከለከላቸውን ነገሮች ሁሉ በመከልከል ያዘዛቸውን ነገሮች በመታዘዝ መልካም ነገሮችን መስራት ነው። ፆም…..በእናንተ ላይ ተደነገገ አሏህን ትፈሩ ዘንድ(2:183)።
የሰው ልጅ በትንሳኤ ቀን በመጀመሪያ የሚጠየቀው ስለ ሶላቱ ነው። እንዲሁም በሙእሚኖችና በኩፋሮች መካከል ያለ መለያ ሶላት ነው። ሶላት አንዱ የኢስላም ምሶሶ ሲሆን ልክ እንደሌሎቹ ኢባዳዎች ሊፈፀም የሚገባው የረሱልን ፈለግ በመከተል ነው። ይህን በተመለከተም ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ስሰግድ እንዳያችሁኝ ስገዱ ብለዋል።
ይህ መጽሐፍ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሶላት ያለውዱ ባዶ ነው ያሉበትን እንዲሁም ስሰግድ እንዳያችሁኝ አድርጋችሁ ስገዱ ይሉበትን ጉዳይ ይተነትናል። በዚች መፅሐፍ የገላ ትጥበትን ፣ የውዱ አደራረግን ፣ የተየሙም አደራረግን እና ጫማ ላይ እንዴት እንደሚታበስ በዝርዝር የሚማሩበት፤ ስለ ሶላትና ትሩፋቱ ፣ ስለ ሶላት አሰጋገድ ፣ ሶላትን ያለመስገድ ብያኔ ፣ ስለ ተውባ እና ስለ አጠቃላይ የቀብር ስነ-ስርአት ለማወቅ እና እውቀትዎን ለማዳበር ልዩ አስተዋፅኦ ይኖራታል።
ዘመኑ የውድድርና የሽቅድድም ዘመን በመሆኑ የሰው ልጅ ሩጫው ለዱንያና ዱንያ ለያዘችው ነገር ሆኗል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ሰዎች ስራ ማጣት ፣ በቂ ገቢ አለማግኘት ፣ እራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት ነገር አለማግኘት ፣ ትዳር መስርተው የሚኖሩበት ወይም ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩበት በቂ ሲሳይ ማጣት ያስጨንቃቸዋል። ሆኖም ይህን ችግር ለማስወገድ በአሏህ መንገድ ላይ ሆነው ከመፈለግ ይልቅ ሃራም የሆኑ የለውጥ ጎዳናዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል።በዚች አነስተኛ መጽሐፍ ውስጥ እንዴት ቀናውን የአሏህ መንገድ ተከትለን ሲሳይ ማግኘት እንደምንችል ከቁርአንና ከሐዲስ ማስረጃዎችን በማጣቀስ የተወሰኑ ጠቋሚ ነጥቦች ተዳሰዋል። መልካም ንባብ!
ሁሉም ሰው ህይወቱ መልካም ፍፃሜ ያገኝለት ዘንድ ይመኛል ያልማል። አብዛሃኛው ወጣቱ ክፍልም ነገን በተስፋ እየጠበቀ ወጣትነቱን ተደስቶበት በማሳለፍ ሃምሳዎቹና ስልሳዎቹ የእድሜ ክልል ላይ ወደ አሏህ እንደሚመለስብ ያስባል። ትልቁ ጥያቄ ግን ነገን ስለመኖርህ ዋስትናህ ምንድነው? ነገ የተቃና ሰው እንደምትሆን ምንድነው ማረጋገጫህ? የሚል ነው።
በዚች አነስተኛ መጽሐፍ የመልካም ፍፃሜ ምንነት ፣ ምልክቶቹ ፣ የመጥፎ ፍፃሜ ምንነትና ምልክቶቹ እንዲሁም ወጣቶች ላይ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችና ቁርአናዊ ግሳፄዎች ተዳሰውበታል ያንብቡት!
ቁርአን የጥበቦች ሁሉ መፍለቂያ ድንቅ እና ታላቅ መለኮታዊ መጽሐፍ ሲሆን ዘላለማዊ ተአምር የሆነ ሙሉ የህይወት መመሪያ ነው። ይህን መለኮታዊ መጽሐፍ እያስተነተን ተረድተነው ለማንበብ ደግሞ ከቁርአን ጋር በሚኖረን ትስስር ልንላበሳቸው የሚገቡ ደንቦችና በስርአት ለማንበብ የሚያስችሉን ህጎች አሉ። ይህም የተጅዊድ ህግ ተብሎ ይጠራል። ለዚህም ነው አሏሁ አዘወጀል “ወረቲሊል ቁርአነ ተርቲላ” ያለን።
እያንዳንዷ እስትንፋሳችን አየር ወደ ውስጥ ማስገባትና ማስወጣትን የያዘ ሲሆን አንዱ ሌላውን ያለ ማቆም ይከተላል። ይህ ሂደት በተፈጥሮ ያለኛ ቁጥጥር ወይም ንቃተ ህሊና ይፈጠራል። እያንዳንዷ እስትንፋሳችነም በህይወት ለመቆየት ምክኒያት ነው። በእያንዳንዷ እስትንፋሳችነም ህይወታችን ይራዘማል። ነገርግን ይህ አንድ ቀን ያቆማል። ያኔ የመጨረሻ እስትንፋሳችን ላይ ቀልባችን በምን ሁኔታ ላይ ይሆን? በዚህ መጽሐፍ ኡስማን ኑሪ ቶፕባሽ ለሞት የመዘጋጀትን አስፈላጊነት ይጠቁመናል።
ኢስላም የእዝነት ሃይምኖት ሲሆን እዝነቱ ለሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ የሰው ልጆች ፣ ከሰው ልጆችም አልፎ ለእንስሳት ጭምር ነው። የኢስላም አብይ ስብዕና የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ዋነኛ መገለጫቸው አሏህ በቁርአኑ እንደገለፀው እዝነት ነው። ዛሬ ግን የሰው ልጅ እርስ በርሱ በመጨካከን እና በመበላላት ከአውሬዎች እንኳ በልጦ በተገኘበት በዚህ ዘመን የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የእዝነት ትምህርትና ምሳሌ ከአየርና ከውሃ የበለጠ እጅጉን ይልስፈልገዋል።
አላዋቂ ሙስሊሞችም ሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ የሴት መብት ጠበቆች ሙስሊም ሴቶች ጭቁኖች ፣ ኋላ ቀር ፣ በኢስላም ቦታ የሌላቸው አድርገው ያስባሉ።
የሴትን ልጅ ህይወት ከጨለማው ዘመን ያላቀቀ ፣ ሴቶች ከወንዶች ጋር ጦርሜዳ እንዲዘምቱ የፈቀደ ፣ እኩል ከወንዶች ጋር ሐዲሶችን እንዲያስተላልፉ ያደረገ ኢስላም እንደሆነ ቢያውቁስ። ህዝባቸውን ፣ ባላቸውን ፣ ልጆቻቸውን በማስተማር ይህን ትውልድ የቀረፁ ሴቶች እንዳሉ ቢረዱስ።
እውቅት የጠፋች የሙስሊሞች ሃብት ናት! የትም ቢሆን ፈልጓት
ነብዩ ሙሐመድ ﷺ