ይህን ያውቁ ኖሯል

Author picture
ኒወርክ ከተማ ውስጥ የነበረው የአለም ንግድ ማዕከል መንትያ ህንፃ ተቆራርጦ አመድ የሆነው በፈረንጆቹ የቀን አቆጣጠር መስከረም 11/2001G.C ነው።
ይህን ያውቁ ኖሯል

ኒወርክ ከተማ ውስጥ የነበረው የአለም ንግድ ማዕከል መንትያ ህንፃ ተቆራርጦ አመድ የሆነው በፈረንጆቹ የቀን አቆጣጠር መስከረም 11/2001G.C ነው። ያኔ አለምን አስደንግጧል።
ቀኑ 11
ወሩ 9
ህንፃው የያዘው የወለል ብዛት 110 ነው።

ይህን ቁጥር አስታውሱ 11_9_110
አሁን ቅዱስ ቁርአንን ክፈቱና
ጁዝዕ 11
ምዕራፍ 9
አንቀፅ 110 ተመልከቱ

የዚህ አንቀፅ የአማርኛ ትርጉም:

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ተውባ 9:110)

“የገነቡት ግንባታ በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅናና የጥርጣሬ ምንጭ ከመሆን ፈፅሞ አይወገድም፤ ልቦቻቸው (በሞት) ካልተቆራረጠ በቀር። አሏህ ሁሉን አዋቂ ጥበበኛ ነው።”

ከዚህ አንቀፅ ቀደም ብሎ ያለው አያ እንዲህ ይላል:

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ተውባ 9:109)

“የግንቡን መሰረት አሏህን በመፍራትና ውዴታውን በመፈለግ ላይ ያደረገ ሰው ይበልጣል ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ የገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሰረተና በእርሱ (ይዞት) በገሃነም እሳት ውስጥ የወደቀ ሰው (ይበልጣል)? አሏህ በደለኛ ህዝቦችን አይመራም።”

እነዚህ አንቀፆች የተገለፁት ከ1439 አመታት በፊት ነው። በእርግጥ ቅዱስ ቁርአን ለምትረዳ ልብ በር ከፋች ነው።

Related posts

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

Read More »
መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »

Share