ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

Author picture
ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።
ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

ብዙ ከሃዲዎች (ካፊሮች) ብቸኛው ፈጣሪ አሏህ እንደሆነ ያምናሉ። ነገርግን አምልኮ ለእሱ ብቻ የሚገባ መሆኑን አያምኑም። የቁረይሽ ሙሽሪኮች ላኢላሃ ኢለሏህ እንዲሉ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጠየቋቸው ጊዜ

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሷድ 38፡5)

አማልክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? በእውነቱ ይህ ድንቅ ነው አሉ።

ላኢላሃ ኢለሏህ

ላኢላሃ ኢለሏህ የሚለው የእምነት ቃልኪዳን የእስልምና ሃይማኖት መሰረት ነው። የኢማን ከፍተኛው ደረጃ ነው። አሏህ ሁሉንም መልእክተኞች የላከው ለዚሁ ምስክርነት ነው። የነብያቶች መደምደሚያ ደግሞ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው።

ይህ ምስክርነት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ ማመንን ይይዛል። ሆኖም ሸሃዳ ሁለት ክፍሎች አሉት።

የእምነት ምስክርነት ቃል
  1. ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ የለም ብሎ ማመን እና
  2. ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ ማመን ነው።

የምስክርነት ቃል ቅድመ ሁኔታዎች

  1. እውቀት፡ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃሉ የያዘውን ትርጉም እና የቃሉ ትርጉም የሚፈልገውን ተግባር ወይም ስራ በትክክል ማዎቅ እና መረዳት ነው። ቁርአን እንዲህ ይላል፡ “እነሆ ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ አለመኖሩን እወቅ።” (አል-ቁርአን 47፡19)
  2. እርግጠኛነት፡ አሏህ ሊመለክ የሚገባው የአለማት ጌታ መሆኑን እና ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን በእርግጠኝነት ያለምንም ጥርጣሬ ማመን ነው። አሏህ እውነተኛ አማኞችን ሲያሞካሽ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሑጅራት 49፡15)

ሙእሚኖች (አማኞች) በአሏህ እና በመልዕክተኛው ያመኑት፤ ከዚያም ያልተጠራጠሩት ፣ በገንዘባቸው እና በነፍሶቻቸው በአሏህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው። እነዚያ እነሱ አማኞች ናቸው።”

መቀበል፡ ማለት ስለሸሃዳ እውቀት ከያዙ ፣ በእሱም እርግጠኛ ከሆኑ ሸሃዳ የያዘችውን እና የምታመለክተውን ነገር መቀበል ነው። የአይሁድ እና የክርስቲያን ቀሳውስት እና መነኮሳት እንዳደረጉት ከፊሉን ተቀብሎ ከፊሉን መተው ሳይሆን ሸሃዳ የያዘችውን ነገር ሙሉ በሙሉ መቀበል ነው። እነሱ በአሏህ ቢያምኑም፤ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በእሱ መላካቸውን ግን ክደዋል።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 2፡109)

የመጽሐፉ ሰዎች ብዙዎቹ እውነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በሆነ ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሃዲዎች አድርገው ሊመልሷችሁ ተመኙ።”

መታዘዝ፡ ለአሏህ ትዕዛዛት በስራዎች መታዘዝ እና ሙሉ በሙሉ ለእሱ እጅ መስጠት ነው። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(አል-ቁርአን 31፡22)

መልካም ሰሪ (ሙህሲን) ሆኖ ፊቱን(እራሱን) ለአሏህ የሰጠ ሰው በእርግጥ ጠንካራ ገመድን ጨበጠ።”

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መውደድ እና መታዘዝ የሚገለፀው ሱናቸውን በመከተል ነው። ቅዱስ ቁርአን እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡65)

በጌታህ ይሁንብኝ! በክርክሮቻቸው ሁሉ መሃል ዳኛ እስኪያደርጉህ ድረስ እና ከዚያም በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከሚያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስኪታዘዙ ድረስ አያምኑም።”

እውነተኛነት፡ ይህን በተመለከተ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “በቅንነት ከቀልቡ ላኢላሃ ኢለሏህ ያለ ሰው ጀነት ይገባል” ብለዋል። (አህመድ) ነገርግን በአፉ እየደለለ በልቡ ትርጉሙን የሚክድ ሰው በእሷ አይጠበቅም። ይህ የሙናፊቆች መገለጫ ነው። ቁርአን እንደሚለው

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 2፡8-10)

ከሰዎችም ሳያምኑ በአሏህና በመጨረሻው ቀን አምነናል የሚሉ (ሙናፊቆች) አሉ። እራሳቸውን ብቻ የሚያታልሉ እና እማያውቁ ሆነው ሳለ አሏህን እና እነዚያ ያመኑትንም ሊያታልሉ ይሻሉ። በልቦቻቸውም ውስጥ (የጥርጣሬና የንፍቅና) በሽታ አለ።

ኢህላስ፡ የሽርክ ተቃራኒ ነው። ቁርአን እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ዙመር 39፡14)

ሃይማኖቴን ለእሱ ያጠራሁ ሆኜ የምገዛው አሏህን ብቻ ነው በል።

ሆኖም ማምለክ ያለብን አሏህን ብቻ እና መከተል ያለብን ደግሞ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ብቻ ነው።

ውዴታ፡ ማለት አሏህን እና መልዕክተኛውን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መውደድ ነው። አሏህ የሚወዳቸውን ንግግሮች እና ስራዎች ሁሉ መውደድ ነው። እንዲሁም ለእሱ ታዛዥ የሆኑ ባሮቹንም መውደድ ነው።

መካድ፡ ከአሏህ ውጭ የሚመለኩ ጣኦቶችን ውድቅ ማድረግ እና መካድ ነው። ሁሉም የአሏህ ነብያቶች እና መልእክተኞች ህዝባቸውን ያስተማሩት ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ አለመኖሩን እንዲመሰክሩና አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ ነው።

ላኢላሃ ኢለሏህ የምትለው ንግግር ብዙ ቱሩፋት አሏት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)

“ከአሏህ ውጭ በሐቅ ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ እና ሶላት እንዲሰግዱ ፣ ዘካ እስኪከፍሉ ድረስ ሰዎችን እንድፋለም ታዘዝኩ። ይህን ካደረጉ ለነፍሶቻቸው እና ለገንዘባቸው ከእኔ ጥበቃ ያገኛሉ። (የሚያስቀጣቸውን ስራ እስካል ሰሩ ድረስ) ሂሳባቸው ከሃያሉ አሏህ ጋር ነው።”

ተውሂድ ፣ ሸሃዳ እና ሱና ተመልከቱ

Related posts

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »
ጀነት

ጀነት

ጀነት ሃያሉ አሏህ ለደጋግ ባሮቹ ያዘጋጀው ዘላለማዊ የደስታ ቤት ነው፡፡ ይህ ዘላለማዊ ደስታ አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ ነው፡፡ ጀነት የሚገቡ ሰዎች የፈለጉትን ፣

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share