ሙስሊም ሰው ከነብዩ ሙሐመድ ዝርዝር ታሪኮች ጋር እራሱን ማስተዋወቅ አለበት። ያ ሲሆን በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሳሌነታቸውን መከተል ይችላል። ምክኒያቱም የህይወት ታሪካቸው ተጨባጭ የእስልምና እና የህግጋቱ ስንቅ ነውና።
ነብዩ ሙሐመድ

ሙስሊም ሰው ከነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ዝርዝር ታሪኮች ጋር እራሱን ማስተዋወቅ አለበት። ያ ሲሆን በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሳሌነታቸውን መከተል ይችላል። ምክኒያቱም የህይወት ታሪካቸው ተጨባጭ የእስልምና እና የህግጋቱ ስንቅ ነውና።

የዘር ሐረጋቸው

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ሐረግ በላጭ እና የተከበረ የዘር ሐረግ ነው። እሳቸው፡ ሙሐመድ ቢን አብዱሏህ ቢን አብዱል ሙጦሊብ ቢን ሐሽም ቢን አብድ መናፍ ቢን ቁሰይ ቢን ኪላብ ቢን ኪላብ ቢን ሙራ ቢን ካአበድ ቢን ሉዋይ ቢን ጋሊብ ቢን ፋህር ቢን ማሊክ ቢን አል-ነድር ቢን ኪናን ቢን ሁዘይማህ ቢን መድረቃ ቢን ኢልያስ ቢን ሙዳር ቢን ኒዛር ቢን ማአድ ቢን አድናን ናቸው። አድናን ደግሞ የተወለደው ከነብዩ ኢስማኤል (ዐ.ሰ) ነው።

ወላጆቻቸው

አባታቸው አብዱሏህ ቢን አብዱል ሙጦሊብ ቢን ሐሽም ሲሆን የሞተው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በእናታቸው ማህፀን ውስጥ ሆነው እያለ ነው። እናታቸው አሚና ቢነት ወሃብ ቢን አብደ መናፍ ቢን ዘህራ ይባላሉ።

አብዱሏህ ከሐሽም ቤተሰቦች ውስጥ ሲሆን ሐሽም ደግሞ የታላቁ ቁረይሽ ጎሳ አንዱ አካል ነው። የተወለዱት በአመል ፊል (በዝሆኑ አመት) 571አ.ዶ መካ ውስጥ ነው።

አባታቸው የሞተው ከመወለዳቸው በፊት ሲሆን እናታቸው የሞተችው ደግሞ የሰድስት አመት ልጅ እያሉ ነበር። ሆኖም ያደጉት የሙት ልጅ ሆነው ነው።

ጡት የጠቡት

ከእናታቸው ሞት በኋላ የተንከባከበቻቸው እና ያጠባቻቸው የመጀመሪያዋ ሴት ሱወይባህ ትባላለች። ከዛም በኋላ የተንከባከበቻቸው እና ያጠባችው ከታዋቂው የበኑ ሰአድ ገሳ የሆነችው ሐሊማ ናት። በኑ ሰአድ ብርቱ በሆነው የበረሃ አየሩ ይታወቃል።

መካ

እድሜ ጠገቡ አያታቸው ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ተንከባክቦ እንደ ልጁ አድርጎ አሳደጋቸው። የሞቱትም ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የስምንት አመት ልጅ እያሉ ነው። ከዛም በኋላ አጎታቸው አቡጧሊብ ተንከባክቦ አሳድጓቸዋል።

አስተዳደጋቸው እና ወጣትነታቸው

1 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከበኑ ሰአድ ቤታቸው መካ ውስጥ ወዳለችው ወደ እናታቸው አሚና በተመለሱ ጊዜ በእናታቸው እቅፍ ውስጥ ሆነው አደጉ።

ከዚያም እናታቸው የሞተችው የስድስት አመት ልጅ እያሉ ከመዲና ወደ መካ በመመለስ ላይ ሳሉ አል-አብዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ያለ አባት እና ያለ እናት ብቻቸውን ቀሩ።

2 አያታቸው አብዱል ሙጦሊብ ወደ መካ መለሳቸው። እዛም ስምንት አመት ከሁለት ወር ከአስር ቀን እስኪሆናቸው ድረስ ተንከባከባቸው። ከዚያም አያታቸው አብዱል ሙጦሊብ መካ ውስጥ አረፉ (ሞቱ)።

3 ከአያታቸው ሞት በኋላ ተንከባክቦ ያሳደጋቸው አጎታቸው አቡጧሊብ ነው። ከልጆቹ ጋር አደባልቆ ፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ወዶ እና ትልቅ አክብሮትን ሰጥቶ አሳደጋቸው። ለእሳቸው የነበረው እንክብካቤ እና ጥበቃ ለ40 አመታት ያህል አልተለያቸውም ነበር።

ነብዩ ሙሐመድ

በዛ ለጋ እድሜያቸው አንስቶ በውብ እና ደግ ምግባራቸው ይታወቃሉ። በህዝቦቻቸውም አሲዲቅ ፣ አል-አሚን (እውነተኛው ፣ ታማኙ) ተብለው ተጠርተዋል።

ነብይ ሆነው ከመላካቸው በፊት የሰሯቸው ስራ

  1. በልጅነታቸው ጥቂት የወርቅ ኪራት ለሚሰጧቸው የመካ ነዋሪዎች በጎችን ይጠብቁ ነበር።
  2. በአስራ ሁለት አመታቸው ከአጎታቸው አቡጧሊብ ጋር ወደ ሻም (ጆርዳን ፣ እስራኢል ፣ ሶርያ ፣ ኦማን) ለንግድ ሄደዋል።

በሃያ አምስት አመታቸው ከቁረይሽ ነጋዴዎች የታወቀችው ከበርቴዋ ነጋዴ ኸድጃ ቢንት ሁወይሊድ ለንግድ ሸቀጧን ይዘው ወደ ሻም እንዲሄዱ ጠየቀቻቸው።

ለሌሎች ከምትከፍለው ሁሉ የበለጠ እንደምትከፍላቸው ቃል ገባች። ምክኒያቱም ታማኝ ሰው መሆናቸው ፣ የነበራቸው ልግስና ፣ የግብይት ስርአታቸውን እና ሌሎች ውብ ስብዕናቸውን ሰምታ ስለነበር ነው።

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ከአገልጋያ መይሰራ ጋር ወደ ሻም አቀኑ። እሷም ወደ መካ በተመለሰች ጊዜ ኸድጃ በታማኝነታቸው እና ከዚያ ጊዜ በፊት አይታ የማታውቀውን ትርፍ እና በረከት አይታ ተደነቀች።

ከመላካቸው በፊት የነበራቸው ህይወት

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ነብይ ሁነው ከመላካቸው በፊት የነበራቸው ህይወት ውስጥ ስህተት ወይም መዘንበል የሌለበት ፣ መልካም እና የተባረከ ህይወት ነበራቸው።

የአሏህ መልዕክተኛ ያደጉት በሃያሉ አሏህ እንክብካቤ ነው። አሏህ ከድንቁርና እድፍ ጠብቋቸዋልም። በህዝባቸው ዘንድ ‹‹ታማኝ እና እውነተኛ›› ተብለው እስኪታወቁ ድረስ ጎረቤታቸውን አክባሪ ፣ ታጋሽ ፣ በንግግራቸው እውነተኛ ፣ አደራን ጠባቂ እና ከመጥፎ ባህሪ ሁሉ የራቁ ነበሩ።

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች

ኸድጃ (ረ.ዐ) ባገቡ ጊዜና ከመይሰራ ጋር ወደ ሻም ለንግድ ሲሄዱ ሃያ አምስት አመታቸው ነበር። መይሰራ ስብዕናቸው ፣ ታማኝነታቸው እና አደራ ጠባቂነታቸው አስደነቀው።

ከጉዟቸው በተመለሱ ጊዜ ያየውን ነገር ሁሉ ነገራት። በዚህም ምክኒያት እንዲያገቧት ፈለገች። ከቁረይሽ ባለባቶች እና ከበርቴዎች ለገብች ስትጠየቅ ኖራ እንቢ ብላየቆየች ቢሆንም በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፍቅር ተነደፈች።

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያገቧት የመጀመሪያዋ ሴት እሷ ናት። እስከሞተችበት ጊዜ ድረስ አላገቡም። ከልጃቸው ኢብራሂም በቀር የልጆቻቸው ሁሉ እናት እሷ ናት። ኸድጃ የሞተችው ወደ መዲና ከመሰደዳቸው ከሶስት አመት በፊት ቀደም ብሎ ነው።

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ስም

  1. ኸድጃ (ረ.ዐ)
  2. ኸድጃ በሞተች ጊዜ ሰውዳ ቢንት ዘአምን አገቡ
  3. ከዚያም የአቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ) ልጅ የሆነችውን አኢሻን አገቡ
  4. ከዛም ሐፍሷ ቢንት ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) አገቡ
  5. ከዚያም የሁዘይማ ቢን አል-ሐሪስ (ረ.ዐ) ልጅ የሆነችውን ዘይነብን አገቡ
  6. ኡሙ ሰላማ ወይም በቅፅል ስሟ (ኩንያ) ሂንድ ተብላ የምትታወቀውን የኡመያን ልጅ አገቡ
  7. ከዚያም ዘይነብ ቢንት ጀዕሽን አገቡ
  8. ከዚያም የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጁወይሪያ ቢንት አል-ሐሪስ (ረ.ዐ) አገቡ
  9. ከዚያም ረምላን ወይም በቅፅል ስሟ (ኩንያ) ኡሙ ሃቢባ ተብላ የምትታወቀውን አገቡ። ሂንድም የአቡ ሱፍያን ልጅም ናት ተብሏል።
  10. ከኸይበር ድል በኋላ ሳፊያ ቢንት ሁየይ ኢብን ኸጧብ (ረ.ዐ) አገቡ
  11. ከዚያም መይሙና ቢንት ሐሪስን አገቡ፤ እሷም የአሏህ መልዕክተኛ ያገቧት የመጨረሻዋ ሴት ናት።

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች ሰባት ናቸው። ሶስት ወንዶች እና አራት ሴት ልጆች ነበራቸው።

እነሱም፡- በቅፅል ስማቸው የሚጠራው እና ጥቂት ጊዜ ብቻ በህይወት የቆየው ቃሲም ፣ አጧሂር ተብሎ የሚጠራው አብዱሏህ ወይም አጦይብ እና ኢብራሂም ናቸው። አራት ሴት ልጆች ነበሯቸው። እነሱም፡- ከሁሉም ትልቋ ዘይነብ ፣ ሩቅያ ፣ ኡሙ ኩልሱም እና ፋጢማ ናቸው።

ከልጃቸው ኢብራሂም በቀር የነብዩ ወንድ እና ሴት ልጆች ሁሉም ከምዕመናን እናት ከሆነችው ከሚስታቸው ኸድጃ (ረ.ዐ) የተወለዱ ናቸው። ልጃቸው ኢብራሂም የተወለደው ከእቁባታቸው ማሪያ አል-ቂብጢያ ነው።

0%
27
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩ ሙሐመድ የህይወት ታሪክ 1

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ 1 ትምህርት ፈተና 7 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችነም በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 7

Bookmark question icon

1 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጡት የጠቡባቸው ሴቶች

2 / 7

Bookmark question icon

2 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያ ሚስታቸው ማን ናት?

3 / 7

Bookmark question icon

3 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ሐረጋቸው ከ______ ይመዘዛል።

4 / 7

Bookmark question icon

4 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ሚስታቸው ማን ናት?

5 / 7

Bookmark question icon

5 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ሐረግን ከፊተኛው ወደ ኋላ ያለውን በቅደም ተከተሉ አስተካክላችሁ አስቀምጥ?
አብዱል ሙጦሊብ
ሐሽም
አብዱሏ
ሙሐመድ

6 / 7

Bookmark question icon

6 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በልጅነታቸው እና በወጣትነታቸው ይሰሩ የነበረው_____

7 / 7

Bookmark question icon

7 ትክክለኛ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች _____ ናቸው።

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 30%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ከእስልምና መልዕክት ጋር መላካቸው

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ነብይነት መጀመሪያ የጀመረው በእውነተኛ ህልም ነው። በእንቅልፋቸው ህልም አያዩም እንደ ንጋት ጮራ (ብርሃን) ሆኖ የመጣ ቢሆን እንጅ።

ይህ ከሆነ በኋላ ስድስት ወራት አለፉ፤ ከዚያም ወህዩ (ራዕ) መገለጥ ጀመረ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እድሚያቸው ወደ አርባ በተቃረበ ጊዜ ከሰው መገለልው (ለብቻቸው) መሆን ይወዱ ነበር። የረዷንን ወር በሂራ ዋሻ ውስጥ ብቻቸውን ሆነው አሏህን እየተገዙ ያሳልፉም ነበር።

ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን ከሰው አግልለው በቆዩበት አመት የመጀመሪያው የራዕይ መገለጥ እስተቀበሉበት ጊዜ ድረስ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ቆዩ።

አርባ አመት በሞላቸው ጊዜ የነብይነት ብርሃን አካበባቸው። ሃያሉ አሏህ ለፍጡራኖቹ በላከው መልዕክት አከበራቸው። ይህ ክብር ለእሳቸው ነጥሎ ሰጣቸው፤ በእሱ እና በባሪያው መካከል ባላደራ አደረጋቸው።

በጅብሪል (ዐ.ሰ) አማካኝነት ትዕዛዙን (መልዕክቱን) ለአለማት እዝነት ፣ ለሰዎች አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርጎ ላካቸው።

በአርባ አመታቸው አሏህ ከሃይማኖቱ ጋር ለሰው ልጅ በሙሉ ላካቸው። እሳቸው የነብያቶች ሁሉ መጨረሻ እና መደምደሚያ ናቸው።

ሚስታቸው አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያውን ራዕይ የተቀበሉት በእውነተኛ ህልማቸው ነበር። “ህልም አይቶ አያውቅም ልክ እንደ ቀኑ ንጋት ዘወትር ያለፈ ቢሆን እንጅ።” (ቡኻሪ)

መልአኩ ጅብሪል (ዐ.ሰ) የአሏህን ወህይ (ራዕይ) ወደሳቸው ይዞ መጣ። የመጀመሪያዎቹን አንቀፆች እንደሚከተለው ገለፀላቸው

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አለቅ 96፡1-5)

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው፤ ጌታህ በጣም ቸር ነውና። ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰው የማያውቀውን ሁሉ ያሳወቀ።

ሂራ ዋሻ

እነዚህ አያዎች የተገለፁላቸው በአንድ ወቅት የሂራ ዋሻ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ነው። በዚህ ዋሻ ውስጥ እራሳቸውን በማግለል ቀንና ሌሊት አሏህን ይገዙ ነበር።

ሚስጥራዊ ዳዕዋ (ጥሪ)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ሰዎች የጥላቻ ተቃውሞ እንዳይገጥማቸው በማሰብ ወደ እስልምና በሚስጥር መጥራት ጀመሩ። እናም ለእሳቸው ቅርብ ለሆኑ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለጓደኞቻቸው ፣ መልካም ነገር ላዩባቸው እና እውነትንና መልካም ነገርን ይወዳሉ ላሏቸው ሰዎች እስልምናን አስተዋውቀዋል።

እስልምናን የተቀበለው የመጀመሪያው

እስልምናን በመጀመሪያ ደረጃ የተቀበሉት ሚስታቸው ኸድጃ ቢንት ኽወይሊድ (ረ.ዐ) ፣ ጓደኛቸው አቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ) እና የአጎታቸው ልጅ አሊ ኢብን አቢ ጧሊብ እና ነፃ ያወጡት ዘይድ ቢን ሐሪስ (ረ.ዐ) ናቸው።

ህዝባዊ (የአደባባይ) ስብከት

በአደባባይ እንዲያስተምሩ ከሃያሉ አሏህ ትዕዛዝ መጣ ‹‹የታዘዝክበትን ነገር በይፋ ግለፅ።›› (ሱረቱል ሂጅር 94) የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ኢስላም ያደረጉት ጥሪ ተገለጠ፤ ሃያሉ አሏህ እንዳዘዛቸውም እውነቱን አወጁ።

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጥሪያቸውን ይፋ ባወጡ ጊዜ የቁረይሽ መሪዎች በጥላቻ ፊታቸውን አዞሩባቸው። ተቃውሟቸውንም በፌዝ ፣ በስላቅ ፣ በንቀት እና በክህደት የሞራላቸውን ጥንካሬ ሊያዳክሙ ሞከሩ ፣ የእስልምና ሃይማኖት አስተምህሮት ሊያንቋሽሹ ፣ ጥርጣሬን ሊያጭሩ ፣ የውሸት ወሬ በመንዛት ጥሪውን አስተባበሉ።

ህዝባዊ (የአደባባይ) ስብከት

እናም ጥሪያቸውን ከተው ጥቅማጥቅሞችን እንደሚሰጧቸው በመንገር ሊደራደሯቸው ፈለጉ።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የእስልምና መልእክት ለማድረስ የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል።

የአቢስንያው ስደት

ሙሽሪኮች እነዚህ የጥላቻ ሴራዎች እንዳልሰሩ ሲያውቁ እና ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) በጥሪያቸው መፅናታቸውን ባዩ ጊዜ እስልምናን ለመዋጋት ወሰኑ፤ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ባልደረቦቻቸውን ማሰቃየት እና ማሳደድ ጀመሩ።

ሙሽሪኮች ያደርሱባቸው የነበርው ግፍ በበረታ ጊዜ ሶሃቦቻቸው ወደ አቢሲንያ (ኢትዮጲያ) እንዲሰደዱ አዘዙ። የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ወንዶች እና ሴቶች ነብዩ ከተላኩ ከአምስት አመት በኋላ ተሰደዱ።

ኢስራዕ እና ሚዕራጅ

በዚህ ጊዜ የነበር የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጥሪያቸው በስኬት እና በስደት መካከል ሆኖ እያለ ነው የኢስራዕ እና ሚዕራጅ ክስተት የተፈፀመው።

ይህ ክስተት ከብዙ አመት ጥሪ ፣ ከሙሽሪኮች ጥቃት ፣ ክህደት እና መገፋት በመታገሳቸው ሊያፀናቸው እና ሊያከብራቸው የመጣ ነው።

ከመካ ውጭ ያደረጉት ዳዕዋ

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ውጭ እስልምናን ለሰዎች ማስተዋወቅ ጀመሩ። እናም ለዚሁ አላማ ወደ ጧኢፍ ሄዱ። ከጧኢፍ ነዋሪዎች ተቃውሞ በገጠማቸው ጊዜ ወደ መካ ተመልሰው ለተለያዩ ጎሳዎች እና ሐጅ ለሄዱ ሰዎች እስልምናን ማስተዋወቅ ቀጠሉ።

የአቀባ የአብሮነት ቃልኪዳን

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በተላኩ በአስራ አንደኛው አመት ላይ መዲና ብለው የሰየሟት የያነዋ ያስሪብ ከተማ ውስጥ ስድስት ሰዎችን አገኙ። እስልምናን አስተዋወቋቸው ፣ እውነቱን ገለፁላቸው ወደ አምልኮተ አሏህ ጠሯቸው።

እናም ቅዱስ ቁርአን ካነበቡላቸው በኋላ እስልምናን ተቀበሉ። እነሱም ወደ መዲና ተመልሰው እስልምና በመካከላቸው እስኪስፋፋ ድረስ ህዝባቸውን ማስተማር ቀጠሉ።

ከዚያ በአስራ ሁለተኛው አመት የአቀባ የአብሮነት ቃልኪዳን ተፈፀመ። ሁለተኛው የአቀባ የአብሮነት ቃልኪዳን በሚስጥር ተፈፀመ።

ነብዩ በመዲነቱል ሙነወራ ውስጥ

አብዘሃኛዎቹ ሙስሊሞች ከመካ ከተሰደዱ በኋላ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና አቡበክር (ረ.ዐ) ወደ መዲና ተሰደዱ። ነገርግን የሄዱት ቁረይሾችን አቅጣጫ ለማሳት በተቃራኒ አቅጣጫ ነበር።

ከዚያም በሰውር ዋሻ ውስጥ ለሶስት ቀን ያህል ከቆዩ በኋላ የቀይባህር ዳርቻን ተረተራማ ቦታ ተከትለው በመሄድ ወደ መዲና አቀኑ።

ከአጋራቸው ጋር በመዲና ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ሙስሊሞች በሚያስደንቅ ሃሴት እና ፈንጠዝያ በተሞላበት ሰልፍ በእልልታ ተቀበሏቸው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና በደረሱ ጊዜ ያደረጉት የመጀመሪያው ነገር የነብዩን መስጅድ መገንባት እና ሙሐጅሮችን (ስደተኞቹን) እና አንሷሮችን (የመዲና ሰለምቴ ደጋፊዎችን) በወዳጅነት ማስተሳሰር ነበር። ይህም ለአዲሱ እስላማዊ ማህበረሰብ ፅኑ መሰረት ጣለ።

ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ የእስልምና ህግጋት ልክ እንደ ዘካ ፣ ፆም ፣ ሐጅ ፣ ጅሃድ ፣ አዛን የሶላት ጥሪ ፣ በመልካም ማዘዝ እና ከክፉ ነገር መከልከል እና ሌሎች እስላማዊ ህግጋቶች መገለጣቸውን ቀጠሉ።

የነብዩ ድል

ሙስሊሞች ሃይማኖተራቸውን እንዲከላከሉ እና ዘላለማዊውን መልዕክት እንዲያስፋፉ ፈቃዱን አወረደላቸው (ገለጠላቸው)። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐጅ 39)

እነዚያ በበደል የሚገደሉ ምዕመናን የተበደሉ በመሆናቸው መዋደቅ (መጋደል) ተፈቀደላቸው።

ለመፋለም (ለመዋደቅ) የተፈቀደበት የመጀመሪያው አንቀፅ ይህ ነው። ከዚያም የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) 27 ወታደራዊ ዘመቻዎችን መርተዋል፤ ሃምሳ ስድስት ሰላዮችን አበጅተዋል።

ከሒጅራ (ከስደቱ) በኋላ የተከሰቱ በጣም ወሳኝ ክስተቶች

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ የተከሰቱ በጣም ወሳኝ ከስተቶች እንደሚከተለው እጥር ምጥን ባለመልኩ ቀርበዋል።

የሂጅራ የመጀመሪያው አመት

  1. ሂጅራ
  2. የነብዩ መስጅድ መገንባት
  3. የመጀመሪያው እስላመዊ መንግስት መስረታ

የሒጅራ ሁለተኛው አመት

የዘካ (ምፅዋት) ፣ ፆም እና አሏህ ለምዕመናን በቁረይሽ ከሃዲያን ላይ ድልን የተጎናፀፉበት ታላቁ የበድር ጦርነት የተደነገገበት ነው።

የሒጅራ ሶስተኛው አመት

የኡሁድ ጦርነት የተካሄደበት ጊዜ ሲሆን ቀስተኞች ምርኮ ለመሰብሰብ ብለው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ በመጣስ ከተራራው ወርደው ሽንፈትን ተከናንበዋል።

የሒጅራ አራተኛ አመት

የበኑ ነዲር አይሁዶች ከሙስሊሞች ጋር የነበራቸውን ስምምነት በመጣሳቸው ምክኒያት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያስወጧቸው መሆኑን ተከትሎ የበኑ ነዲር ጦርነት የተካሄደበት ነው።

የሒጅራ አምስተኛ አመት

የበኒ ሙስጦሊቅ ጦርነት ፣ የአህዛብ ጦርነት እና የበኒ ቁረይዛ ጦርነት የተካሄደበት ጊዜ ነው።

የሒጅራ ስድስተኛ አመት

የሁደይቢያ የሰላም ስምምነት በሙስሊሞች እና በቁረይሾች መካከል የተካሄደበት ነው።

የሒጅራ ሰባተኛው አመት

የኸይበር ጦርነት የተካሄደበት እና የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና ሙስሊሞች መካ ገብተው ኡምራ ቀዳ ያደረጉበት አመት ነው።

የሒጅራ ስምንተኛ አመት

በሙስሊሞች እና በሮሞች መካከል ሙዕጣህ ጦርነት የተካሄደበት ፣ መካን ድል ያደረጉበት እና በሐውዚን እና ሰቂፍ ጎሳዎች ላይ የሁነይን ጦርነት የተካሄደበት አመት ነው።

የሒጅራ ዘጠንኛው አመት

የተቡክ ጦርነት የመጨረሻው ጦርነት የተካሄደበት ነው። ይህዝብ እንደራሴዎች (ተወካዮች) ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጡበት እና ብዙ ሰዎች በገፍ (በብዛት) ወደ አሏህ ሃይማኖት የገቡበት አመት ነው። ይህ አመት የእንደራሴዎች አመት ተብሎ ይጠራል።

የሂጅራ አስረኛው አመት

ሐጀተል ወዳዕ (የስንብት ሐጅ) አንድ መቶ ሽህ የሚበልጡ ሙስሊሞች ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሐጅ ያደረጉበት አመት ነው።

አሟሟታቸው

ጥሪው (ዳዕዋው) ሙሉ በሙሉ በተፈፀመበት ጊዜ ፣ በአረብ ባህረሰላጤ በሙሉ እስልምና ተስፋፋ ፣ ሰዎች ወደ እስልምና በገፍ (በጣም በብዛት) ገቡ፤ በአለም ዙሪያ እንደራሴዎች (መልዕክተኞች) ተላኩ።

እስልምና ከሌሎች ሃይማኖቶች የበለጠ ተቀባይነት አገኘ። ይህኔ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፍፃሚያቸው (ሞታቸው) መቃረቡ ተሰማቸው። ከዚያም ጌታቸውን ለመገናኘት ዝግጅት ጀመሩ።

ንግግራቸው እና ስራቸው ከዚች ጠፊ አለም መለየታቸው የማይቀር መሆኑን ያመላክት ነበር።

በአስራ አንደኛው የስደት አመት በ12ኛው ረቢኡል አወል ወር ሰኞ ቀን የአሏህ መልዕክተኛ ይችን አለም ተለዩ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሞቱት በስልሳ ሶስት አመታቸው ነው። አርባ አመት ነብይ ከመሆናቸው በፊት እና ሃያ ሶስት አመት፤ አስራ ሶስቱን መካ ውስጥ እና አስሩን መዲና ውስጥ ነብይ እና መልዕክተኛ ሆነው ኖረዋል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሞተዋል ነገርግን ሃይማኖቱ ዘላቂ (ዘላለማዊ) ነው። እሳቸው ሞተዋል፤ ይሁን እንጅ መልካም ነገርን አልተውም (አላስቀሩም) ህዝባቸውን ወደ እሱ ያመላከቱ ቢሆን እጅ።

እንዲሁም ክፍን (መጥፎ) ነገር አልተውም ከእሱ ያስጠነቀቁ ቢሆን እንጅ። ወደ መልካም ነገር ያመላከቱት አሃዳዊነትን ፣ አሏህ የሚወደውን እና የሚደሰትበት ነገር ሁሉ ነው።

ከክፉ ነገር ያስጠነቀቁት ደግሞ ሽርክ (በአሏህ ላይ ማጋራት) እና አሏህ የሚጠላው እና የማይቀበለው ነገርን በሙሉ ነው።

በአንድ ምዕተ አመት ውስጥ እስልምና በምዕራቡ አለም ከስፔን እስከ ሩቅ ምስራቅ ቻይና ድረስ ተስፋፍቷል። እስልምና በፍጥነት እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከተስፋፋበት ምክኒያት መካከል እውነታነቱ ፣ የእምነቱ አስተምህሮት እና የተግባራቶቹ ግልፅነት ነው።

እስልምና ወደ አንድ አምላክ እምነት ብቻ የሚጣራ እውነተኛ ሃይማኖት ነው። ሊመለክ የሚገባው አሏህ ብቻ ነው ሲል ያስተምራል።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የፍፁም ታማኝነት ፣ የፍትህ ፣ የእዝነት ፣ የርህራሄ እና የጀግንነት ምርጥ ምሳሌ ናቸው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የፍፁም ታማኝነት ፣ የፍትህ ፣ የእዝነት ፣ የርህራሄ እና የጀግንነት ምርጥ ምሳሌ ናቸው። ምንም እንኳ ሰው ቢሆኑም ከመጥፎ ባህሪያት ሁሉ የራቁ ነበሩ።

ሙሉ በሙሉ ለአሏህ ብቻ ሲሉ ይጥሩ (ይታገሉ) ነበር። ምንዳቸውም በመጭው አለም ህይወት ነው። በሁሉም ስራዎቻቸው እና ንግግራቸው ጥንቁቅ እና አሏህን ፈሪ ናቸው። የአሏህ ሰላት እና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን!

አሏህ የላካቸው ለሰው ልጆች ሁሉ እዝነት  ፣ ለሙዕሚኖች መልካም አብሳሪ እና ለከሃዲዎች አስጠንቃቂ አድርጎ ነው። በፍርዱ ቀን የአደም ልጆች ሁሉ መሪ የሆኑ ፣ ቀብራቸው በመጀመሪያ ደረጃ የሚከፈት ፣ በመጀመሪያ ምልጃ የሚፈቀድላቸው እና የሚያማልዱት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው። የነብያቶች መሪ እና ወደ ጀነት የሚገቡ የመጀመሪያው ሰው ናቸው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት ከጌታቸው ከሆነ እውነት ጋር ነው። ሆኖም ሙዕሚኖች እሳቸውን እንዲወዱ ፣ እንዲከተሉ እና እንዲታዘዙ አሏህ አዟል። አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ፈትህ 48፡29)

ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ ነው።

እንዲህም ብሏል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡59)

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ታዘዙ፤ መልዕክተኛውንም ታዘዙ።

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ አንዳችሁም አላመናችሁም ከልጆቹ ፣ ከወላጆቹ እና ከሁሉም ሰዎች በላይ ከእሱ ዘንድ ተወዳጅ እስክሆን ድረስ።” (ቡኻሪ) እንዲህም አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“እኔን የታዘዘ፤ በእርግጥ! አሏህን ታዘዘ። እኔን ያልታዘዘ አሏህን አልታዘዘም።”

በእርግጥ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለመውደድ እና በእሳቸው ለማመን አንዱ ቅድመ ሁኔታ እሳቸውን መከተል እና መታዘዝ ነው። ቁርአን እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኢምራን 3፡31-32)

በእውነት አሏህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ፤ አሏህ ይወዳችኋል፤ ሃጢያቶቻችሁን ይምርላችኋል።  አሏህ መሃሪ አዛኝ ነውና በል! አሏህን እና መልዕክተኛው ታዘዙ። ብትሸሹ ግን አሏህ ከሃዲዎችን አይወድም በል!

0%
5
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ 2

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ታሪክ 2 ፈተና 7 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 7

Bookmark question icon

1 የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሞቱት በረቢኡል አወል ወር ሰኞ ቀን _____ አመት ነው።

2 / 7

Bookmark question icon

2 በሒጅራ በሶስተኛው አመት ላይ የተካሄደው ጦርነት የትኛው ነው?

3 / 7

Bookmark question icon

3 በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ መሰረት የሚከተሉትን ክስተቶች ከሩቁ ወደ ቅርቡ ሰድረህ አስቀምጥ?
የአቀባ ቃልኪዳን
ይፋዊ ጥሪ
ወደ አቢሲንያ (ኢትዮጲያ) የተደረገው ስደት
ኢስራዕ እና ሚዕራጅ
ሚስጥራዊ ጥሪ (ዳዕዋ)

4 / 7

Bookmark question icon

4 የሚከተሉትን ጦርነቶች በቅደም ተከተላቸው ከሩቁ ወደ ቅርቡ ክስተት ሰድረህ (አስተካክለህ) አስቀምጥ?
የአህዛብ ጦርነት
የበኒ ነዲር ጦርነት
የኡሁድ ጦርነት
የኸይበር ጦርነት
ታላቁ የበድር ጦርነት

5 / 7

Bookmark question icon

5 የኢስራዕ እና ሚዕራጅ ክስተት የተፈፀመው

6 / 7

Bookmark question icon

6 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት በስንት አመታቸው ነው?

7 / 7

Bookmark question icon

7 ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ መዲና የተሰደደው ማን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 15%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

አመል ፊል የዝሆኑ አመት ፣ መካ ፣ አል-መዲና እና ሂጅራ ተመልከቱ

Related posts

የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

አሏህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት እና ስብዕናዎች ከሁሉ የተለዩ አድርጓቸዋል። ይህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት ልቦች በፍቅራቸው እና በውዳሴያቸው እንዲነጉዱ ያደርጋል። በዚህ ጽሁፉ ውስጥ ከእነዚህ ባህሪያት የተወሰኑትን

Read More »

የነብዩ ሙሐመድ መልዕክት

ሃያሉ አሏህ መልዕክተኞችን ከላቀ ጥበብ ጋር የላካቸው ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ ከሁሉም በላይ አልቆ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ (ማብቂያ) አድርጓቸዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እነዚህንም ጥበቦች እና ነብዩ

Read More »
የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ

የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 5

የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 5 ክፍል አምስት የኡመር ኢብን አል-ኽጧብ (ረ.ዐ) ኢስላምን መቀበል ኡመር (ረ.ዐ) ኢስላምን የተቀበለው ሐምዛ (ረ.ዐ) ኢስላምን ከተቀበለ ከሶስት ቀን መሳሪያ ታጥቆ በከረረ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share