ጅብሪል (ዐ.ሰ) የአሏህን ወህይ (ራዕይ) ለመልዕክተኞቹ የሚያደርስ መልአክ ነው። አሏህ የፈጠረው ከብርሃን ነው። የአሏህ መልዕክተኞች መልአክቶችን በተፈጥሯዊ ቅርፃቸው ሊያያቸው ይችላሉ።

ጅብሪል (ዐ.ሰ) የአሏህን ወህይ (ራዕይ) ለመልዕክተኞቹ የሚያደርስ መልአክ ነው። አሏህ የፈጠረው ከብርሃን ነው። የአሏህ መልዕክተኞች መልአክቶችን በተፈጥሯዊ ቅርፃቸው ሊያያቸው ይችላሉ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መልአኩ ጅብሪል በተፈጥሯዊ ቅርፁ ላይ ሆኖ ማየታቸውን አኢሻ (ዐ.ሰ) አስተላልፋለች።

ሂራ ዋሻ

በሂራ ዋሻ ውስጥ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጣው መልአክ ይሄው መልአክ ሲሆን የመጀመሪያዎቹን አምስት የቁርአን አንቀፆች ገልፆላቸዋል። አሏህ እንዲህ አላቸው፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ አለቅ 96፡1-5)

“አንብብ ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው። አንብብ! ጌታህ በጣም ቸር ነው። ያ በብዕር ያሰተማረ፤ የሰው ልጅ የማያውቀውን ያሳወቀ ነው። በእርግጥ ሰው ወሰንን ያልፋል።”

እንዲሁም ወደ ሰባቱ ሰማያት እጅቧቸው የሄደው መልአኩ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነው። (ኢስራዕ እና ሚዕራጅ ተመልከቱ)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ብዙ ጊዜ ዲህያ አል-ኸልቢ ተብሎ በሚጠራ በሰው ቅርፅ ተመስሎ ያዩት ነበር። የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦች በጥቂት አጋጣሚዎች እና ክስተቶች በሰው ቅርፅ ተመስሎ አይተውታል።

ለምሳሌ ከእነዚህ አጋጣሚዎች መካከል በአንድ ወቅት እነ ኡመር (ረ.ዐ) ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ቁጭ ብለው እያለ ልብሱ እጅግ በጣም የነጣ ፣ ፀጉሩ በጣም የጠቆረ ፣ የመንገደኛነት ምልክት የማይታይበት ፣ አንዳቸውም የማያውቁት የሆነ በሰው ተመስሎ ያዩበት ጊዜ ነው።

ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሄደና ጉልበቱን ከጉልበታቸው ገጥሞ ተቀመጠ። የእጆቹን መዳፍ ታፋቸው ላይ አስቀመጠ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ እስልምና ፣ ስለ ኢማን ፣ ስለ ኢህሳን እና ስለ ፍርዱ ቀን እና ምልክቶቹ ጠየቃቸው።

ሁሉንም ጥያቄዎች መለሱለት። በሄደ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ይህ ሰው ጅብሪል ነው፤ የመጣው ሃይማኖታችሁን ሊያስተምራችሁ ነው አሏቸው።

0%
8
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ስለ መላእክት ምን ያህል ያውቃሉ?

መላእክት አንድ ሙስሊም መኖራቸውን ሊያምንባቸው ከሚገቡት ስድስቱ የኢማን መሰረቶች መካከል ናቸው። በቁርአን እና በበርካታ ሐዲሶች ውስጥ ተጠቅሰዋል፤ ይህም አንዳንዶቹ መላእክት ከሌሎቹ የበለጠ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያጎላል።

ስለ መላእክት ምን ያህል ያውቃሉ? ከታች ባለው ጥያቄና መልስ እውቀትዎን ይፈትሹ!

1 / 14

Bookmark question icon

1 ለእያንዳንዱ ሰው የተመደቡ ስንት መላእክት አሉ?

2 / 14

Bookmark question icon

2. የትንሣኤ ቀን መቃረቡን የሚያመለክተውን ጥርንቧ (ጡሩምባን) የሚነፋው መልአክ ስም ማን ይባላል?

3 / 14

Bookmark question icon

3. መላእክት ክንፍ አላቸው?

4 / 14

Bookmark question icon

4. ጅብሪል (ዐ.ሰ) ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሰጣቸው የመጀመሪያ መመሪያ ምን ነበር?

5 / 14

Bookmark question icon

5. መላእክት የሰውን መልክ (ቀርፅ) መያዝ ይችላሉ?

6 / 14

Bookmark question icon

ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ ዘግበዋል፡ “አንድ ቀን ከአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ተቀምጠን ሳለ፣ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ እና በጣም ጥቁር ፀጉር ያለው አንድ ሰው ብቅ አለ። የጉዞ ምልክት አይታይበትም ነበር እኛም አናውቀውም ነበር። በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፊት ተቀምጦ ጉልበቶቹን በጉልበታቸው አስደግፎ እጆቹንም በጭናቸው ላይ አሳረፈ…”

6. ኡመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) የገለጹት ማነን ነበር?

7 / 14

Bookmark question icon

7. መላእክት አላህን መበደል (ማመፅ) ይችላሉ?

8 / 14

Bookmark question icon

8. መላእክት ከምን ተፈጠሩ?

9 / 14

Bookmark question icon

9. ጀነት እና ጀሐነምን የሚጠብቁት መላእክት ስም ማን ይባላል? (በቅደም ተከተል)

10 / 14

Bookmark question icon

10. የሙስሊም ሰራዊት እንዲያሸንፍ ለመርዳት በሺዎች የሚቆጠሩ መላእክት የተላኩት በየትኛው ጦርነት ላይ ነበር?

11 / 14

Bookmark question icon

11. መቃብር ውስጥ ስንት መላእክት ይጠይቁናል?

12 / 14

Bookmark question icon

12. በግራ በኩል ሆኖ መጥፎ ስራዎቻችንን የሚመዘግበው መልአክ ወዲያውኑ በመዝገባችን ላይ ይጽፈዋል?

13 / 14

Bookmark question icon

13. መላእክት ይበላሉ ይጠጣሉም?

14 / 14

Bookmark question icon

14. አላህ ሰውን ወደ ምድር ሊልክ መሆኑን ሲያውቁ መላእክት ምን አሉ?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 15%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

መላኢካ ፣ ኢስራዕ እና ሚዕራጅ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Share