ጀሐነም ለከሃዲዎች እና ለሃጢያተኞች አሏህ ያዘጋጀው የመቀጫ ቦታ ነው። ጀሐነም ቁርአን በሌላ መጠሪያ ስሞች ማለትም አል-ሁታማህ (የሚያጠፋው) ፣ አሰኢር (ነበልባላው እሳት) ፣ አልጀሂም እና አል-ሐዊያ በሚል ይገልፀዋል።

ጀሐነም ለከሃዲዎች እና ለሃጢያተኞች አሏህ ያዘጋጀው የመቀጫ ቦታ ነው። ይህን ቦታ ቅዱስ ቁርአን በሌላ መጠሪያ ስሞች ማለትም አል-ሁታማህ (የሚያጠፋው) ፣ አሰኢር (ነበልባላው እሳት) ፣ አልጀሂም (የሚቀጣጠለው እሳት) እና አል-ሐዊያ (የእንጦረጦስ ጉድጓድ) በሚል ይገልፀዋል። አሏህ (ሱ.ወ.ተ) እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሙልክ 67፡6)

ለእነዚያ በጌታቸው ለካዱ የጀሐነም ቅጣት አለላቸው። በእርግጥ ማረፊያው የከፋ ነው።

የጀሐነም እሳት

የጀሐነም እሳት እጅግ በጣም የጋለ እና ሙቅ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ እሱ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ትርሚዚ)

“ይች የእናንተ እሳት ከሰባ የጀሐነም እሳት አካል አንዷ አካል እንጅ ሌላ አይደለችም።”

ጀሀነም እጅግ በጣም ሰፊ ነው። ሰዎች ወደ እሷ ከተወረወሩ ቡኋላ እንዲህ ትባላለች

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ቃፍ 50፡30)

ጀሐነም ሞላሽ እንዴ? በምንል ቀን፤ ሌላ ተጨማሪ የሚመጡ ካሉ ትላለች።

ማቀጣጠያዎቿ ሰዎች እና ድንጋዮች ናቸው። በእሷም ላይ የተሾሙ ጥብቅ ሃይለኛ መልአክቶች (መላኢካ) አሉ። ከአሏህ የተቀበሉትን ትዕዛዛት ከመፈፀም ፍንክች አይሉም። የታዘዙትን ነገር በትክክል ይፈፅማሉ።

 ዘቁም

ወደ እሷ የሚገቡ ሰዎች ምግብ ዘቁም (የሚመር ፣ የሚያስጠላ ፣ የሚሰነፍጥ ሽታ እና ጣዕም ያለው ዛፍ) ነው። መጠጣቸው ሐሚም (እጅግ በጣም የፈላና የሚፍለቀለቅ ውሃ) እና ገአሳቅ (ከቁስል የሚወጣ ፈሳሽ እና መግል) ነው።

ልብሳቸው ከእሳት የተሰራ ነው። የፈላ ውሃ በእራሳቸው ላይ ይደፋባቸዋል፤ ቆዳቸው እና በሆዳቸው ውስጥ ያለው ሁሉ ይቀልጣል፤ ይፈርሳልም።

ከእሷ ጭንቀት መውጣት ሲፈልጉ ወደ እሷ እንደገና ተመልሰው ይወሰዳሉና “የመቃጠልን ቅጣት ቅመሱት› ይባላሉ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“በትንሳኤ ቀን ከጀሐነም እሳት ሰዎች መካከል ትንሽየ ቅጣት ያለው ሰው ከእግሩ ጉበን ላይ ፍም (እሳት) ተደርጎበት በእሷ አንጎሉ እንዲፈላ የሚደረግ ሰው ነው።

ጀነት ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share