እስልምና የሰላም ሃይማኖት

Author picture
እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ያዘዘው መልካም ነገር እንጂ ሌላ መልካም ነገር የለም፤ እንዲሁም እርሱ የከለከለው ክፉ ነገር እንጂ ሌላ ክፉ ነገር የለም።

እስልምናን በተግባር ማዋል ሁሉም ሰው መብቶቹ በተጠበቁበት ስርዓት ውስጥ በደህንነት እና በሰላም እንዲኖር ዋስትና ይሰጣል።

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንዐም 6:151-152)

“ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ (በአላህ) ምንንም ነገር አታጋሩ፡፡ ለወላጆችም በጎን ሥራ (ሥሩ)፡፡ ልጆቻችሁንም ከድህንት (ፍራቻ) አትግደሉ፡፡ እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና፡፡ መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለጸውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ፡፡ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጅ አትግደሉ፡፡ ይህን ታውቁ ዘንድ (አላህ) በእርሱ አዘዛችሁ፡፡ የየቲምንም ገንዘብ ብርታቱን (አካለ መጠን) እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጅ አትቅረቡ፡፡ ስፍርንና ሚዛንንም በትክክሉ ሙሉ፡፡ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም፡፡ በተናገራችሁም ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም እንኳ (እውነትን በመናገር) አስተካክሉ፡፡ በአላህም ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ እነሆ ትገሰጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡”

ከዚህ በተጨማሪ አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ነህል 16: 90)

“አላህ በማስተካከል ፣ በማሳመርም ፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር) ፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡”

ስለሆነም የእስልምና ሃይማኖት ሰላምን ያዘለ ሁሉን አቀፍ ሃይማኖት ነው። ይህ አላህ እንዳለው የሙስሊሙን ማህበረሰብ ውስጣዊ ደረጃ ይመለከታል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አህዛብ 33:58)

“እነዚያንም ምእምናን እና ምእምናነት ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትን እና ግልጽ ሃጢያትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡”

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም የተስማሙበት ሀዲስ)

“ሙስሊም ማለት በምላሱ እና በእጁ (ሰዎችን ከመጉዳት) የተጠበቀ ሰው ነው። (ስደተኛ) ማለት ደግሞ አላህ የከለከለውን ነገር የተወ ሰው ነው።”

እንዲሁም ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቲርሚዚ)

“አማኝ ማለት ሰዎች የሚያምኑት ሰው ነው።”

እስልምና በደህንነት ፣ በረጋ መንፈስ እና በእስልምና መሰረቶች ላይ በተመሰረቱ ወዳጃዊ ግንኙነቶች አማካኝነት በአለም አቀፍ ደረጃም ሰላምን ያረጋግጣል።

ከዚህም በላይ የሙስሊም ማህበረሰብ በሌላ ማህበረሰብ ላይ በተለይም በእምነታቸው ላይ ቅን በሆኑት ላይ ጥቃት አይሰነዝርም፡፡

በደጋፊዎቿ ላይም ጠላትነትን አያነሳም። አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 2:208)

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በሙሉ እምነት (በእስልምና) ውስጥ ግቡ፤ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና።”

የእስልምና እምነት ፍትህን ያዛል፣ ጭቆናንም ይከለክላል፣ እነዚያን መርሆች የሚቃወሙትንም እንኳ። አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ማኢዳ 5:8)

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች ፣ በፍትሕ መስካሪዎች ሁኑ። የሕዝቦች ጥላቻ ፍትህን ከመፈጸም አይከልክላችሁ። ፍትሃዊ ሁኑ፤ እርሱ ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። አላህንም ፍሩ፤ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጣዊ አዋቂ ነውና።”

አሰላም (የሰላም ምንጭ ፣ ከአላህ ውብ ስሞች አንዱ ነው፡፡) እንዲህ ብሏል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐሽር 59:23)

“እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ ፣ ንጉሡ ፣ ከጉድለት ሁሉ የጠራው ፣ የሰላም ባለቤቱ ፣ ጸጥታን ሰጪው ፣ ባሮቹን ጠባቂው ፣ አሸናፊው ፣ ኀያሉ ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡”

አሰላም ከጀነት ስሞች ውስጥ አንዱ ነው። ሃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንአም 6:127)

“ለእነሱ ጌታቸው ዘንድ የሰላም ሐገር አላቸው፤ እነርሱም ይሠሩት በነበሩት ምክንያት እሱ ረዳታቸው ነው፡፡”

አሰላም ከዚህም በላይ ሙስሊሞች በዚህ ዓለም እርስ በርስ ሰላምታ የሚለዋወጡበት ነው።

እንዲሁም በመጨረሻው ዓለም የጀነት ሰዎች ሰላምታ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አህዛብ 33:44)

“በሚገናኙት ቀን ሰላምታቸው «ሰላም» ነው፤ ለእነርሱም የተከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል።”

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

አንድ ሙስሊም ሌላ ሙስሊምን ሰላም ሲል “አሰላሙ አለይኩም!” ሲል ይሰማል። ይህ ሰላምታ ብቻ ሳይሆን ጸሎትም ነው፡፡

ሰላምታ ለሚሰጠውም ሆነ ለሚሰጠው ሰው መረጋጋት ፣ ደስታ እና ምቾት ያስገኛል። ይህ የሆነው በዚህ ሰላምታ ውስጥ የደህንነት እና የሰላም መግለጫ በመሆኑ ነው።

ይህንን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአንድን ሰው እምነት ሙሉ ከሚያደርጉ ተግባራት ውስጥ አንዱ አድርገውታል። እንዲህም ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም፤ እስክትዋደዱም ድረስ አታምኑም። ብታደርጉት የምትዋደዱበትን ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አብዙ!”

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ይህ ከምርጥ ተግባራት አንዱ እንደሆነ አስተምረውናል።

ይህ የሆነበት ምክንያት ሰላምታ ሲሰጥም ሆነ ሲሰማ ልቦችን ስለሚያቀራርብ እና ስለሚያለዝብ ነው።

እንዲሁም ልዩነቶችን እና ጥላቻን ያስወግዳል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)

“ከእስልምና ክፍል የትኛው ነው በላጭ?” ተብለው በተጠየቁ ጊዜ “ሰዎችን መመገብ እና የምታውቀውንም ሆነ የማታውቀውን ሰው ሰላም ማለት ነው!” ሲሉ መለሱ።

ስለሆነም የእስልምና እምነት እንደ ጦርነት ፣ ትዳር ፣ ኢኮኖሚክስ ፣ ፖለቲካ ፣ አምልኮ እና ለመሳሰሉት ዘርፎች ደንቦች እና ህጎችን አውጥቷል።

ይህ የሆነው አንድ ሙስሊም ከጌታው ፣ ከማህበረሰቡ እና በአካባቢው ካለው ዓለም – የሰው ፣ የእንስሳት እና የእፅዋት አለም – ጋር ያለውን ግንኙነት ለመተግበር እና ለመቆጣጠር ያለመ ነው።

መላው የሰው ልጅ የእስልምናን መሰል ማምጣት አይችልም። ይህን የመሰለ ፍጹምነት እና ሁሉን አቀፍነት ያለው እምነት መቀበል ፣ ወደ እርሱ መጋበዝ እና ማክበር የተገባ ነው።

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

መብቶች በእስልምና

እስልምና ተከታዮቹ ለሰዎች የሚገባቸውን መብቶች እንዲሰጡ አዟል፡፡ ወላጆች ፣ ባለትዳሮች ፣ ልጆች ፣ ጎረቤቶች ወ.ዘ.ተ በዚህ አለም ውስጥ ባላቸው ልዩ ሚና መሰረት የተወሰኑ መብቶች አሏቸው፡

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share