አሰላም (የሠላም ምንጭ) ከአሏህ ስሞች መካከል አንዱ ነው። ኢስላም ማለት ደግሞ ሰላም ማለት ሲሆን ሙስሊሞች ሰላምታን የሚለዋወጡበት ቃልም ነው።
አሰላም

አሰላም (የሠላም ምንጭ) ከአሏህ ስሞች መካከል አንዱ ነው። ኢስላም ማለት ደግሞ ሰላም ማለት ሲሆን ሙስሊሞች ሰላምታን የሚለዋወጡበት ቃልም ነው። አሰላሙ አለይኩም “ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን” አንዱ ንግግር ነው።

አሏህ አማኞች ፈቃድ እንዲጠይቁና እርስ በእርሳቸው ሰላምታን እንዲለዋወጡ አዟቸዋል።

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 24፡27)

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእራሳችሁ ቤት ውጭ በሆኑ ቤቶች ሳታስፈቅዱና በውስጣቸው ያሉ ሰዎች ሰላም ሳትሉ አትግቡ። ይህ ለእናንተ ታስታውሱ ዘንድ መልካም ነው።”

አንድ ሙስሊም ሰላምታን በጥሩ መመለስ አለበት። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡86)

“ሰላምታ በቀረበላችሁ ጊዜ ከእሷ በበለጠ ሰላምታ መልሱ። ወይም እሷኑ መልሱ። በእርግጥ አሏህ ሁሉም ነገር ላይ ተቆጣጣሪ ነው።”

ሰላምታ

ሰላምታውን የሚጀምረው ሰው አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ (የአሏህ ሰላም ፣ እዝነት እና በረከት በእናንተ ላይ ይሁን) እንዲል ይመከራል።

ይህ ሰላምታ የቀረበለት ሰው ደግሞ “ወአለይኩም ሰላም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ”  (የአሏህ ሰላም ፣ እዝነት እና በረከት በእናንተም ላይ ይሁን ሲል መመለስ አለበት።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአንድ ሐዲስ ውስጥ እንደገለፁት አንድ ሰው እነዚህን ሐረጎች አብዝቶ በሰላምታው ውስጥ በተጠቀመ ቁጥር ብዙ ምንዳዎችን ያገኛል ብለዋል። ስለዚህ አንድ ሰው አሰላሙ አለይኩም ካለ አስር ሃሰና (ምንዳ) ያገኛል።

ወረህመቱሏሂ የሚለውን ከጨመረበት ሃያ ምንዳዎችን ያገኛል። ከዚህ በላይ ደግሞ ወበረካቱህ የሚለውን ከጨመረበት ሰላሳ ሃሰና (ምንዳዎች) ያገኛል።

ወጣቶች ለታላቆቻቸው ፣ ጥቂቶች ለብዙ ሰዎች ፣ ፈረስ የጋለበ ወይም መኪና የሚነዳ ሰው በእግሩ ለሚሄድ ሰው ፣ በእግሩ የሚሄድ ሰው ለተቀመጠ ሰው ሰላምታ ማቅረብ አለበት።

የተቸገሩትን ማብላት

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኢስላም በላጭ ስለሆነ ነገር በተጠየቁ ጊዜ እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ እና ሙስሊም)

“የተቸገሩትን ማብላት እና ለማታውቋቸውም ለምታውቋቸውም ሙስሊሞች ሰላታ ማቅረብ ነው።” ሲሉ መልሰዋል።

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share