ሐዲስ የነብዩ ሙሐመድ ንግግር እና አስተምህሮት

Author picture
ሐዲስ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፉ ንግግሮች ፣ የእሳቸው ስራዎች ፣ የዝምታ ማረጋገጫዎች ወይም ደግሞ የእሳቸው ባህርያት እና አካላዊ ቁመና ገላጭ የሆኑ ነገሮች ዘገባ ነው።
ሐዲስ

ሐዲስ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፉ ንግግሮች ፣ የእሳቸው ስራዎች ፣ የዝምታ ማረጋገጫዎች ወይም ደግሞ የእሳቸው ባህርያት እና አካላዊ ቁመና ገላጭ የሆኑ ነገሮች ዘገባ ነው።

ሐዲስ

ከንግግሮቹ ውስጥ አንድ ምሳሌ የሚሆነን “የስራዎች ሁሉ ምንዳ መሰረቱ ኒያ (ማሰብ) ነው። ሁሉም ሰው ባሰበው ነገር ላይ ሽልማት ያገኛል።” የሚለው ነው። (ቡኻሪ)

ከስራዎቹ ውስጥ አንድ ምሳሌ የሚሆነን የውዱእ አደራረግን አስመልክቶ የተላለፈው ዘገባ ነው።

የዝምታ ማረጋገጫ አንድ ምሳሌ የሚሆነን፤ አንዳንድ ሶሃቦች በሰሩት ስራ በጉዳዩ ላይ ዝም በማለት እነሱን ባልከለከሉት ፣ ባልወቀሷቸው እና የተግባሩን መፈቀድ በዝምታቸው ያረጋገጡበት ነው።

በእስልምና ሃይማኖት ሐዲስ ከቁርአን ቀጥሎ ሁለተኛው የእስልምና ህግጋት ምንጭ ነው። በጣም ታዋቂ ከሆኑ የሐዲስ መጽሐፍት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

የሐዲስ መጽሐፍት
  1. ሰሂህ አል-ቡኻሪ
  2. ሰሂህ ሙስሊም
  3. ጃሚ አትርሚዚ
  4. ሱነን አነሳኢ
  5. ሱነን ቡዳውድ
  6. ሱነን ኢብን ማጃ

ሐዲስ ሁለት ቅርንጫፎች አሉት። እነሱም ኢስናድ እና መትን ናቸው።

ኢስናድ ማለት በእያንዳንዱ ዘገባ ውስጥ የዘጋቢዎች ትስስር እና እስከ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ድረስ ያለውን ሰንሰለት የሚያሳይ ነው። መትን ማለት ደግሞ ፅሁፉ ራሱ ነው።

ሐዲሰል ቁድሲ ተመልከቱ

Related posts

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ (ቅዱስ ወይም መለኮታዊ ንግግር) ማለት ትርጉሙ ከአሏህ የሆነ፤ የቃላት አቀማመጡ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሆነ ንግግር ነው። የሚከተለው ሐዲስ የሐዲሰል ቁድስ አንድ ማሳያ ምሳሌ ነው።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share