የምዕመናን እናት ያስተላለፏቸው ሐዲሶች

Author picture
በሐዲስ የተመሰከረላቸው እናቶቻችን! ከሙዕሚኖች እናት የተገኙ ውድ ሐዲሶችና ስለ ልዩ ደረጃቸው የሚያበስሩ አስተማሪ ዘገባዎች።

መግቢያ

ስለተወዳጆቹ የምዕመናን እናት የላቀ ደረጃና ክብር ከምንጩ ለማወቅ ፈልገው ያውቃሉ? የእነሱ ታላቅነት የሚገለጠው በግል ታሪካቸው ብቻ ሳይሆን ነብዩ (ﷺ) ስለነሱ በመሰከሩትና እነሱም ራሳቸው ለአለም ባስተላለፉት ውድ ሐዲሶች ነው።

ይህ ጽሑፍ የግል አስተያየት ሳይሆን በቀጥታ ከሐዲስ መዛግብት የተገኙ እውነተኛ ዘገባዎችን ያቀርብልዎታል።

ከኸዲጃ (ረ.ዐ) የጀነት ብስራት እስከ ጀወይሪያ (ረ.ዐ) የዚክር ትምህርት ድረስ፤ እያንዳንዱ ሐዲስ የእናቶቻችነን ልዩ ክብርና በዲናችን ውስጥ ያላቸውን ወሳኝ ሚና ያሳያል።

በእነዚህ ወርቃማ ቃላት ውስጥ የተደበቀውን ጥበብና ትምህርት አብረን እንመርምር።

የምዕመናን እናት ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረ.ዐ)

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንዴ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጥቶ እንዲህ አላቸው፡ “የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ኸዲጃ ምግብ ወይም መጠጥ ያለበት ዕቃ ይዛ መጥታለች። ስትደርስ ከጌታዋና ከእኔ ሰላምታን አቅርብላት። በጀነት ውስጥ ከዕንቁ የተሰራ ፣ ጫጫታና ድካም የሌለበት ቤት እንደሚኖራት አበስራት።” (ቡኻሪ 3820 እና ሙስሊም 2432)

የምዕመናን እናት አኢሻ ቢንት አቢ በክር (ረ.ዐ)

አቡ ሙሰል አሽአሪ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ “ብዙ ወንዶች ፍጽምና ላይ ደርሰዋል። ከሴቶች ግን ከኢምራን ልጅ መርየም እና ከፈርዖን ሚስት አሲያ በስተቀር ፍጽምና ላይ የደረሰ የለም። የአኢሻ በሴቶች ላይ ያላት ብልጫ ልክ ሰሪድ (ከፍተኛ ጥራት ያለው ምግብ) በሌሎች ምግቦች ላይ እንዳለው ብልጫ ነው።” (ቡኻሪ)

የምዕመናን እናት ሐዲሶች

የምዕመናን እናት ሐፍሷ ቢንት ኡመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ)

አነስ ኢብን ማሊክ እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐፍሷን ከፈቷት በኋላ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ወደ እሳቸው መጥቶ እንዲህ አላቸው፡ “ሙሐመድ ሆይ! ሐፍሷን ፈታሃትን? እሷ እኮ ፆመኛና ለሊት ሰጋጅ ናት። በጀነትም ውስጥ ሚስትህ ናትና መልሳት።” (ሐኪም በሙስተድረክ ውስጥ ዘግቦታል፡ 6836)

የምዕመናን እናት ዘይነብ ቢንት ጀህሽ (ረ.ዐ)

የሙዕሚኖች እናት አኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ አለች፡ የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለሚስቶቻቸው “ከእናንተ ውስጥ እኔን ቶሎ የምትከተለኝ (በሞት) እጇ ረጅሙ ናት” አሏቸው። አኢሻ እንዳለችው፤ እነሱም የትኛቸው እጅ እንደሚረዝም ይለካኩ ነበር። ረጅሙ እጅ የነበራት ዘይነብ ነበረች፤ ምክንያቱም በእጇ ትሰራና ምጽዋት ትሰጥ ነበር። (ቡኻሪ 1420)

የምዕመናን እናት መይሙና ቢንት አል-ሐሪስ (ረ.ዐ)

ከኢብኑ አባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ምዕመናት እህትአማቾቹ ናቸው፡፡ እነሱም፡- የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባለቤት መይሙና ፣ ኡሙል ፈድል አል-ሐሪስ የሐምዛ ባለቤት ሰልማ እና አስማ ቢንት ኡመይስ፣ እሷም የእናታቸው ልጅ በመሆኗ እህታቸው ናት፡፡›› (ሐኪም በሙስተድረክ መጽሐፋቸው በሐዲስ ቁጥር 6801 ላይ ዘግበውታል፡፡) እንዲህም ብለዋል፡ (ይህ ሐዲስ) በኢማሙ ሙስሊም መስፈርት መሰረት ሶሂህ (ትክክለኛ) ነው፡፡

የሙዕሚኖች እናት የምዕመናን እናት ሶፊያ ቢንት ሁየይ (ረ.ዐ)

ከአነስ (ረ.ዐ) ተይዞ እንደተወራው ሐፍሷ (ረ.ዐ) ሶፊያን (ረ.ዐ) “የአይሁዳዊ ልጅ” እንዳለቻት ወሬ ደረሳት፡፡ ሶፊያም አለቀሰች። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) እያለቀሰች ሳለ ወደ እሷ ገቡና “የሚያስለቅስሽ ምንድን ነው?” አሏት። እሷም “ሐፍሷ የአይሁዳዊ ልጅ አለችኝ” ስትል መለሰች። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሏት፡ “አንቺ የነብይ ልጅ ነሽ፣ አጎትሽም ነብይ (ነብዩሏህ ሙሳ) ነው ፣ አንቺም እኮ ያለሽው ከነብይ (ከሙሐመድ) ጋር በትዳር ነው፡፡ ታዲያ በምን ትበልጥሻለች (ትፎካከርብሻለች)?” ካሉ በኋላ “ሐፍሷ ሆይ! አሏህን ፍሪ” አሉ። (ትርሚዚ ዘግበውታል 3894)

የሙዕሚኖች እናት ጀወይሪያ ቢንት አል-ሐሪስ (ረ.ዐ)

ኢብን አባስ (ረ.ዐ) ከጁወይሪያ (ረ.ዐ) ይዞ እንዳወራው፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ቀን ማለዳ መስገጃ ቦታዋ ላይ ሆና አለፉት፡፡ ከዚያም እኩለ ቀን አካባቢ ሲመለሱ አሁንም በዚያው ሁኔታ ላይ ሆና አገኟትና “አሁንም በነበርሽበት ሁኔታ ላይ ነሽ?” አሏት። እሷም “አዎን” አለች። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሏት፡- “የምትያቸውን ቃላት አላስተምርሽምን? ‘ሱብሃነሏሂ ዐደደ ኸልቂሂ’ (በፍጥረቱ ብዛት ልክ ለአላህ ጥራት ይገባው) ሶስት ጊዜ ፣ ‘ሱብሃነሏሂ ሪዷ ነፍሲሂ’ (በነፍሱ ውዴታ ልክ ለአላህ ጥራት ይገባው) ሶስት ጊዜ ፣ ‘ሱብሃነሏሂ ዚነተ አርሺሂ’ (በአርሹ ክብደት ልክ ለአላህ ጥራት ይገባው) ሶስት ጊዜ ፣ ‘ሱብሃነሏሂ ሚዳደ ከሊማቲሂ’ (በቃላቱ ብዛት ልክ ለአላህ ጥራት ይገባው) ሶስት ጊዜ በይ።” (ሙስሊም)

የሙዕሚኖች እናት ዘይነብ ቢንት ኹዘይማ (ረ.ዐ)

ዘይነብ (ረ.ዐ) “የምስኪኖች እናት” በመባል ትታወቅ ነበር። ኢብን ከሲር እንዳሉት ይህ የሆነው ለምስኪኖች በብዛት ምጽዋት በመስጠቷ ፣ በደግነቷና በመልካምነቷ ነው። (ኢብን ከሲር፡ አልቢዳያ ወኒሃያ 5/581)

የምዕመናን እናት ማሪያ አል-ቂብጢያ (ረ.ዐ)

ማሪያ (ረ.ዐ) በ16ኛው ዓመተ ሂጅራ በሙሐረም ወር ሞተች። ኡመር (ረ.ዐ) ለቀብሯ ሥነ-ስርዓት ሰዎችን ሰብስቦ ነበር፤ ሶላቱም በአል-በቂዕ ተሰግዶባታል።

የሙዕሚኖች እናት ኡሙ ሐቢባ (ረ.ዐ)

ኡሙ ሐቢባ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “በቀን እና በሌሊት አሥራ ሁለት ረከዓ የሰገደ ሰው ጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል።” ኡሙ ሐቢባ እንዲህ ትላለች፡ ‹ይህን ከአሏህ መልዕክተኛ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ (እነዚህን ረከአዎች) ትቻቸው አላውቅም።

አምር ኢብን አውስም እንዲህ አለ ‹‹ከአንበሰህ ከሰማኋቸው ጊዜ ጀምሮ ትቻችው አላውቅም፡፡››

ኑዕማን ኢብኑ ሳሊምም (ይህን ከአምሩ ኢብን አውስ የሰሙት) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከአምር ኢብን አውስ ከሰማኋቸው ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም፡፡››

ዘጋቢ፡ ኡሙ ሐቢባ የምዕመናን እናት

የምዕመናን እናት ኡሙ ሰላማ (ረ.ዐ)

አነስ ኢብን ማሊክ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የኡሙ ሰላማን ልጅ ዘይነብ ጋር ይጫወቱና ደጋግመው “ያ ዙወይኒብ! ያ ዙወይኒብ!” ይሏት ነበር። (ዙወይኒብ የሚለው ቃል ዘይነብ የሚለው ስም በአረብኛ ሲቆላመጥ ነው)

ክፍል 12

ከኡስማን ኢብን አብዲላህ ኢብን መውሀብ (ረ.ዐ) ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ፡ ‹‹ወደ ኡሙ ሰላማ ቤት ገባሁ፤ እሷም የተቀለሙ የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፀጉሮች አወጣችልን። በሌላ ዘገባ ደግሞ ኡሙ ሰላማ ቀይ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፀጉር አሳይታቸዋለች።

የሙዕሚኖች እናት ሰውዳ ቢንት ዘምዓ (ረ.ዐ)

ከአኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው እንዲህ አለች፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሰውዳ ቢንት ዘምአህን አገቡ፡፡ የሰውዳ ወንድም አብድ ኢብን ዘምዓ ከሐጅ ሲመለስ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እህቱን ማግባታቸውን ሲሰማ በሐዘን አፈር በራሱ ላይ መነስነስ ጀመረ። እስልምናን ከተቀበለ በኋላ “ነብዩ ሰውዳን በማግባታቸው አፈር በራሴ ላይ የነሰነስኩበት ቀን ምንኛ ሞኝ ነበርኩ” ብሏል።

ክፍል 14

የምዕመናን እናት አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው እንዲህ አለች፡ ‹‹በቆዳዋ (በእሷ ማንነት) ውስጥ መሆን ከምመኘው ከሰውዳ ቢንት ዘምአህ በለጠ የምወዳት ሴት አላየሁም፡፡ በውስጧ ጥንካሬ (ቁርጠኝነት) ያላት ሴት ነበረች፡፡›› አኢሻም ቀጠለችና እድሜዋ በገፋ ጊዜ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር የነበራትን ቀን ለአኢሻ ሰጠቻት፡፡ እንዲህም አለች፡ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ከእርስዎ ጋር ያለኝን ቀን ለአኢሻ ሰጥቻታለሁ፡፡ ከዚያም የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለአኢሻ ሁለት ቀናትን ይመድቡ ነበር፡፡ የራሷን ቀን እና የሰውዳን ቀን፡፡

የሒጃብ አንቀፅ የወረደበት ምክኒያት

ሂጃብየምዕመናን እናት አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው እንዲህ አለች፡ ‹‹ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶቻቸውን እንዲሸፍኑ (ሒጃብ እንዲያደርጉ) ይነግራቸው ነበር። ነገርግን (በዚያን ጊዜ) አላደረጉም ነበር፡፡ የነብዩ ባለቤቶች በሌሊት ወደ መናሲዕ (መፀዳጃ ቦታ) ይወጡ ነበር፡፡ አንድ ቀን ሰውዳ (ረ.ዐ) ወጣች፤ ረጅም ሴት ነበረች፡፡ ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) በመሰብሰቢያ ቦታ ላይ ሆኖ አያትና “ሰውዳ ሆይ! አውቄሻለሁ አላት፡፡ ይህም የሒጃብ አንቀጽ እንዲወርድ በመጓጓት ነበር። ከዚያም አሏህ (ሱ.ወ) የሒጃብን አንቀፅ አወረደ።

ማጠቃለያ

እነዚህ የተመረጡ ሐዲሶች እንደሚያሳዩን ፣ የምዕመናን እናት ደረጃ በአላህና በመልዕክተኛው (ﷺ) የተረጋገጠ ነው። እያንዳንዱ ዘገባ—ስለ ዒባዳቸው ፣ ስለ ቸርነታቸው ፣ ስለ ክብራቸው የተነገረው—ለእኛ እንደ መመሪያ ብርሃን ያገለግላል።

ከእነዚህ ትክክለኛ ሐዲሶች የምንወስደው ትምህርት ፣ የእነሱን ፈለግ እንድንከተልና በህይወታችን ውስጥ የእነሱን መልካም ባህሪያት ለማንጸባረቅ እንድንጥር ያነሳሳናል።

ከእነዚህ ሐዲሶች ውስጥ እርስዎን በጣም የነካዎትና አዲስ ነገር ያስተማረዎት የትኛው ነው? አስተያየትዎን ከታች ያካፍሉን።

Related posts

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ (ቅዱስ ወይም መለኮታዊ ንግግር) ማለት ትርጉሙ ከአሏህ የሆነ፤ የቃላት አቀማመጡ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሆነ ንግግር ነው። የሚከተለው ሐዲስ የሐዲሰል ቁድስ አንድ ማሳያ ምሳሌ ነው።

Read More »

የነብዩ ሱና

የእስልምና ሃይማኖት በሁለት ምንጮች ላይ የተመሰረተ ነው። እነሱም ቅዱስ ቁርአን እና የነብዩ ሱና ናቸው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እውነት እና በኢስላም ውስጥ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share