ክፍል አንድ
በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት አቡ ኹረይራ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ጅብሪል(ዐ.ሰ) ወደ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) መጣና እንዲህ አለ፦ "የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ለየት ያለ ምግብ እና መጠጥ ወደ አንተ ይዛ የምትመጣው ኸድጃ ናት። ወደ አንተም በደረሰች ጊዜ በአሏህ ስም ሰላምታ አቅርብላት። በጀነት ውስጥ ምንም ጫጫታም ሆነ ልፍት የሌለበት የሆነ፤ ከቀሰብ የተሰራ ቤተ-መንግስት ያላት መሆኑን የምስራች ስጣት" አለ።
ጠንካራ ባህሪዋና ታላቅ ስብዕናዋ በጅብሪል አማካኝነት የአሏህን ሰላምታ በማግኘት ይህን የመሰለ ክብር አግኝታለች። ታማኝ ፣ ሃቀኛ ፣ መልካም ባህሪን የተላበሰች ፣ ለጋስ ፣ ቸር ፣ ምራቋን የዋጠች ሴት ስትሆን ያደገችውም በሃብትና በቅንጦት ላይ ነበር።
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጥሪ ባደረጉላት ጊዜ እስልምናን ሃይማኖቷና የህይወት ጎዳናዋ አድርጋ የተቀበለች የመጀመሪያዋ እንስት እሷ ናት።
በአሏህ (ሱ.ወ.ተ) እና በጅብሪል (ዐ.ሰ) ሰላምታ የቀረበላት ሲሆን በዚህ በኩል ክብርን ያገኘች የመጀመሪያዋ ሴት ናት።
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያ ሚስታቸው እሷ ስትሆን በህይወት ዘመኗም በድጋሚ ሌላ ሴት አላገቡም ነበር። በሰላም ፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ ከ24 ዓምት በላይ ኑረዋል።
በሷም ቤት ውስጥ ነበር የአሏህ ራዕይ በጅብሪል አማካኝነት የሚገለፅላቸው። በዛ መከራ ጊዜ የድሎት ህይወቷን መስዋዕት በማድረግ አለሁልህ ከጎንህ ነኝ ትላቸው ነበር።
ኸድጃ (ረ.ዐ) የተወለደችው በመካ ውስጥ ሲሆን የእናቷ ስም ፋጢማ ቢንት ዘይድ እና የአባቷ ስም ደግሞ ኽወይሊድ ቢን አሰድ ይባላል። አባቷ በጣም ሃብታም የሆነ የንግድ ሰው ሲሆን ከቁረይሾች ጎሳ መካከል የታወቀ መሪም ነበር። ሆኖም የሞተው ፉጃር በተባለ ጦርነት ላይ እየተዋጋ እያለ ነው።
ኸድጃ (ረ.ዐ) አቡ ሐላህን አግብታ ሁለት ልጆች የወለደችለት ሲሆን ልጆቹም ሐላህ እና ሒንድ ይባላሉ። ሁሌም ባሏ ባለፀጋና ትልቅ የንግድ ሰው ሆኖ ማየት ትመኝ ነበር። ነገርግን የአሏህ ውሳኔ ሆኖ ብዙም ሳይቆይ ዱንያን ተሰናበተ።
ከሆነ ጊዜ ብኋላም ወጣቷ ጋለሞታ ኸድጃ (ረ.ዐ) አቲቅ ቢን አይስ ቢን አብዱሏህ አል-መክዙሚ የተባለ ሰው አግብታ ሒንዳ የተባለች ልጅ ወለደች። ነገርግን ባለመመቻቸት ጉዳይ ብዙም ሳይቆዩ ትዳራቸው ፈረሰ።
ከዚህ ሁሉ ብኋላ ትኩረቷ ልጆቿን ተንከባክባ ማሳደግ እና ከአባቷ የወረሰችውን ንግድ ማደራጀትና ማስቀጠል ሆነ።
የነበራት ብልጠትና የንግድ ክህሎቷ ከቁረይሾችበአካባቢዋ መካከል የታወቀች የንግድ ሰው እንድትሆን አስችሏታል። አላማዋ ጠንካራና ታማኝ የሆነ ሠራተኛ መቅጠር ነበር።
ምክኒያቱም እንደዛሬ ያኔ ምቹ መጓጓዧም ሆነ የመግባቢያ መንገድ አልነበረምና እራቅ ወዳለ ቦታ በመጓዝ ሁሉንም የንግድ ሸቀጦቿን በመቆጣጠር የሚገበይላት ሰው ትፈልግ ስለነበር ነው። ሸቀጦቿን የምታስመጣው ልክ እንደ ሶርያ ራቅ ካለ ቦታ ሲሆን ንግዷን የሚቆጣጠርላት፤ የሚሸጥ የሆነ ሸቀጥ ከእንደዚህ አይነት ራቅ ካሉ ገበያዎች ገዝቶ የሚያመጣላት ሰው ትፈልጋለች።
በዛ ላይ መካ ለንግድ አመች የሆነች ቦታ ላይ በመሆኗ ንግዳቸው ትርፋማ ነበር። ንግዷን የሚቆጣጠርላት ሰውም የትርፍን ሃምሳ በመቶ (50%) የሚያገኝ ሲሆን ይህም ለነሱ በቂ ማበረታቻ ነበር።
ይህኔ ነበር ኸድጃ (ረ.ዐ) ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታማኝነት ፣ ስለ መልካም ባህሪያቸውና ስለ ውብ ስብዕናቸው የሰማችው። እናም ሸቀጧን ለንግድ ይዘውላት ይሄዱ ዘንድ የስራ ውል አቀረበችላቸው።
እሳቸውም ጥያቄዋን በደስታ ተቀብለው ለሷ መስራት ጀመሩ። አንድ የንግድ ጉዞ ላይ ታማኝ የድሮ ባሪያዋ መይሰራ እንዲያጅባቸውና አንዳንድ ነገር እንዲያግዛቸው በማሰብ አብራ ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጋር አያይዛ ለንግድ ላከቻቸው።
ይህ የንግድ ጉዞ እጅግ በጣም ትርፋማ ሲሆን በዚህ የንግድ ጉዞ ላይ መይሰራ በተመለከተው የሚያስደንቁ ክስተቶች ተገረመ። መልካም ባህሪያቸው ፣ የንግድሲል መርሆዋቸው ፣ ታመኝ ግብይታቸው እና የንግድ ክህሎታቸው ልቡን ገዛው።
ከሶርያም በመመለስ ላይ እያሉ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ የዛፍ ጥላ ስር ለተወሰን ጊዜ እረፍ አሉ። በዚህ ቅፅበት ነስቶራ የተባለ የአይሁዳ መነኩሴ ተመለከታቸውና መይሰራን ይህ ሰው ማነው? ጠየቀው።
መይሰራም ስለ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የሚያውቀውን ስብዕናቸውን ፣ ታማኝነታቸውን እና ጉብዝናቸውን ሁሉ ነገረው። ነስቶራም ይህ ሰው ወደ ፊት ወደ ነብይነት ከፍይላል ከዚች ዛፍ ማንም አያርፍም እርሱ ነብይ ቢሆን እንጅ አለ።
ወደ ቤት በተመለሱ ጊዜ መይሰራ ለኸድጃ ወደ ሶርያ ባደረጉት ጉዞ ላይ የተከሰተውን እና ያስተዋለውን ነገር ሁሉ ነገራት። ታዲያ ይህን ስትሰማ ውስጧ ላይ ደስታም ፍርሃትም አድሮባት ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የትዳር ጥያቄ ለማቅረብ ማሰላስል ጀመረች።
ፍርሃቷ ከዚህ በፊት ከታላቅ የቁረይሽ ቤተሰቦች የቀረባላትን ብዙ የትዳር ጥያቄዎች ባለመቀበሏ ሃሳቧንቤተሰቦች እንዴት ለሳቸው መግለፅ እንደምትችል አስጨንቋት ነው።
ሃሳቤን እንዴት አድርጌ ልገለፅለት እችላለሁ? ጎሳዎቼ ጥያቄየን እንዴት ያዩት ይሆን? ቤተሰቦቼስ ምን ይሉ ይሆን? ከዚህም በላይ ይህ ያላገባ የቁረይሽ ወጣት ጥያቄየን ይቀበለኝ ይሆን? ስትል አሰበች።
ኸድጃ (ረ.ዐ) ከዚህ በፊት ከታላቅ የቁረይሽ የቀረባላትን ብዙ የትዳር ጥያቄዎች ባለመቀበሏ የትዳር ጥያቄዋን እንዴት ለሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መግለፅ እንደምትችል አስጨንቋታል።
ሃሳቤን እንዴት አድርጌ ልገለፅለት እችላለሁ? ጎሳዎቼ ጥያቄየን እንዴት ያዩት ይሆን? ቤተሰቦቼስ ምን ይሉ ይሆን? ከዚህም በላይ ይህ ያላገባ የቁረይሽ ወጣት ጥያቄየን ይቀበለኝ ይሆን? ስትል አሰበች።
እነዚህን ጥያቄዎች እያብሰለሰለች ከራሷ ጋር ሙግት ገጠመች። አንድ ቀን ለሊት ፀሀይ ከሰማይ ወርዳ ወደ አጥር ግቢዋ ገብታ ቤቷን በብርሃን ጨረሯ ስትፈነጥቀው ህልም አየች።
በነቃች ጊዜ ይህን ድንቅ ህልሟን ወደሚፈታላት የአጎቷ ልጅ ወረቃ ኢብን ነውፈል ሄደች። ወረቃ ኢብን ነውፈል አይነበሲር ሰው ሲሆን ህልም በመፍታት ጥበቡ ፣ ባለው ጥልቅ የተውራት እና የኢንጅል እውቀቱ ይታወቃል።