አሏህ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2:164)
“በእርግጥ በሰማያት እና በምድር አፈጣጠር ፣ በሌሊት እና በቀንም መፈራረቅ ፣ ሰዎችን በሚጠቅም ነገር በባሕር ላይ በሚጓዙ መርከቦች ፣ አላህም ከሰማይ ካወረደው ዝናብ በኋላ ምድርን በሕይወት በማደስና በውስጧም ከእንስሳት ሁሉ በመበተን ፣ የነፋሶችንም አቅጣጫና በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ደመናን በመቆጣጠር ለአስተዋዮች ምልክቶች አሉ።”

ቁርአን ማንበብ እና መፃፍ የማይችሉ ለነበሩት ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የወረደው ነው። ሕዝቦቻቸውም በአብዛኛው ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ነበሩ። ታዲያ እንዲህ ያለ ሰው እጅግ በጣም አንደበተ ርቱዕ የሆኑ ሰዎችን ያስደነቀ ቅዱስ መጽሐፍ እንዴት ሊያመጣ ቻለ?
አላህ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢስራዕ17:88)
“«ሰዎች እና ጅኖች የዚህን ቁርአን መሰል ለማምጣት ቢሰበሰቡ እና ከፊላቸው ለከፊላቸው ረዳቶች ቢሆኑም እንኳ መሰሉን አያመጡም» በላቸው።”
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ብዙ ባልደረቦቻቸው ድሆች ነበሩ። እሳቸውም ሳይንሳዊ እውነታዎችን የያዙ የቁርአን አንቀጾችን ያነቡላቸው ነበር። ቁርአን ከወረደ ከ1400 ዓመታት በኋላ ዘመናዊው ሳይንስ እነዚህን እውነታዎች በላቁ መሣሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች አሁን እየደረሰባቸው ነው!
ቶማስ ካርላይል እንዲህ ብሏል፡-

“ሐሰተኛ ሰው ሃይማኖትን አገኘ? እንዴት! ሐሰተኛ ሰው የጡብ ቤት እንኳን መሥራት አይችልም! ጭቃውን ፣ የተቃጠለውን ጡብ እና ሌሎች የሚጠቀምባቸውን ነገሮች በትክክል ካላወቀ እና ካልተከተለ የሚሠራው ቤት ሳይሆን የቆሻሻ ክምር ነው። አንድ መቶ ሰማንያ ሚሊዮን ሰዎችን ለማኖር ለአሥራ ሁለት ምዕተ ዓመታት አይቆይም፤ ወዲያው ይፈርሳል።” (1)
(1) ቶማስ ካርላይል፣ በቪክቶሪያ ዘመን የነበረ ስኮትላንዳዊ ጸሐፊ፣ ድርሰት ጸሐፊ፣ የታሪክ ጸሐፊ እና አስተማሪ። ጥቅሱ የተወሰደው ከድርሰቶቹ ስብስብ፣ On Heroes, Hero-Worship, and the Heroic in History ከተባለው ነው።

Share