የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 2

Author picture

Table of Contents

ክፍል ሁለት

የአያታቸው ሞት

አያታቸው አብዱል ሙጦሊብ ሲሆኑ የሞቱት ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የስምንት አመት እድሜ ልጅ እያሉ ነው። አያታቸው በጣም የተከበሩ የመካ መሪ እና የካዕባ ጠንካራ ጠባቂዎች ናቸው።

እሳቸውም የሞቱት በ84 አመታቸው ሲሆን አያታቸው ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጣም ተወዳጅና ብቸኛው የአብዱሏህና የአሚና ልጅ መልከ መልካም የሙትልጅ ስለነበሩ በጣም ጥልቅ ፍቅር ነበራቸው።

የአቡጧሊብ ደጋፊነት

አቡጧሊብ በጣም ተወዳጅ የሆኑት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አጐት ናቸው። የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አያት ከመሞታቸው በፊት ለአቡጧሊብ ተንከባክቦ እንዲያሳድጋቸው በአደራ መልክ ሰጧቸው።

አቡጧሊብ አሁን ሃላፊነቱ ተቀብለው ተንከባክበውና ማህበራዊ አድርገው በጥልቅ ፍቅርና ውዴታ አሳደጓቸው። በዚህ ጊዜ ነበር ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የንግድን ጥበብ የተማሩት።

የነብዩ ሙሐመድ ሥራ

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወጣት ሲሆኑ በቤተሰብ ስራ ላይ አዘነበሉ። ነገር ግን ምንም ገንዘብ አልነበራቸውም። ታላቋ ሴት ኸድጃ በጣም ሃብታም ነጋዴ ስትሆን ለተወሰነ ጊዜ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የንግድ ሸቀጦችን በአደራ መልክና በተቆጣጣሪነት በአጐታቸው በኩል የተሰጡ ሲሆን ኸድጃም በታማኝነታቸው ፣ ባማረ ስብዕናቸው ፣ በኑሮ ዘዴያቸው ፣ በግብይት ስርአታቸውና ከሰው ጋር ባለቸው ቅርርብ ትደመም ነበር።

እናም እሷ እራሷ ለንግድ ሸቀጦቿን ይዘውላት እንዲሄዱ ጠየቀቻቸው። አብዛኛውን ስራዎቿን ለሳቸው ሰጠች። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከዚህ ብኋላ ታማኝና ታላቅ የንግድ ሰው ሆኑ። በንግዳቸውም ብዙ ማትረፍ ጀመሩ። ኸድጃም በታላቅነታቸው ፣ በታማኝነታቸው ፣ በግብይት ስርአታቸው መደመሟን ቀጥላለች።

ከኸድጃ ጋር ያደረጉት ጋብቻ

የኸድጃ (ረ.ዐ) አገልጋይ የነበረው መይስራህ በግብይት ወቅት ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ይሆን ነበርና ሁልጊዜም ለኸድጃ የረሱልን ታላቅ ባህሪ ፣ ለጋስነትና ጨዋነት ይተርክላት ነበር።

ይህን ድንቅ ያማረና ታላቅ ስብዕናና ቅድስና በመስማት ኸድጃ (ረ.ዐ) ረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ለጋብቻ ጠየቀች። በጋብቻው ወቅት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የ25 አመት መልከ መልካም ወጣት የነበሩ ሲሆን ኸድጃ (ረ.ዐ) ደግሞ 40 አመቷ ነበር።

ከነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ከተጋባች ለ25 አመት ያህል ኑራለች። ይህን ተከትሎም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የጠቅላላ ስራዎቿ ተቆጣጣሪ ሆኑ። ሁሉንም ጊዜያቸውን ኃያሉ አሏህን በመገዛትም ያሳልፉ ነበር።

ነብዩ ሙሐመድ በሂራ ዋሻ ውስጥ ያደርጉት አምለኮተ አሏህ

የመካ ሙሽሪኮች እምነተ ቢሶች ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ተስፋ ለማስቆረጥ ያልጣሩትና ያላደረጉት ነገር የለም። ይሁን እንጂ በሂራ ዋሻ ጧት ማታ እዛው በመሆንና ምግብና ውሃ ይዘው በመሄድ የአምልኮት ተግባራቸውን ጀመሩ።

የሂራ ዋሻ ከመካ በስተቀኝ አቅጣጫ በኩል ከሚገኘው የኑር ተራራ ላይ ያለ ሲሆን እዚህ ዋሻ ውስጥ ነበር ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ያለማቋረጥ አሏህን ይገዙና ይለምኑ የነበረው። ምግብና ውሃቸው ካለላለቀ በቀር ወደ ከተማይቱ አይመለሱም።

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top