የነብዩ ሙሐመድ መልዕክት

Author picture
ሃያሉ አሏህ መልዕክተኞችን ከላቀ ጥበብ ጋር የላካቸው ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ ከሁሉም በላይ አልቆ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ (ማብቂያ) አድርጓቸዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እነዚህንም ጥበቦች እና ነብዩ በኡመታቸው ላይ ያላቸውን መብት ትማራላችሁ።

የትምህርቱ አጭር መግለጫ

ሃያሉ አሏህ መልዕክተኞችን ከላቀ ጥበብ ጋር የላካቸው ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከሁሉም በላይ አልቆ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ (ማብቂያ) አድርጓቸዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እነዚህንም ጥበቦች እና ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኡመታቸው ላይ ያላቸውን መብት ትማራላችሁ።

የትምህርቱ አላማ

  • መልዕክተኞች የተላኩበትን ጥበብ ታውቃላችሁ
  • ከሌሎቹ የበለጠ የነብይነት ፀጋ ታውቃላችሁ
  • ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኡመታቸው (በህዝባቸው) ላይ ያላቸውን መብት ታውቃላችሁ

የሰው ልጆች መልዕክተኞች ያስፈልጋቸዋል

ከሃያሉ አሏህ ጥበብ ውስጥ ለሁሉም ኡማ (ህዝብ) ያወረደውን ራዕይ እና መመሪ የሚያብራሩ አስጠንቃቂ ነብያትን ማድረጉ ነው። ይህም በዚች አለም ሆነ በመጭው አለም ህይወት ያለውን ሁኔታ የሚያስተካክሉበት ነው።

ሃያሉ አሏህ እንዲገህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱቱ ፋጢር 24)

“ማንኛውም ህዝብ በውስጡ አስፈራሪ (አስጠንቃቂ) ያላለፈበት የለም።”

በዚህ አለም ሆነ በመጭው አለም ህይወት ወደ ደስታ እና ፈላህ (ደህንነቱ የሚረጋገጥበት) መንገድ የለም በነብያቶች ቢሆን እንጅ። ልክ እንደዚሁ ጥሩ እና መጥፎውን በዝርዝር ለመለየት የሚያስችል መንገድ የለም በእነሱ በኩል ቢሆን እንጅ። የሃያሉ አሏህ ውዴታ የሚገኘውም በእነሱ እጅ ነው።

መልካም ቃላት ፣ መልካም ስራዎች እና ውብ ፀጋዎች የሚገኙት ከአስተምሮታቸው እና ይዘውት ከመጡት ነገር ነው።

ነብዩ ሙሐመድ የአሏህ ነብይ አና  መልዕክተኛ መሆናቸውን ማመን

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ አገልጋይ እና መልዕክተኛ መሆናቸውን ፣ ቀደምትም ሆኖ የመጨረሻው ዘመን ትውልዶች የበላይ መሆናቸውን ፣ የነብያት መደምደሚያ (ማብቂያ) መሆናቸውን ፣ መልዕክቱን እንዳደረሱ ፣ አማናውን (አደራውን) እንደጠበቁ ፣ ኡማውን እንደመከሩ ፣ በአሏህ መንገድ እውነተኛ መታገልን እንደታገሉ እናምናለን።

ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ፈትህ 29)

“ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ ነው።”

በነገሩን ማመን ፣ ያዘዙትን መታዘዝ ፣ የከለከሉትን እና የገሰፁትን መከልከል እና መራቅ ፣ በሱናቸው መሰረት አሏህን ማምለክ እና አርአያነታቸውን መከተል አለብን።

የነብያቶች እና የመልዕክተኞች መደምደሚያ

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የነብያቶች እና የመልዕክተኞች ሁሉ መደምደሚያ ናቸው። ከእሳቸው በኋላ ነብይ የለም።

የእሳቸው መልዕክት ከሳቸው በፊት የነበሩ ሰማያዊ መልዕክቶች መደምደሚያ (ማብቂያ) ነው። እንዲሁም ሃይማኖታቸው የሃይማኖቶች ሁሉ ማብቂያ እውነተኛ ሃይማኖት ነው።

ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አህዛብ 40)

“ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዳችሁም አባት አይደለም። ነገርግን የአሏህ መልዕክተኛ እና የነብያቶች ማብቂያ ነው።”

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 3535)

“የእኔ እና ከእኔ በፊት የነበሩ ነብያት ምሳሌ ልክ ቤቱን አሳምሮ እና አስውቦ እንደ ሰራ ሰው ሲሆን ጠርዝ (ዳር) ላይ ካለች የጡብ ቦታ በቀር አሉ። እናም ሰዎች ተዘዋውረው አይተው እያደነቁ ‹‹ይሄን ጡብ ለምንድን ነው ያደረከው?›› አሉ። እሳቸውም፡ እኔ ጡቡ ነኝ፤ እኔም የነብያቶች ማብቂያ ነኝ›› አሉ።”

የመልዕክተኞች እና የነብያ ፈርጥ

ነብያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የነብያቶች ሁሉ ምርጥ ፣ የፍጡራኑ ሁሉ ምርጥ እና ከሃያሉ አሏህ ዘንድ በደረጃ ከሁሉም የላቁ ናቸው። አሏህ ደረጃቸውን ከፍ አድርጎታል። አሏህ ከፍጡራኖቹ ሁሉ በላጭ ያደረጋቸው ሲሆን ከአሏህ ዘንድ ትልቁን ክብር የያዙ ናቸው። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 113)

“አሏህም በአንተ ላይ መጽሐፉን እና ጥበቡን አወረሰ። የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ። የአሏህ ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው።”

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢንሽራህ 4)

መወሳትህን ለአንተ ከፍ አደረግንልህ።

የአደም ልጆች ሁሉ አለቃ ፣ መቃብራቸው የሚከፈተው የመጀመሪያው ሰው ፣ ምልጃ የሚፈቀድላቸው የመጀመሪያው አማላጅ ፣ ለፍርድ በመቆሚያዋ ቀን የምስጋና ባንድራ በእጃቸው የሚኖር ፣ የሲራጥን መንገድ የሚሻገሩ የመጀመሪያው እና በመጀመሪያ የጀነት በር የሚያንኳኩ እና ወደ እሷም የሚገቡ የመጀመሪያው ሰው እሳቸው ናቸው።

ለአለም እዝነት ናቸው

ሃያሉ አሏህ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የላካቸው ለአለማት እዝነት አድርጎ ነው። መልዕክታቸው ለሁሉም የሰው ልጆች እና ለጅን ዘሮች ነው። መልዕክታቸውም ለሰው ልጅ በሙሉ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንቢያ 107)

“ለአለማት እዝነት አድርገን እንጅ አላክንህም።”

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሰበዕ 28)

ለሰው ልጅ በሙሉ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን እንጅ አላክንህም።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አዕራፍ 158)

“እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለሁላችሁም (የተላኩ) የአሏህ መልዕክተኛ ነኝ በላቸው።”

ሃያሉ አሏህ ለአለማት እዝነት አድርጎ የላካቸው ለሁለቱ የሰው እና የጅን ዘሮች በሙሉ ከሽርክ ፣ ከክህደት እና ከድንቁርና አውጥተው ወደ እውቀት ፣ ኢማን (እምነት) እና ንፁህ ወደ ሆነው የአሃዳዊነት ብርሃን እንዲያሻግሯቸው ነው። በዚህም የአሏህን ምህረት ፣ ውዴታ ማግኘት እና ከቅጣቱ እና ከቁጣው መዳን ይችላሉ።

በእሳቸው ማመን እና መልዕክታቸውን የመከተል ግዴታ

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት ከእሳቸው በፊት የነበሩ መልዕክቶችን ሁሉ ሽሯል። አሏህ ሃይማኖትን ከማንም አይቀበልም ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) የተከተለ ቢሆን እንጅ። እንዲሁም የጀነት ሃሴት (ፍፁም ደስታ) አያገኝም መንገዳቸውን በመከተል ቢሆን እንጅ።

ምክኒያቱም ከነብያቶች ሁሉ በጣም የተከበሩ ፣ ህዝባቸው ከህዝቦች ሁሉ በላጭ የሆኑ እና ሸሪአቸው ከሸሪአዎች (ከህጎች) ሁሉ ፍፁም እና ሙሉ የሆነ ነውና።

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢምራን 85)

“ከእስልምና ውጭ ሌላን ሃይማኖት የፈለገ ሰው ተቀባይነት የለውም። በመጭው አለም ከከሳሪዎች አንዱ ይሆናል።”

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 153)

‹‹የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ይሁንብኝ! በዚህ ኡማ ከአይሁድ ወይም ከክርስቲያን የተላኩበትን ነገር ሰምቶ ሳያምን የሞተ ሰው የለም ከጀሐነም ጓዶች አንዱ እሱ ቢሆን እንጅ ብለዋል።››

ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተአምራት አንዱ መልዕክታቸው ነው

የላቀው እና የተወደሰው አሏህ ነብያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለመልዕክታቸው እና ለነብይነታቸው ምስክር እና ማስረጃ የሚሆኑ አስደናቂ ተአምራትን እና ምልክቶቸፍን ሰጥቷቸዋል። ከእነዚህ ተአምራት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

ቅዱስ ቁርአን

ረሱላችን (ሰ.ዐ.ወ) ከተሰጡት ምልክቶች (አያት) ውስጥ ትልቁ ነፍስን እና አዕምሮን የሚያወራው ቅዱስ ቁርአን ሲሆን እስከ ቂያማ ቀን ድረስ የማይቀየር እና የማያለዋወጥ ቋሚ ምልክት (ተአምር) ነው። በቋንቋው እና በአሰራሩ ፣ በህግጋቱ ፣ በፍርዱ እና በዜናው የምንግዜም ተአምር ነው።

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራዕ 88)

“የሰው ልጆች እና ጅኖች (ጋኒኖች) የዚህን ቁርአን አምሳያ ለማምጣት ቢሰባሰቡ እና ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆኑ እንኳ አምሳያውን አያጡም በላቸው።”

የጨረቃ መከፈል

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ቀመር 1-2)

c”ሰአቲቱ (የትንሳኤዋ ቀን) ተቃረበች ፣ ጨረቃም ተሰነጠቀች ፣ ተአምርንም ቢያዩ ‹ከእምነት› ይዞራሉ፤ ይህማ ዘውታሪ ድግምት ነውም ይላሉ።”ccccx

ይህ የጨረቃ መሰንጠቅ (መከፈል) የተከሰተው በእሳቸው (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ዘመን ሲሆን ቁረይሾች እና ሌሎችም ተመልክተውት ነበር።

በእጃቸው የበነበረውን ምግብ አብዝተዋል

ከእሳቸው ጋር የነበሩ ሰዎች ከምግቡ እና ከፍርፋሪው በልተዋል። ከሰሙራ ቢን ጁንዱብ የመጣው ይሁ ሲሆን እንዲህ አለ፡ ‹‹ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሁነን እያለ አንድ ሳህን ገንፎ ይዘው መጡ። እንዲህ አለ፡ ‹‹እሳቸውም በሉ፤ ሰዎቹም በሉ። የቀትር ሰአት እስኪደርስ ድረስ ሰዎቹ አዘዋወሩት፤ ሁሉም ሰዎችም ይበላሉ ይነሳሉ። እናም ሰዎች ይመጣሉ፤ እረስ በእርስም ይተካካሉ።›› (ሙሰነድ አህመድ 20135)

ስላልታዩ ነገሮች መነገራቸው

ያልታዩ ነገሮች አስመልክቶ የተነገሯቸው ነገሮች ይከሰታሉ። ከተናገሩትም ብዙው ተከስቷል። ከተናገሩትም ነገሮች እስካሁን ድረስ ሲከሰቱ እናያለን።

አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ኡመር ኢብን ኸጧብ (ረ.ዐ) የበድር ሰዎችን ታሪክ አስመልክቶ እንዲህ አለ፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ከጦርነቱ በፊት) ታገይ የበድር ሰዎችን አሳዩን። የአሏህ ፈቃድ ከሆነ እገሌ እና እገሌ የሚሞቱበት ቦታ ይሆናል አሉ። ኡመር ኢብን ኸጧብ እንዲህ አሉ፡ ከእውነት ጋር በላከው (አሏህ) ይሁንብኝ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የጠቆሙላቸውን የመሞቻቸውን ቦታ አልሳቱም።›› (ሙስሊም 2873)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኡመታቸው (በህዝባቸው) ላይ ያላቸው መብት

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በህይወታቸው ላይ ያላቸው መብት ብዙ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል።

1 በነብይነታቸው ማመን

በነብይነታቸው ፣ በመልዕክተኝነታቸው እና መልእክታቸው ከእሳቸው በፊት የነበሩ መልዕክቶችን ሁሉ የሻረ መሆኑን ማመን ነው።

2 ተሰደቁሁ (እውነቱን ነው ማለት)

የተናገሩትን ማመን ፣ ያዘዙትን ነገር መታዘዝ ፣ የከለኩትን መከልከል እና በእሳቸው መንገድ አሏህን መገዛት ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐሽር 7)

“መልዕክተኛው የሰጣችሁን ነገር ያዙ፤ የከለከላችሁንም ነገር ተከልከሉ።”

3 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያመጡትን መቀበል

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዘውት የመጡትን ነገር መቀበል ፣ ሱናቸውን መተግበር እና መመሪያቸውን የአክብሮት እና የውዳሴ ስጦታ ማድረግ በእኛ ላይ ግዴታ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 65)

“በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስኪያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከሚያገኙ እና ፍፁም መታዘዝን እስኪታዘዙ ድረስ አያምኑም።”

4 የእሳቸውን (ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ ከመጣስ መጠንቀቅ

ትዕዛዛቸውን ከመጣስ መጠንቀቅ አለብን። ምክኒያቱም ትዕዛዛቸውን መጣስ ጥመት ፣ መሳሳት እና አሳማሚ ቅጣት የሚያስከትል ነውና። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 63)

“እነዚያ ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።”

5 ውዴታን ከሌላ ሰው በፊት ለእሳቸው ማደረረግ

አንድ ሰው እራሱን ፣ ልጆቹን ፣ ወላጆቹን እና ሌሎች ፍጡራንን ከሚወደው በላይ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ውዴታ ማስቀደም በእሱ ላይ ግዴታ ነው። አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 15)

‹‹አንዳችሁም አላመናችሁም ከወላጆቹ ፣ ከልጆቹ እና ከሌሎች ሰዎች ሁሉ በላይ አብልጦ እስኪወደኝ ድረስ።››

በሌላ ዘገባ ደግሞ ኡመር ኢብን ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! አንቱ ለእኔ ከሁሉም ነገር በላይ ተደዳጅ ነሁ፤ ከነፍሴ (ከእራሴ) በቀር›› አላቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡ ‹‹አይደለም! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ! ከነፍስህ (ከእራስህ) በላይ ለአንተ ተወዳጅ እስክሆን ድረስ ነው›› አሉት። ኡመርም አለ፡ ‹‹በአሏህ ይሁንብኝ አሁን ከነፍሴም በላይ ለእኔ ተወዳጅ ነሁ።›› ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሁኑኑ ኡመር አሉት።›› (ቡኻሪ 6632)

6 መልዕክቱን እንዳስተላለፉ ማመን

መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) መልእክቱን ሙሉ በሙሉ አስተላልፈዋል ፣ አደራቸውን ተወጥተዋል ፣ ህዝባቸውንም መክረዋል ብሎ ማመን ያስፈልጋል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ማኢዳ 3)

“ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ። ፀጋየንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ። ከሃይማኖትም እስልምናን ለእናንተ ወደድኩ።”

ከዚህ በተጨማሪ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦች በትልቅ ስብስቦች ላይ እና ሐጀተል ወዳዕ (የስንብት ሐጅ) በሐጅ ወቅት መልዕክቱን እንዳደረሱ መስክረዋል። በጃቢር ሐዲስ ውስጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ እንዳሉ ተዘግቧል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 1218)

‹‹ስለ እኔ በተጠየቃችሁ ጊዜ፤ ስለ እኔ ምነድን ነው የምትሉት? አሉ። እነሱም (ሶሃቦች) መለሱ፡ ‹‹መልዕክቱን እንዳደረሱ ፣ አደራን እንደመለሱ እና መልካም ምክርን እንደለገሱ እንመሰክራለን። ከዚያም አመልካች ጣታቸውን ቀስረው ወደ ሰማዩ እና ወደ ሰዎቹ አፈራርቀው እየጠቆሙ ሶስት ጊዜ ‹‹አሏህ ሆይ! ምስክሬ ሁን! አሏህ ሆይ! ምስክሬ ሁን!›› አሉ።

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት የሚለው ትምህርት ፈተና 12 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 10 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 12

Bookmark question icon

1 ትክክለኛው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች ስንት ናቸው?

2 / 12

Bookmark question icon

2 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያ ሚስታቸው ማናት?

3 / 12

Bookmark question icon

3 ከነብዩ ሙሐመድ ተአምራቶች ውስጥ የሆነው የትኛው ነው?

4 / 12

Bookmark question icon

4 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጡት የጠቡባቸው ሴቶች የትኞቹ ናቸው?

5 / 12

Bookmark question icon

5 የነብያት እና የመልዕክተኞች ሁሉ ቁንጮ (የበላይ) ማን ነው?

6 / 12

Bookmark question icon

6 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ሐረግ ከ _____ ይመዘዛል።

7 / 12

Bookmark question icon

7 ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት ለማን ነው?

8 / 12

Bookmark question icon

8 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በልጅነታቸው እና በወጣትነታቸው ዘመን _____ ሆነው ሰርተዋል።

9 / 12

Bookmark question icon

9 አንድ ሙስሊም ሰው ከሌሎች ሰዎች ውዴታ ሁሉ ማስቀደም (ማስበለጥ) ያለበት ለማን ነው?

10 / 12

Bookmark question icon

10 ከእስልምና ሃማኖት ውጭ ሌላ ሃይማኖት መከተል የተፈቀደ ነው።

11 / 12

Bookmark question icon

11 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተናገሩትን ማመን ፣ ያዘዙትን መታዘዝ እና የከለከሉትን መከልከል እና መራቅ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

12 / 12

Bookmark question icon

12 የነብያት እና የመልዕክተኞች መደምደሚያ (ማብቂያ) የሆነው ነብይ የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ነብዩ ሙሐመድ

ነብዩ ሙሐመድ

ሙስሊም ሰው ከነብዩ ሙሐመድ ዝርዝር ታሪኮች ጋር እራሱን ማስተዋወቅ አለበት። ያ ሲሆን በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሳሌነታቸውን መከተል ይችላል። ምክኒያቱም የህይወት ታሪካቸው ተጨባጭ የእስልምና እና የህግጋቱ

Read More »
የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

አሏህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት እና ስብዕናዎች ከሁሉ የተለዩ አድርጓቸዋል። ይህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት ልቦች በፍቅራቸው እና በውዳሴያቸው እንዲነጉዱ ያደርጋል። በዚህ ጽሁፉ ውስጥ ከእነዚህ ባህሪያት የተወሰኑትን

Read More »
የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ

የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 5

የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 5 ክፍል አምስት የኡመር ኢብን አል-ኽጧብ (ረ.ዐ) ኢስላምን መቀበል ኡመር (ረ.ዐ) ኢስላምን የተቀበለው ሐምዛ (ረ.ዐ) ኢስላምን ከተቀበለ ከሶስት ቀን መሳሪያ ታጥቆ በከረረ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share