ቁርአን በመልአኩ ጅብሪል አማካኝነት ለመጨረሻው መልዕክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተገለፀ አቻ የሌለው የአሏህ ንግግር ነው። በውስጡ 114 ምዕራፎች ይዟል።
ቅዱስ ቁርአን

ቁርአን በመልአኩ ጅብሪል አማካኝነት ለመጨረሻው መልዕክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተገለፀ አቻ የሌለው የአሏህ ንግግር ነው። በውስጡ 114 ምዕራፎች ይዟል።

የሚጀምረው በሱረቱ ፋቲሃ (የመክፈቻይቱ ምዕራፍ) ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ በሱረቱ ናስ (በሰዎች) ምዕራፍ ነው።

የቁርአን ሌላ መጠሪያ ስሞቹ አል-ፉርቃን (መመዘኛው) ፣ አል ኪታብ (መጽሐፉ) እና አዚክሩ (መልዕክቱ/ውዳሴው) የሚሉት ናቸው።

ኪታብ

ከሙስሊሞች መካከል በላጩ ቁርአን ተምሮ ለሌሎች ያስተማረ ነው።

አንዲትን ፊደል ከእሱ ያነበበ ሰው እንደ አንድ ምንዳ ወይም ሽልማት ይያዝለታል። አንዷ ምንዳ አስር እጥፍ ምንዳ ታስገኘዋለች።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በልቡ ውስጥ ከቁርአን ምንም ነገር የሌለውን ሰው ሲገልፅ ልክ እንደፈረሰና እንደተተወ ፣ ሰው እንደሌለው ቤት ነው ሲሉ ገልፀውታል።

አሏህ ያወረደው ለሙእሚኖች እንደ መመሪያ ፣ ምህረት ፣ መድሃኒት አድርጎ ነው። የነብዩ ሙሐመድ እውነተኛነት የሚያረጋግጥ ተአምር ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራዕ 17፡88)

“በላቸው ሰዎች እና ጅኖች የዚህን ቁርአን አምሳያ ለመፍጠር አንድ ላይ ቢሰባሰቡ ፣ አንዳቸው ለአንዳቸው ቢረዳዱ ቢደጋገፉ እንኳ የእሱን አምሳያ መፍጠር አይችሉም።”

መጽሐፍት

በቀደምት ዘመናት የተገለፁ ቅዱሳን መጽሐፍት ከተጭበረቡና ከተዛቡ ቡኋላ ቁርአን እውነተኛውን የመጀመሪያውን የኢስላም መልዕክት ለማረጋገጥ መጣ።

ቁርአን በውስጣቸው ያለውን እውነቱን በማረጋገጥ እና ውሸቱን በሃሰትነቱ ማረጋገጥ የቆመ ህያው ምስክር ነው።

ምንም እንኳ እነዚህ ቅዱሳን መጽሐፍት አሁንም ቢኖሩም ግን ያሉት በመጀመሪያ ይዘታቸው አይደለም።

ምክኒያቱም የሰው ልጅ ይዘታቸውን በመቀናነስ እና በመጨመር ትክክለኛውን መለኮታዊ መልዕክት በርዘውታልና ነው።

ቅዱስ ቁርአን የጊዜውን ፈተና የሚቋቋም ብቸኛው መለኮታዊ ቅዱስ መጽሐፍ ነው። ምክኒያቱም የሚጠብቀው አሏህ ነውና።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሒጅር 15፡9)

“በእርግጥ! ዚክሩን (ውዳሴውን/ቁርአንን) ያወረድነው እኛ ነን። በእርግጥም! እንጠብቀዋለን።”

አል-ቁርአን

ሱረቱል ፉሲለት 41፡41-42

በእርግጥ! ወደ እሱ በመጣ ጊዜ በዚክሩ (በውዳሴው/በቁርአን) የካዱ ቅጣቱን ይቀበላሉ። በእርግጥ የተከበረ የላቀ መጽሐፍ ነው። ውሸት ከበፊትም ከስተኋላውም ወደ እሱ አይመጣም። ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው።

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

የቁርአን ጥያቄና መልስ (ለጀማሪዎች)

ስለ ቅዱስ ቁርአን ያለዎት እውቀት ምን ያህል ነው? በዚህ ጥያቁና መልስ ላይ ጥሩ ውጤት እንደሚያገኙ እርግጠኛ ነዎት? እንግዲያውስ ፈተናውን ይውሰዱና አሸናፊ ሆነው ያሳዩን፡፡ ሃሳብ አስተያየትዎን ከታች ባለው የሐሳብ መስጫ ቦታ ያሳውቁን!

1 / 9

Bookmark question icon

1 በሱረቱል ካህፍ (የዋሻው ምዕራፍ) ውስጥ ከእንቅልፋሞቹ ጋር በዋሻው ውስጥ እንደነበር የተጠቀሰው እንስሳ የትኛው ነው?

2 / 9

Bookmark question icon

2 ለመጀመሪያ ጊዜ ለነብዩ የወረዱት አንቀጾች ከየትኛው ሱራ (ምዕራፍ) ውስጥ ነበሩ?

3 / 9

Bookmark question icon

3 የነብዩ ኑህ መርከብ (ከጥፋት ውኃ) በኋላ በቁርአን እንደተጠቀሰው ያረፈችበት ቦታ የትኛው ነው?

4 / 9

Bookmark question icon

4 “የቁርአን ልብ” ተብላ የምትጠቀሰው ሱራ የትኛዋ ናት?

5 / 9

Bookmark question icon

5 በቁርአን ውስጥ በነብያት ስም የተሰየሙ ስንት ሱራዎች አሉ?

6 / 9

Bookmark question icon

6 አልኮል መጠጣትን የሚከለክለውን አንቀጽ በየትኛው ሱራ ውስጥ ያገኙታል?

7 / 9

Bookmark question icon

7 በቁርአን ውስጥ በስም የተጠቀሰው ብቸኛው ወር የትኛው ነው?

8 / 9

Bookmark question icon

8 በቁርአን ውስጥ የ30ኛው ጁዝ የመጀመሪያ ሱራ ምንድነው?

9 / 9

Bookmark question icon

9 በአቡ በክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ኸሊፋነት ዘመን፣ የተበታተኑትን የቁርአን አንቀጾች በሙሉ ወደ አንድ የተሟላ መጽሐፍ እንዲያጠናቅር ያዘዙት ማንን ነበር?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ቅዱስ ቁርአን

ቁርአን ሙሉ በሙሉ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በህይወት በነበሩበት ጊዜ የተፃፈ ሲሆን የተፃፈው ሉህ (ብራና) ፣ የዘምባባ ዛፍ ቁርጥራጮች እና አጥንት ላይ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ አስር ሽህ የነብዩ ሶሃባዎች ልክ በተገለፀበት አግባብ ሸምድደውታል። ቁርአን አሁንም በመጀመሪያው ቋንቋ በአረብኛ እየተነበበና በአለም ዙሪያ የሚገኙ ሚልዮን ሰዎች የሚማሩት መጽሐፍ ነው።

በተመዘገበ ታሪክ ውስጥ ይህን አቻ የሌለው እንክብካቤ ያገኘ ሌላ ሐይማኖታዊ መጽሐፍ  የለም።

ቁርአን ፍፁም እንከን የሌለበት በተገለፀበት በአረብኛ ቋንቋ ብቻ ነው።

የቁርአን ትርጉም ስራዎች ፍፁም ያልሆነው ተሳሳች የሰው ልጅ ውጤቶች ናቸው። ስለዚህ የትርጉም ስራዎች የቁርአን ሃተታዎች ብቻ ናቸው።

0%
3
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

ጥያቄና መልስ፡ የቅዱስ ቁርአን መግቢያ

የቅዱስ ቁርአን መግቢያ ፈተና 6 ጥያቄዎችን የያዘ ሲሆን ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 ቅዱስ ቁርአን በመጽሐፍ መልክ የተሰበሰበው ______ የአስተዳደር ዘመን ነበር።

2 / 6

Bookmark question icon

2 የቅዱስ ቁርአን ምዕራፎች ስንት ናቸው?

3 / 6

Bookmark question icon

3 ቁርአን ከሃያሉ አሏህ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የወረደው ______ አማካኝነት ነው።

4 / 6

Bookmark question icon

4 ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጀመሪያ ላይ የተገለጠላቸው ራዕይ በየትኛው ወር ውስጥ ነበር?

5 / 6

Bookmark question icon

5 ከቁርአን መጠሪያ ስሞች ውስጥ የሆነው የትኛው ነው?

6 / 6

Bookmark question icon

6 ሃያሉ አሏህ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የገለጠላቸው መጽሐፍ የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 26%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ጅብሪል ተመልከቱ

Related posts

ቁርአን የደመና እና የዝናብ አፈጣጠርን በተመለከተ ምን ይላል

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- “ነፋሶችንም ለምለም አድርገን ላክን፤ ከሰማይም ውሃን አወረድን፤ ከእርሱም አጠጣናችሁ፤ እናንተም ለእርሱ አከማቾች አይደላችሁም።” (አል-ቁርአን15:22) ዘመናዊ ሳይንስ በነዚህ የቁርአን አንቀፆች

Read More »

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

ፅንስ የሚያልፍባቸውን ደረጃዎች በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው የሚያልፍባቸው ደረጃዎች፡- ከጭቃ ንጥር፡ የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ከጭቃ ተፈጥሯል። ይህ የሚያመለክተው ሰዎች የተለየ ፍጥረት

Read More »

ቁርአን ስለ ከባቢ አየር

ቁርአን ስለ አየር ግፊት ምን ይላል አላህ እንዲህ ይላል፡- ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ሰው ወደ ከባቢ አየር በወጣ ቁጥር መተንፈስ እየከበደው ይሄዳል። ይህም በከባቢ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share