በቁርአን ውስጥ ስለ ውቅያኖሶች የተጠቀሰው ምንድን ነው

Author picture

ቁርአን በባህሮች መካከል ስላለው ግርዶሽ

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል ፉርቃን 25:53

“ሁለቱን ባሕሮች በአንድነት የለቀቀ እሱ ነው፤ አንዱ ጥዑም የሚጣፍጥ ሲሆን ሌላው ጨዋማ የሚመረግግ ነው። በመካከላቸውም ግርዶሽ እና የተከለለን ክልል አድርጓል።”

በባህር ዳርቻ የውሃ መስመሮች ውስጥ ሶስት ዋና ዋና የጨዋማነት ስርዓቶች አሉ፡- የተነባበረ ፣ በከፊል የተቀላቀለ እና ሙሉ በሙሉ የተቀላቀለ።

የውቅያኖሶች ውሃ እርስ በእርሳቸው የማይቀላቀሉበትን እውነታ በቅርቡ በውቅያኖስ ተመራማሪዎች የተገኘ ነው።

ይህ የሆነው “የወለል ውጥረት” ተብሎ በሚጠራው አካላዊ ኃይል ምክንያት ነው። በዚህም የባህር ውሃዎች አይቀላቀሉም።

ይህ የሚከሰተው በውሃዎቻቸው ጥግግት ልዩነት ነው። የወለል ውጥረት ልክ በመካከላቸው ቀጭን ግድግዳ እንዳለ እርስ በእርሳቸው እንዳይዋሃዱ ይከላከላል።

የአማዞን ወንዝ ውሃ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ይፈስሳል። ነገርግን ወደ ውቅያኖሱ 200 ሜትር ከገባ በኋላም ባህሪያቱን እንደያዘ ይዘልቃል።

ቁርአን በባህሮች ውስጥ ስላለው ጨለማ እና ውስጣዊ ሞገዶች

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱ ኑር 24:40

“(የካፊሮች ስራ) በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንዳለ ጨለማ ነው፤ ሞገድ የሚሸፍነው ሲሆን ከላይውም ሌላ ሞገድ ያለበት ከላይውም ደመና ያለበት፤ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ድርብርብ የሆኑ ጨለማዎች ናቸው። እጁን (በውስጡ) ባወጣ ጊዜ ሊያየው እንኳ አይቀርብም። አላህም ብርሃን ያልሰጠው ሰው ለእሱ ምንም ብርሃን የለውም።”

ይህ አንቀጽ በባህር ውስጥ ስለሚገኙ የተለያዩ የጨለማ ደረጃዎች እና ሞገዶች በግልፅ ያስረዳል።

የውቅያኖስ ጥልቀት በጨመረ ቁጥር የብርሃን ጨረሮች እየቀነሱ በመሄዳቸው ጨለማው እየበረታ ይሄዳል።

ከዚህም በላይ በውሃ ውስጥ የሚፈጠሩ ውስጣዊ ሞገዶች ከላይ ከሚታዩት ሞገዶች በተጨማሪ የጨለማውን ሁኔታ ሊያባብሱ ይችላሉ።

ይህ የሚያሳየው የቁርአን ተአምራዊነት ነው፡፡  በምድር እና በሰማያት አላህ ሁሉ ቻይነት ነው።

በውቅያኖስ ውስጥ እጅግ በጣም ጥልቅ በሆነ ቦታ ላይ ብርሃን እንደሌለ ፣ ጨለማ ብቻ እንዳለ በሳይንስ የተረጋገጠ እና በሰፊው የሚታወቅ ነው።

ለዚህ ምክንያቱ የፀሐይ ጨረሮች ወደዚያ ቦታ መድረስ ስለማይችሉ ነው። ምክንያቱም የውቅያኖሶች ጥልቀት ከጥቂት መቶ ሜትሮች እስከ 10994 ሜትር ይደርሳል።

በባህር እና በውቅያኖስ ውስጥ ያለው ጨለማ ከ200 ሜትር እና ከዚያ በታች ባለው ጥልቀት ላይ እንደሚጀምር ተረጋግጧል። በዚህ ጥልቀት ላይ ምንም አይነት ብርሃን የለም።

ከ1000 ሜትር በታች ባለው ጥልቀት ደግሞ በፍጹም ብርሃን ዘልቆ አይገባም። ሆኖም አብዛኛዎቹ የፀሐይ ጨረሮች 100 ሜትር ላይ በውሃው ይዋጣሉ።

ይህ የባህር ክፍል ብሩህ ክፍል በመባል ይታወቃል። ከዚያ በኋላ 1% የፀሐይ ጨረሮች በ150 ሜትር ላይ የሚታዩ ሲሆን በ200 ሜትር ደግሞ 0.01% የሚሆኑት ጨረሮች ብቻ ይታያሉ።

ይህ ሥዕላዊ መግለጫ ብርሃን በጠራ የውቅያኖስ ውሃ ውስጥ ምን ያህል ጥልቀት እንደሚገባ ያሳያል። ቀይ ብርሃን በጠንካራ ስለሚዋጥ በጣም ጥልቀት የሌለው የመግባት ጥልቀት አለው፡፡ ሰማያዊ ብርሃን ደግሞ በጣም ጥልቅ የሆነ የመግባት ጥልቀት አለው። (አፕላይድ ኦፕቲክስ፣ ጥራዝ 20 (177) ስሚዝ፣ አር.ሲ. እና ኬ.ኤስ. ቤከር። 1981። በተጨማሪ ይመልከቱ፡ https://daac.gsfc.nasa.gov/oceancolor/scifocus/oceanColor/oceanblue.shtml )

በከባቢ አየር ውስጥ ያለው የኦዞን ሽፋን አብዛኛዎቹን የአልትራቫዮሌት ጨረሮች ያንፀባርቃል።

ደመናዎች ደግሞ ከእነዚህ ጨረሮች ውስጥ 30% ያህሉን ሲያንፀባርቁ 19%ቱን ደግሞ ሰብስበው ይይዛሉ። ወደ ባህር የሚደርሰው 51% ብቻ ነው።

ከ3% እስከ 30% የሚሆነው የፀሐይ ብርሃን በባህር ወለል ላይ ይንፀባረቃል። ከዚያም ከሰባት የብርሃን ስፔክትረም ቀለሞች ውስጥ ሰማያዊ የሞገድ ርዝመት በስተቀር ሁሉም ማለት ይቻላል በመጀመሪያዎቹ 200 ሜትሮች ውስጥ አንድ በአንድ ይዋጣሉ።

ቁርአን ስለ ውስጣዊ ሞገዶች ምን ይላል

ሳይንቲስቶች በቅርቡ “በተለያየ ጥግግት ባላቸው ንብርብሮች መካከል ባሉ የጥግግት ወሰኖች ላይ የሚከሰቱ” ውስጣዊ ሞገዶች እንዳሉ ደርሰውበታል።

ጥልቅ ውሃዎች ከላይ ካሉት ውሃዎች የበለጠ ጥግግት ስላላቸው ውስጣዊ ሞገዶች የባህርን እና የውቅያኖሶችን ጥልቅ ውሃዎች ይሸፍናሉ።

ውስጣዊ ሞገዶች እንደ ወለል ሞገዶች ይሠራሉ። ልክ እንደ ወለል ሞገዶች ሊሰበሩም ይችላሉ። ውስጣዊ ሞገዶች በሰው ዓይን ሊታዩ አይችሉም።

ነገርግን በተወሰነ ቦታ ላይ ያለውን የሙቀት መጠን ወይም የጨዋማነት ለውጥ በማጥናት ሊታወቁ ይችላሉ።

የተለያየ ጥግግት ባላቸው ሁለት የውሃ ንብርብሮች መካከል የሚፈጠሩ ውስጣዊ ሞገዶች።

አንዱ ጥቅጥቅ ያለ (የታችኛው) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ጥቅጥቅነቱ ያነሰ (የላይኛው) ነው። (ግሮስ፣ ኤም. ግራንት. የውቅያኖስ ጥናት። ኒው ጀርዚ፡ ፕረንቲስ ሆል. 1993. የታተመ)

ውስጣዊ ሞገዶች እና የውቅያኖስ ድብልቅ መለኪያዎች። (የውቅያኖስ ጥናት፣ ክሪስ ጋሬት። በተጨማሪም ይህንን ይመልከቱ፡ http://www.nature.com/nature/journal/v422/n6931/full/422477a.html )

ለምሳሌ፡ የሜዲትራኒያን ባህር ውሃ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ውሃ ጋር ሲነጻጸር ሞቃታማ ፣ ጨዋማ እና ጥቅጥቅነቱ ያነሰ ነው።

የሜዲትራኒያን ውሃ በጅብራለተር ባህረ ሰላጤ ላይ ወደ አትላንቲክ ሲገባ በራሱ ሞቃታማ ፣ ጨዋማ እና ጥቅጥቅነቱ ያነሰ ባህሪያትን ይዞ በ1000 ሜትር አካባቢ ጥልቀት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ወደ አትላንቲክ ይጓዛል።

የሜዲትራኒያን ውሃ በዚህ ጥልቀት ላይ ይረጋጋል። በእነዚህ ባህሮች ውስጥ ትላልቅ ሞገዶች ፣ ጠንካራ ጅረቶች እና ማዕበሎች ቢኖሩም አይቀላቀሉም ወይም ግርዶሹን ጥሰው አያልፉም።

በጥልቅ ውቅያኖስ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና የውሃ ክምችቶች በሙቀት መጠናቸው እና በጨዋማነታቸው ይለያያሉ።

እነዚህ ባህሪያት አንፃራዊ ጥግግታቸውን የሚወስኑ ሲሆን ይህም በተራው የውቅያኖሶችን ጥልቅ የሙቀት-ጨዋማ ዝውውርን ያንቀሳቅሳል።

NADW = የሰሜን አትላንቲክ ጥልቅ ውሃ። AABW = የአንታርክቲክ የታችኛው ውሃ። ከፔንስሎቬንያ የኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ስቲቭ ሆቫን በሰጡት ምስል ላይ ተሻሽሏል።

ይህ መረጃ እኛ በዚህ ዘመን ያወቅነው እነዚህን ክስተቶች ለመለየት በሚያስችለን የላቀ ቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች አማካኝነት ነው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከውቅያኖስ ርቀው በበረሃማ የአየር ንብረት ውስጥ የኖሩ ሲሆን ምንም አይነት ውቅያኖስን ተሻግረው አያውቁም።

ቁርአን ይህንን ክስተት መጥቀሱ የቁርአንን እውነተኝነት ያሳያል።

Related posts

ቁርአን የደመና እና የዝናብ አፈጣጠርን በተመለከተ ምን ይላል

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- “ነፋሶችንም ለምለም አድርገን ላክን፤ ከሰማይም ውሃን አወረድን፤ ከእርሱም አጠጣናችሁ፤ እናንተም ለእርሱ አከማቾች አይደላችሁም።” (አል-ቁርአን15:22) ዘመናዊ ሳይንስ በነዚህ የቁርአን አንቀፆች

Read More »

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

ፅንስ የሚያልፍባቸውን ደረጃዎች በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው የሚያልፍባቸው ደረጃዎች፡- ከጭቃ ንጥር፡ የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ከጭቃ ተፈጥሯል። ይህ የሚያመለክተው ሰዎች የተለየ ፍጥረት

Read More »

ቁርአን ስለ ከባቢ አየር

ቁርአን ስለ አየር ግፊት ምን ይላል አላህ እንዲህ ይላል፡- ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ሰው ወደ ከባቢ አየር በወጣ ቁጥር መተንፈስ እየከበደው ይሄዳል። ይህም በከባቢ

Read More »

ቁርአን ስለ አጽናፈ ዓለም መስፋፋት

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- እነዚህ አንቀጾች የምንኖርበት አጽናፈ ዓለም በህዋ ውስጥ ያለማቋረጥ እየሰፋ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ አጠቃላይ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share