ቁርአን የደመና እና የዝናብ አፈጣጠርን በተመለከተ ምን ይላል

Author picture

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል አዕራፍ 7:57

“እሱም ከአዝነቱ በፊት የምስራች አድርገው ነፋሶችን የሚልክ ነው። ከባድ ደመናዎችን ባነሱ ጊዜ ወደ ሞተች ምድር እንነዳዋለን። በእርሷም ዝናብን እናወርዳለን፤ በእርሷም ከፍራፍሬዎች ሁሉ እናወጣለን። እንደዚሁ ሙታንን እናወጣለን፤ ልትገሰጹ ይከጀላልና።”

የኩሙሎኒምቡስ ደመና። ይህ ፎቶ የተነሳው በናሳ ሳተላይት ነው። የሚታይ እጅ የኩሙለስ ደመናዎችን ወደሚሰበሰቡበት ቦታ እየገፋ እንዳለ ነው።

ደመናውንና ነፋሱን ጨምሮ የከባቢ አየር ምስል።

አላህ እንዲህ ይላል፡- “ነፋሶችንም ለምለም አድርገን ላክን፤ ከሰማይም ውሃን አወረድን፤ ከእርሱም አጠጣናችሁ፤ እናንተም ለእርሱ አከማቾች አይደላችሁም።” (አል-ቁርአን15:22)

ዘመናዊ ሳይንስ በነዚህ የቁርአን አንቀፆች ውስጥ የተጠቀሱትን ሳይንሳዊ ነጥቦች አረጋግጧል።

ነፋሶች በጨው የበለፀጉ የውሃ ቅንጣቶችን ወደ ከባቢ አየር ይሸከማሉ። “ኤሮሶል” የሚባሉት እነዚህ ቅንጣቶች የውሃ ወጥመድ ሆነው ያገለግላሉ፡፡

እናም በራሳቸው የውሃ ትነት ዙሪያ በመሰብሰብ የደመና ጠብታዎችን ይፈጥራሉ።

ደመናዎች በአየር ውስጥ ባሉ የጨው ክሪስታሎች ወይም የአቧራ ቅንጣቶች ዙሪያ ከሚጨመቀው የውሃ ትነት የተሠሩ ናቸው።

በእነዚህ ደመናዎች ውስጥ ያሉ የውሃ ጠብታዎች በጣም ትንሽ (ከ 0.01 እስከ 0.02 ሚሜ የሆነ ዲያሜትር ያላቸው) ስለሆኑ ደመናዎቹ በአየር ላይ ተንጠልጥለው በሰማይ ላይ ይሰራጫሉ።1

ስለዚህ ሰማዩ በደመና የተሸፈነ ነው። በጨው ክሪስታሎች እና በአቧራ ቅንጣቶች ዙሪያ ያሉት የውሃ ቅንጣቶች እየወፈሩ የዝናብ ጠብታዎችን ይፈጥራሉ፤ ስለዚህ ከአየር የበለጠ ክብደት ያላቸው ጠብታዎች ደመናውን ትተው ወደ መሬት መውረድ ይጀምራሉ።

አሏህ እንዲህ ይላል:-

አል-ቁርአን

ሱረቱ ኑር 24:43

“አላህ ደመናን የሚነዳ መሆኑን አላየህምን ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፡፡ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ሆኖ ታየዋለህ፡፡ ከሰማይም (ከደመና) በውስጧ ካሉት ጋራዎች በረዶን ያወርዳል፡፡ በእሱም የሚሻውን ሰው (በጉዳት) ይነካል፡፡ ከሚሻውም ሰው ላይ ይመልሰዋል፡፡ የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል፡፡”

የዝናብ ደመናዎች በተወሰኑ ስርአቶች እና ደረጃዎች መሰረት ይፈጠራሉ፤ ቅርጽም ይይዛሉ።

የኩሙሎኒምቡስ (አንድ አይነት የዝናብ ደመና) የአፈጣጠር ደረጃዎች  የሚከተሉት ናቸው፡-

1ኛ ደረጃ፡ በነፋስ መነዳት፡ ደመናዎች በነፋስ ይወሰዳሉ፣ ማለትም በነፋስ ይነዳሉ።

2ኛ ደረጃ፡ መቀላቀል፡ ከዚያም በነፋስ የሚነዱ ትናንሽ ደመናዎች (የኩሙለስ ደመናዎች) አንድ ላይ በመቀላቀል ትልቅ ደመና ይፈጥራሉ።

3ኛ ደረጃ፡ መደራረብ፡ ትናንሽ ደመናዎች አንድ ላይ ሲቀላቀሉ በትልቁ ደመና ውስጥ ያለው ወደ ላይ የሚወጣ የአየር ፍሰት ይጨምራል።

በደመናው መሃል አካባቢ ያለው ወደ ላይ የሚወጣ የአየር ፍሰት በጠርዙ አካባቢ ካለው የበለጠ ጠንካራ ነው።

ይህ ወደ ላይ የሚወጣ የአየር ፍሰት የደመናውን አካል በአቀባዊ እንዲያድግ ያደርገዋል ስለዚህም ደመናው ይደራረባል።

ይህ ቀጥ ያለ እድገት የደመናውን አካል ወደ ቀዝቃዛ ከባቢአየር እንዲዘረጋ ያደርገዋል። እዚያም የውሃ ጠብታዎች እና በረዶዎች ተፈጥረው እየበዙ ይሄዳሉ።

እነዚህ የውሃ ጠብታዎች እና በረዶዎች ወደ ላይ የሚወጣውን የአየር ፍሰት ለመቋቋም በጣም ከባድ በሚሆን ጊዜ ከደመናው እንደ ዝናብ ፣ በረዶ ወዘተ መውረድ ይጀምራል።

በደመና ውስጥ እጅግ የቀዘቀዙ የውሃ ጠብታዎች እና የበረዶ ክሪስታሎች ባሉበት አካባቢ በረዶ በሚወርድበት ጊዜ ደመናው በኤሌክትሪክ ይሞላል።

የውሃ ጠብታዎች ከበረዶ ድንጋይ ጋር ሲጋጩ ወዲያውኑ ይቀዘቅዛሉ፤ ሙቀትንም ይለቃሉ። ይህ የበረዶውን ድንጋይ ገጽታ በዙሪያው ካሉት የበረዶ ክሪስታሎች የበለጠ እንዲሞቅ ያደርገዋል።

የበረዶው ድንጋይ ከበረዶ ክሪስታል ጋር በሚገናኝበት ጊዜ አንድ አስፈላጊ ክስተት ይከሰታል። ኤሌክትሮኖች ከቀዝቃዛው ነገር ወደ ሞቃታማው ነገር ይፈስሳሉ።

ስለዚህ የበረዶው ድንጋይ አሉታዊ ሃይል ይይዛል። እጅግ የቀዘቀዙ የውሃ ጠብታዎች ከበረዶ ድንጋይ ጋር ሲገናኙ እና አዎንታዊ ኃይል ያላቸው ትናንሽ የበረዶ ስብርባሪዎች ሲሰበሩ ተመሳሳይ ውጤት ይከሰታል።

እነዚህ ቀላል አዎንታዊ ሃይል ያላቸው ቅንጣቶች ከዚያም ወደ ላይ በሚወጣው የአየር ፍሰት ወደ ደመናው የላይኛው ክፍል ይወሰዳሉ። በረዶው ወደ ደመናው የታችኛው ክፍል ይወርዳል።

በዚህም ምክንያት የደመናው የታችኛው ክፍል አሉታዊ ኃይል ይይዛል። እነዚህ አሉታዊ ሃይሎች እንደ መብረቅ ይለቀቃሉ።

ከዚህ በመነሳት በረዶ መብረቅን ለመፍጠር ዋናው ምክንያት እንደሆነ እንረዳለን።

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱ ረዕድ 13:13

“ነጎድጓድም አሏህን በማመስገን ያወድሳል፤ መላእክትም ከእሱ ፍራቻ የተነሳ (ያወድሳሉ)። መብረቅንም ይልካል፤ እነሱም (ከሐዲዎች) በአላህ ይከራከራሉ፤ በእሱም የሚሻውን ሰው ይመታል።  እሱም በመያዝ  የበረታ ነው።”

  1. ተመልከት፡ ታርቡክ፣ ኤድዋርድ ጄ.፣ እና ሉተንስ፣ ፍሬደሪክ ጄ. (1994)። የሳይንስ ምድር። ኒው ጀርሲ፡ ፕሪንቲስ ሆል። በተጨማሪ ይመልከቱ፡ ዋይትማን፣ ዴቪድ ሲ. (2000)። የተራራ የአየር ሁኔታ ጥናት። ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ። ↩︎

Related posts

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

ፅንስ የሚያልፍባቸውን ደረጃዎች በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው የሚያልፍባቸው ደረጃዎች፡- ከጭቃ ንጥር፡ የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ከጭቃ ተፈጥሯል። ይህ የሚያመለክተው ሰዎች የተለየ ፍጥረት

Read More »

ቁርአን ስለ ከባቢ አየር

ቁርአን ስለ አየር ግፊት ምን ይላል አላህ እንዲህ ይላል፡- ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ሰው ወደ ከባቢ አየር በወጣ ቁጥር መተንፈስ እየከበደው ይሄዳል። ይህም በከባቢ

Read More »

ቁርአን ስለ አጽናፈ ዓለም መስፋፋት

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- እነዚህ አንቀጾች የምንኖርበት አጽናፈ ዓለም በህዋ ውስጥ ያለማቋረጥ እየሰፋ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ አጠቃላይ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share