ቁርአን ስለ ከባቢ አየር

Author picture

ቁርአን ስለ አየር ግፊት ምን ይላል

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል አንዐም 6:125

“አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለኢስላም ይከፍትለታል፡፡ ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል፡፡ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡”

ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ሰው ወደ ከባቢ አየር በወጣ ቁጥር መተንፈስ እየከበደው ይሄዳል። ይህም በከባቢ አየር ግፊት መቀነስና በኦክስጅን መጠን ማነስ ምክንያት ነው።

ይህ ጉዳይ አንድ ሰው ወደ ሰማይ ካልወጣ በስተቀር በምንም መንገድ ሊረጋገጥ አይችልም!

ይህ እውነታ የተገኘው ሰዎች መብረርን እና ወደ ከፍታ ቦታዎች መድረስ  ከተማሩ በኋላ ነው።

አንድ ሰው ከባህር ወለል ስምንት ኪሎ ሜትር ከፍታ በላይ ወደ ሰማይ ሲወጣ በቂ ኦክስጅን ባለመኖሩና በከባቢ አየር ግፊት ዝቅተኛነት ምክንያት የመተንፈስ ችግር ያጋጥመዋል።

በዚህ ምክኒያት በተደጋጋሚ የሚከሰት ችግር ‹‹ሃይፖክሲያ›› ሲሆን ይህም በሰውነት ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ማነስ ነው።

ሌላው ሰዎችን ሊያጋጥም የሚችለው ችግር ‹‹ዲስባሪዝም›› ሲሆን ይህም እጅግ በጣም ዝቅተኛ ወይም በፍጥነት በሚለዋወጥ የከባቢ አየር ግፊት መጋለጥ ምክንያት የሚከሰቱ የተለያዩ ምልክቶች ስብስብ ነው።

እነዚህ ሁለት ችግሮች መደበኛ የሰውነት ተግባራትን ያውካሉ።

ስለዚህ በከፍታ ቦታዎች ላይ የመተንፈስ ችግር በቀላሉ ሰውነትን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።

ቁርአን ስለ ጨለማ እና ስለ ከባቢ አየር የላይኛው ክፍል

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል ሒጅር 15:14-15

“ከሰማይም በር ብንከፍትላቸውና በእሱ ላይ መውጣትን ቢቀጥሉ እንኳ ‘ዓይኖቻችን በእርግጥም ደንዝዘዋል። ይልቁንም እኛ የተደገመብን ሕዝቦች ነን!’ ይሉ ነበር።”

ይህ ምሳሌ አስደናቂ ነው ምክንያቱም ሰዎች ቀደም ሲል የማያውቁትንና በስልሳዎቹ የጠፈር ምርምር ዘመን ብቻ የተገኘን ዓለም አቀፋዊ እውነታን ያቀርባል።

መላው ዩኒቨርስ በጨለማ ተሸፍኗል። በምድር ላይ የሚታየው ብርሃን በሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ውስጥ ብቻ ይታያል፡፡

ከዚህ ባሻገር የውሃ ትነት እና የአቧራ ቅንጣቶች እምብዛም ስለሌሉ በሁሉም አቅጣጫ ጨለማ ይታያል።

ይህ የፀሐይ ግርዶሽ ወቅት ላይ የተነሳ ፎቶ ነው፤ ይህም አጽናፈ ሰማይ በጨለማ የተሸፈነ መሆኑን ያረጋግጣል።   

አላህ ከማንኛውም ጉድለት የራቀ ነው። ይህንን እውነታ ያሳወቀን እሱ ነው።

ቁርአን ስለ አቶም

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱ ዩኑስ 10:61

 “… ከጌታህም በምድርም ሆነ በሰማይ የአቶም ክብደት ያህል፤ ከዚህም የሚያንስም የሚበልጥም ምንም አይርቅም እሱ በግልጽ መዝገብ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጅ።”

በዚህ ውብ አንቀጽ በዩኒቨርስ ውስጥ ከአላህ ምንም ነገር እንደማይሰወር ያስረዳናል፤ ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም።

አቶም በዩኒቨርስ ውስጥ ትንሹ አካል እንደሆነ ይታመን ነበር።

ከፀሐይ በተቃራኒ ያለው የቀን ንብርብር በሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ውፍረት ቀጭን መሆኑን ያሳያል። የተቀረው ምድር ሙሉ በሙሉ በጨለማ ውስጥ ይታያል።   

አቶም ከተሰነጠቀ በኋላ ፕሮቶን የሚባሉ አዎንታዊ የኤሌክትሪክ ባህሪ እና ኤሌክትሮን የሚባሉ አሉታዊ የኤሌክትሪክ ባህሪ ያላቸው ትናንሽ አካላት ተገኝተዋል።

እ.ኤ.አ. በ1939 በበርሊን ዩኒቨርሲቲ የነበሩ ጀርመናዊ ምሁራን ሃን እና ስትራስማን የዩራኒየም አቶምን ሰነጠቁ።

በቀጣይ ምርምር እንደ ኳርክ ያሉ በጣም ትናንሽ ቅንጣቶች እንኳን ተገኝተዋል።

ዘመናዊ ሳይንስ በሕይወት በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ የቴክኒክ  እና ሳይንሳዊ እድገት ላይ ደርሷል። ወደፊትም ተጨማሪ እድገት ይጠበቃል።

ይህ ሂደት እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቀጥላል። የሰው ልጅ በእውቀት ዘርፎች የሚያደርገው የጋራ ጥረት የአላህን እውቀትና ችሎታ ፈጽሞ ሊመጥን ወይም ሊቀርብ እንኳን አይችልም።

አሏህ እንዲህ ይላል:

አል-ቁርአን

ሱረቱ አል-ኢስራዕ 17:85

“ከሩሕም ይጠይቁሃል፡፡ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው ከእውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡”

የአላህ እውቀትና ችሎታ ወሰን የለውም፤ የሚወዳደርም የለም። አላህ በዚህ የቁርአን አንቀጽ የአእምሯችንን አቅም  በአላህ እውቀትና በእኛ እውቀት ያለውን እጅግ ትልቅ ልዩነት እንድናውቅና እንድንገነዘብ ቀላል ማብራሪያን አስቀምጦልናል። ልቅና ለአላህ  ይገባው!

Related posts

ቁርአን የደመና እና የዝናብ አፈጣጠርን በተመለከተ ምን ይላል

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- “ነፋሶችንም ለምለም አድርገን ላክን፤ ከሰማይም ውሃን አወረድን፤ ከእርሱም አጠጣናችሁ፤ እናንተም ለእርሱ አከማቾች አይደላችሁም።” (አል-ቁርአን15:22) ዘመናዊ ሳይንስ በነዚህ የቁርአን አንቀፆች

Read More »

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

ፅንስ የሚያልፍባቸውን ደረጃዎች በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው የሚያልፍባቸው ደረጃዎች፡- ከጭቃ ንጥር፡ የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ከጭቃ ተፈጥሯል። ይህ የሚያመለክተው ሰዎች የተለየ ፍጥረት

Read More »

ቁርአን ስለ አጽናፈ ዓለም መስፋፋት

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- እነዚህ አንቀጾች የምንኖርበት አጽናፈ ዓለም በህዋ ውስጥ ያለማቋረጥ እየሰፋ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ አጠቃላይ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share