ሁሉም ነገር እንዲጠፋ አሏህ የሚያዝበት ቀን የውመል ቂያማ ይባላል። መልአኩ ኢስራፊል (ዐ.ሰ) ቀንዱን እንዲነፋ ያዘዋል። መጀመሪያ ላይ እንደነፋም የሰማያትና የምድር ነዋሪዎች ሁሉ ይሞታሉ፤ አሏህ የሻለት ሲቀር።
የውመል ቂያማ ወይም የትንሳኤ ቀን

ሁሉም ነገር እንዲጠፋ አሏህ የሚያዝበት ቀን የውመል ቂያማ ወይም የትንሳኤ ቀን ይባላል። መልአኩ ኢስራፊል (ዐ.ሰ) ቀንዱን እንዲነፋ ያዘዋል።

መጀመሪያ ላይ እንደነፋም የሰማያትና የምድር ነዋሪዎች ሁሉ ይሞታሉ፤ አሏህ የሻለት ሲቀር።

ለሁለተኛ ጊዜ ኢስራፊል ቀንዱን እንዲነፋ አሏህ ባዘዘው ጊዜ በሰማያትም በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ወደዛች አስፈሪ እና አስደንጋጭ ቀን ይቀሰቀሳሉ። የሰው ልጅ ከአለማት ጌታ ፊት ለፍርድ ይቀርባል።

በዚያን ቀን ሰዎች በጣም አስደንጋጭ ክስተቶችን ይመለከታሉ። በዚያን ቀን

አል-ቁርአን

(ሱረቱ አበሰ 80፡34-37)

ሰው ወንድሙ ፣ ከእናት ከአባቱ እና ከሚስቱ እና ከልጆቹ ይሸሻል። ያን ቀን ሁሉም ሰው ለሌሎች ግድየለሽ ይሆናል።

የውመል ቂያማ ማለት የትንሳኤ ቀን ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢንፊጧር 82፡1-5)

ሰማዩ በተሰነጠቀ ጊዜ፤ ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤ ባህሮችም በገነፈሉ ጊዜ፤ መቃብሮችም በተገላበጡና በተነሱ ጊዜ፤ ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀመጠችውን እና ያቆየችውን (የሸሸገችውን) ታውቃለች።

በዚያን ቀን

አል-ቁርአን

(ሱረቱል መአሪጅ 70፡8-14)

ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትሆንበት ቀን፤ ተራራዎች በተለያዩ ቀለማት እንደተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበነው) በሚሆንበት ቀን፤ ዘመድ ዘመዱን በማይጠቅምበት ቀን፤ እርስ በእርሳቸው ይተያያሉ። ሙጅሪሙ (በዳዩ አመፀኛው) ከዚያ ቀን ስቃይ (ለእራሱ ወንጀል) ልጁን ፣ ሚስቱን ፣ ወንድሙን ፣ በምታስጠጋው ጎሳው ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል። በምድር ያለው ሁሉ (ቤዛ ቢሆነው) ቢያድነው ይመኛል።

የትንሳኤ ቀን ወይም የውመል ቂያማ ብዙ ስሞች አሉት። የውሙዲን (የፍርዱ ቀን) ፣ የውሙል ፈስል (የውሳኔው ቀን) ፣ የውሙል ሂሳብ (የሂሳቧ ቀን) ፣ አል-ሐቃ (እርግጠኛዋ እውነታዋ) ፣ አልጋሽያ  (መንፈስን ስሜትን የምትንጠዋ/የምታንቀጠቅጠዋ) ፣ የውሙል አኺራ (የመጨረሻው ቀን) ፣ አል-ዋቂአ (የማይቀረው ክስተት) እና አሳአ (ሰአቷ) የሚሉት ናቸው።

ያን ቀን ሰዎች እርቃናቸውን ፣ በባዶ እግራቸው እና ያልተገረዙ ሆነው ይቀሰቀሳሉ። ፀሐይ ወደ ሰው ልጆች ጭንቅላት (ራስ) ትቀርባለች። ላበታቸው ብቻ ያሸንፋቸዋል።

የላበታቸው ጥልቀት በዚህ አለም ህይወት ይሰሩት የነበረው መጥፎ ስራ ውጤት ነው። ነገርግን በዚህ ቀን ሰባት አይነት ሰዎች በአሏህ ዙፋን ጥላ ስር ይሆናሉ።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)

“ፍትሃዊ መሪ ፣ አሏህን በመገዛት ያደገ ወጣት ፣ ልቡ (ቀልቡ) መስጅድ ጋር የተያያዘ ፣ ለአሏህ ብለው የሚዋደዱ ፣ ሲገናኙም ሲለያዩም በአሏህ መንገድ ላይ የሆነ ፣ ጥሩ አቋም ያላት ቆንጆ ሴት እንባልግ ባለችው ጊዜ ‹አሏህን እፈራለሁ› ያለ ሰው ፣ ቀኝ እጁ የሰጠውን ግራ እጁ እስከማያውቅ ድረስ ደብቆ ሶደቃ የሚሰጥ ሰው ፣ ገለል ብሎ (ብቻውን ሆኖ አሏህን የሚያስታውስ እና ከአይኖቹ እንባ የሚረግፍ።”

በዚያን ቀን ሰዎች የስራዎቻቸውን መዝገብ ይቀበላሉ። መልካም የአሏህ ባሮች የስራቸውን መዝገብ በቀኝ እጃቸው ይቀበላሉ።

በሃሴት በደስታ ያነቡታል። መጥፎዎች እና በዳዮች ደግሞ በግራ እጃቸው እና በጀርባቸው ይቀበላሉ።

አል-ሚዛን (የስራዎች ሚዛን) ይዘጋጃል፤ ሁሉም ነገር ይለካል። ማንም አይበደልም።

የትንሳኤ ቀን አሏህ ፍጡራኖቹን ፍፁም በሆነ ፍትህ ይዳኛል። ዳኛው እሱ ብቻ ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ጋፊር 40፡17)

ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ትመነዳለች(ትሸለማለች)። ዛሬ በደል የለም። በእርግጥ አሏህ ምርመራው ፈጣን ነው።

በምድራዊ ህይወት ጌታዋን የፈራች እና በጎ ስራ የሰራች ነፍስ አጥናፍ ወሰን በሌለው የአሏህ እዝነት ጀነት ትገባለች።

የትንሳኤ ቀን ካፊሮች እና መጥፎ በደለኞች ደግሞ ወሰን በሌለው የአሏህ ፍትህ ወደ ጀሐነም እሳት ይወረወራሉ።

ሲራጥ ፣ አላመቱ ሰአ አል-ኩብራ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share