የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሙጃደላ 58:11)
“አላህ ከእናንተ እነዚያ ያመኑትን እና እነዚያ እውቀት የተሰጡትን በደረጃ ከፍ ያደርጋል።”
እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት የሚወስድ መንገድ እንደሆነ ይቆጠራል። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
“እውቀትን በመፈለግ መንገድ የጀመረ ሰው አላህ ወደ ጀነት የሚያደርሰውን መንገድ ለእሱ ያገራለታል።” (አቡ ዳውድ)

እውቀትን መደበቅ ክልክል ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው እውቀትን መፈለግ ግዴታው ነውና። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
“እውቀትን የደበቀ ሰው በትንሳኤው ቀን በእሳት ልጓም ይለጎማል።” (ኢብን ሒባን)
እስልምና ለዑለሞች (ለእውቀት ባለቤቶች) ከፍተኛ ክብር ይሰጣል፡፡ እንዲሁም የሚገባቸውን ክብር እንዲያገኙ ይጠይቃል። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
“ታላቆቹን የማያከብር ፣ ለታናሹ የማያዝን ፣ ዑለሞች (ሊቃውንት) የሚገባቸውን መብት የማይሰጥ ከኔ ተከታዮች አይደለም።” (አህመድ)
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በንግግራቸው ስለ ኡለሞች ደረጃ እንዲህ ሲሉ አሳውቀውናል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቲርሚዚ)
“…የሰማያትና የምድር ነዋሪዎች እንዲሁም በጥልቅ ውቅያኖሶች ውስጥ ያሉ ዓሳዎች እንኳ [ለዑለሞች] ምህረትን ይለምናሉ። ዑለማዎች በምዕመናን ላይ ያላቸው በላጭነት ልክ ሙሉ ጨረቃ ከሌሎች ከዋክብት ጋር ያለው የበላይነት ነው። ዑለማዎች የነቢያት ወራሾች ናቸው፤ እነሱ የሚያወርሱት ብር ወይም ወርቅ ሳይሆን እውቀት ብቻ ነው። እሱን ያገኘ ሰው በእርግጥ የተትረፈረፈውን ክፍል አግኝቷል።”


Share