እስልምና ተከታዮቹ ለሰዎች የሚገባቸውን መብቶች እንዲሰጡ አዟል፡፡ ወላጆች ፣ ባለትዳሮች ፣ ልጆች ፣ ጎረቤቶች ወ.ዘ.ተ በዚህ አለም ውስጥ ባላቸው ልዩ ሚና መሰረት የተወሰኑ መብቶች አሏቸው፡፡
በዚህም መሰረት በሙስሊም ማህበረሰብ ፣ በግለሰቦች መካከል የጋራ ትስስር እና ጥንካሬ ሊመሰረት ይችላል፡፡
ይህ ደግሞ ፍቅር እና አንድነት እንዲስፋፋ ሲያደርግ ማህበረሰቡን ከመበታተን እና ከመፈራረስ ይታደጋል፡፡ አሏህ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡36)
“አሏህን ተገዙ፡፡ በእሱም ላይ ምንም ነገር አታጋሩ፡፡ በወላጆች እና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም ፣ በየቲሞችም ፣ በሚስኪኖችም ፣ በቅርብ ጎረቤት ፣ በሩቅ ጎረቤትም ፣ በመንገደኛም ፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው (ባሮች) ላይ መልካም ነገር አድርጉ፡፡ አሏህ ኩራተኛ እና ጉረኛን ሰው አይወድም፡፡”

“አላህ በራሳቸው የሚመኩትንና ጉረኞችን አይወድም።”
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
‹‹ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ፡፡ እናም በእያንዳንዳችሁ ጥበቃ ስር ላለው ነገር ተጠያቂ ናችሁ፡፡ ገዥ የተገዥዎች ጠባቂ ነው፤ ለእሰኑም ተጠያቂ ነው፡፡ ባል የቤተሰቡ ጠባቂ ነው፤ በእነሱም ላይ ተጠያቂ ነው፡፡ ሴት የባሏ ቤት ጠባቂ ናት፤ ለእሱም ተጠያቂ ናት፡፡ አገልጋይ የጌታው ንብረት ጠባቂ ነው፤ ለእሱም ተጠያቂ ነው፡፡››
እንዲሁም ሰዎች የሚተላለፉባቸው መንገዶች ሊሟላላቸው የሚገቡ መብቶች አሏቸው፡፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
‹‹በመተላለፊያ መንገዶች ላይ ከመቀመጥ ተጠንቀቁ፤ ራቁም አሉ፡፡ እነሱም፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! የምንሰባሰብበት እና የምንነጋገርበት ሌላ ቦታ የለንም›› አሉ፡፡ እሳቸውም እንዲህ አሉ፡ ‹‹ይህን ማድረግ የግድ ከሆነ የመንገዶችን መብት ስጡ፡፡›› እነሱም፡ ‹‹የመንገዶች መብቶች ምንድን ናቸው? አሉ፡፡ እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡ ‹‹እይታን ዝቅ ማድረግ (ወደ ተቃራኒ ፆታ አለማየት) ፣ ሌሎችን አለመጉዳት ፣ ሰላምታን መመለስ ፣ በመልካም ማዘዝ እና ከመጥፎ ነገር መከልከል ነው፡፡›
እንስሳትም እንኳ መብት አላቸው፡፡ ለእነሱ ማዘን እና ርህራሄ ማሳየት ፣ እነሱን በአግባቡ መያዝ የሰውን ሃጢያት ምህረት እንዲያገኝ ምክኒያት ይሆናሉ፡፡
የአሏህ መልዕክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
‹‹አንድ ሰው በሆነ ጉዳይ ላይ እያለ በጣም ውሃ ተጠማ፡፡ (የውሃ) ጉድጓድ አገኘ እና ወደ ውስጥ ወርዶ ጠጣ፡፡ (ሲወጣም) አንድ ውሻ ጥማቱ በርትቶበት (ውሃ በመፈለግ) እያለከለከ አፈር ሲልስ አየ፡፡ ሰውየውም: ይህ ውሻ እንደ እኔው ተጠምቷል አለ፡፡ ሆኖም (እንደገና ወደ ጉድጓዱ ወርዶ ጫማውን በውሃ ሞልቶ ውሻውን አጠጣው፡፡ (በዚህ ምክኒያት) አሏህ ሃጢያቶቹን በመማር ዋጋውን ከፈለው፡፡›› እነሱም ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ለእንስሳት በምናደርገው ደግነትም እንኳ እንሸለማለን አሉ፡፡ እሳቸውም ‹‹አዎ በእርግጥ! ለእያንዳንዱ ፍጡር የሚደረግ ደግነት ሁሉ ምንዳ አለው፡፡››

እስልምና እንስሳትን በጭካኔ መያዝን፣ ለምሳሌ ምግብ እና መጠጥ ሳይሰጧቸው ማሰርን ወይም ማሰቃየትን ወደ እሳት ለመግባት ምክንያት አድርጎታል።
የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“አንዲት ሴት አንድን ድመት በማሰሯና ባለመመገቧ፣ የምድርን ትላትሎች እንኳ እንዳትበላ ባለመፍቀዷ ምክንያት ወደ እሳት ገባች።”
ይህ እስልምና ለእንስሳት የሚያሳየው ርኅራኄ ከሆነ አላህ ከሌሎች ፍጥረታት ሁሉ በላይ ላላቃቸው እና ላከበራቸው ለሰው ልጆች ምን ያህል የበለጠ ርኅራኄ ሊኖረን እንደሚገባ ያሳያል?


Share