እስልምና ምንድን ነው?

Author picture
እስልምና ማለት በአላህን አንድነት (አሃዳዊነት) ማመን ፣ ለእርሱ መታዘዝ እና መገዛት ፣ በእሱ ላይ አለማጋራት ፣ ለእሱ ተቀናቃኝ ወይም ባላንጣ አለማበጀት ነው። እስልምና ቀለል ያለ ገር ሃይማኖት ነው።

እስልምና ማለት በአላህን አንድነት (አሃዳዊነት) ማመን ፣ ለእርሱ መታዘዝ እና መገዛት ፣ በእሱ ላይ አለማጋራት ፣ ለእሱ ተቀናቃኝ ወይም ባላንጣ አለማበጀት ነው። እስልምና ቀለል ያለ ገር ሃይማኖት ነው።

አሏህ እንዲህ ይላል:-

“አላህ በእናንተ ላይ ገርን (ነገር) ይሻል፡፡ ለእናንተ ችግርን አይሻም፡፡”

(አል-ቁርአን 2:185)

እስልምና መንፈሳዊ እርካታ እና የልብ ሰላም የሚያገኝበት ሃይማኖት ነው። አላህ እንዲህ ይላል:

“እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረጋጉ ናቸው፡፡ በእርግጥ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ፡፡”

(አል-ቁርአን 13:28)

እስልምና የእዝነት እና የምህረት ሃይማኖት ነው፡፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

“ሁሉን መሃሪ የሆነው ለሚያዝኑት ያዝንላቸዋል፡፡ በምድር ላይ ላሉት እዘኑ፤ ከሰማያት በላይ ያለው ያዝንላችኋልና፡፡” (ትርሚዚ)

የእስልምና ሃይማኖት ለራስ የወደዱትን ለሌሎች የመውደድ ሃይማኖት ነው፡፡

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹አሏህ ዘንድ ከሰዎች ይበልጥ ተወዳጁ ለሌሎች ሰዎች ጠቃሚ የሆነው ነው፡፡›› (ጦበራኒ)

እስልምና ግራ የሚያጋባ ወይም የሚያሻማ ነገር የሌለበት ሃይማኖት ነው፡፡ አሏህ እንዲህ አለ፡

“ከአንተም በፊት ወደ እነሱ ወህይ (ራዕይ) የምናወርድላቸው ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁ ብትሆኑ የእወቀት ባለቤቶችን ጠይቁ፡፡”

(አል-ቁርአን 16፡43)

እስልምና የሰው ልጆች ሁሉ ሃይማኖት ነው፡፡ በመካከላቸውም ልዩነት አያደርግም፤ አሏህን በመፍራታቸው ቢሆን እንጅ፡፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

“ሰዎች ልክ እንደ ማበጠሪያ ጥርስ እኩለ፤ ናቸው፡፡ አንድ አረብ አረብ ባልሆነው ላይ በላጭነት የለውም አሏህን በመፍራት ቢሆን እንጅ፡፡”

የእስልምና ጥሪም ለሰው ዘር በሙሉ እንጅ ለተወሰነ ዘር ወይም ህዝቦች አይደለም፡፡ አሏህ እንዲህ ይላል፡

“ለሰዎች ሁሉ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጅ አላክንህም፡፡ አብዛሃኛዎቹ ሰዎች ግን አያውቁም፡፡”

(አል-ቁርአን 34፡28)

እስልምና ያለፉ ሃጢያቶችን ሁሉ ይቅር ሚል ሃይማኖት ነው፡፡

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ “እስልምና ከእሱ በፊት(ከእስልምና) በፊት የተፈፀመውን ሃጢያቶች ሁሉ ይቅር ይላል፡፡” (ሙስሊም)

የእስልምና ሃይማኖት የተሟላ እና ፍፁም የሆነ ሃይማኖት ሲሆን ቀደም ብለው የተገለጡ ራዕዮችን ሁሉ ሽሯል፡፡አስልምና የመጨረሻው ሃይማኖት ነው፡፡ አሏህ እንዲህ ይላል፡

“ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፡፡   ፀጋየንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ፡፡ ከሃይማኖትም አስልምናን ለእናንተ ወደድኩ፡፡”

(አል-ቁርአን 5፡3)

እስልምና የአምልኮ ተግባራት አሉት፡፡ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቸቹ ቃላዊ ፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ የአምልኮ ተግባራት ናቸው፡፡

እነዚህ የአምልኮ ተግባራት የአንድን ሰው ስነ-ምግባር (ባህሪ) በማስተካከል ፣ ነፍስን በማጥራት ፣ እራስን በመቀየርእና የሙስሊሙን ማህበረሰብ አንድነት በመጠበቅ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡

ስለ እስልምና ምን ይላሉ?

ሞንትጎምሪ ‹‹እስልምና ምንድን ነው›› በሚለው መጽሐፉ ውስጥ እንዲህ ይላል፡ ‹‹አንድ አውሮፓዊ ወይም አሜተሪካዊ እስልነምናን ለማጥናት ሲጀምር የሚገጥመው አንድ እና ብቸኛ ፈተና አግባብ የሌለው ጥላቻ ነው፡፡

መጽሐፉን እንደጀመረ እስልምናን የቁርአን ሃይማኖት ወይም የዛሬው የአራት መቶ ሚልየን ሙስሊሞች ሃይማኖት ብሎ በመግለፅ ይጀምራል፡፡ ከሃይመኖት ምድብ ጋር የማይስማማ ምድብ ያስተዋውቃል፡፡

ሃይማኖት ለምዕራባውያን ምንድን ነው?

ለተራ ሰው ሃይማኖት ማለት አንድ ሰአት ወይም እሁድ ቀን ብቻ ለእለታዊ ህይወቱ ጥንካሬ እና ድጋፍ የሚሰጠውን ተግባራት በመፈፀም ሰአት ማሳለፍ ነው፡፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር ወዳጅነትን በመፍጠር ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ከንግድ ፣ ከኢኮኖሚ ፣ ከፖለቲካ ወይም ከኢንዱስትሪ ጋር ግኑኝነት የለውም፡፡ ከዚህ ሁሉ የከፋው ደግሞ የበለፀጉ ግለሰቦች ላይ መንጠባረርን እና ትዕቢትን ይፈጥራል፡፡

አውሮፓውያን ሃይማኖት ተራ ሰዎችን ለማስገዛት ሲባል በተንኮለኞች የተፈጠረ ማደንዘዣ ዘዴ ነው ብለው ያምናሉ፡፡

ዊልያም ሞንቶጎምሪ ዋት

ዊልያም ሞንቶጎምሪ ዋት – በስኮትላንድ የተወለደ ኦሬንታሊስት እና በኤዲንበርግ ዩኒቨርስቲ የአረብኛ የአስልምና ጥናት ፕሮፌሰር ነው፡፡

ዋት በምዕራቡ አለም እስልምናን ከሚተረጉሙ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ክርስቲያን ምሁራን አንዱ ነበር፡፡

ይህ ደግሞ “አሏህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት እስልምና ብቻ ነው፡፡” (አል-ቁርአን 3፡19) ከሚለው የቁርአን አንቀፅ ጋር ምን ያህል እንደሚፃረር ተመልከቱ፡፡

ዲን የሚለው የአረብኛ ቃል ‹‹ሃይማኖት›› የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን የተሟላ የህይወት መንገድን ያመለክታል፡፡ ለግለሰቦች ግላዊ ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡

ይልቁንም የግል እና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ፣ የማህበረሰቡ አወቃቀር የሚያሰፋፋ ነው፡፡

ይህም አምልኮን ፣ የፖለቲካ ንድፈ ሃሳብን እና ዝርዝር የአኗኗር ደንቦችን (አውሮፓውያን ንፅህና ወይም ግብረገብ) ብለው የሚመድቧቸውን ጉዳዮች ጨምሮ የሚያካትት አጠቃለይ ሃይማኖታዊ መርህ ነው፡፡

እስልምና የአምልኮ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን፣ ከግል ሕይወት እስከ ማህበራዊ ግንኙነት ድረስ ያሉትን የሰው ልጅ እንቅስቃሴዎች በሙሉ የሚዳስስ የተሟላ የሕይወት መመሪያ (ዲን) ነው። የእስልምና ዋና መልእክት በአንድ አላህ ማመን ፣ እርሱን ብቻ ማምለክ እና በምድር ላይ ላሉ ፍጥረታት ሁሉ እዝነትን እና ርህራሄን ማሳየት ነው። አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአን ‹‹አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት እስልምና ብቻ ነው›› (አል-ኢምራን 3:19) በማለት እንደገለጸው፣ ይህ መንገድ ወደ እውነተኛ ሰላም፣ መንፈሳዊ እርካታ እና ዘላለማዊ ድነት የሚወስድ ግልጽና የማያሻማ መንገድ መሆኑን ጽሑፉ ያረጋግጣል።

0%
23
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የእስልምና ምሰሶች

የእስልምና ምሰሶች ጥያቄና መልስ

አምስቱን የእስልምና ምሰሶች ይመርምሩ፦ እምነት ፣ ሶላት ፣ ምጽዋት (ዘካ) ፣ ጾም እና ሐጅ (ጉዞ)፤ እንዲሁም (እነዚህ ምሰሶዎች) የዕለት ተዕለት ኑሮን ፣ ማኅበረሰብን እና አምልኮን እንዴት እንደሚቀርጹ ይመልከቱ።

ርዕሱን ይመርምሩ →

ይህን ጥያቄና መልስ ይሞክሩ

1 / 10

Bookmark question icon

1 . በሙስሊሞች ላይ ግዴታ የሆነው የምጽዋት (የዘካህ) መቶኛ ስንት ነው?

2 / 10

Bookmark question icon

2 . የእስልምና ምሰሶዎች ምንድን ናቸው?

3 / 10

Bookmark question icon

3 . ሙስሊሞች ለአንድ ወር የሚጾሙት (ሰውም) መቼ ነው?

4 / 10

Bookmark question icon

4 . ሙስሊሞች ለሐጅ ጉዞ (ሐጅ) ወዴት ይሄዳሉ?

5 / 10

Bookmark question icon

5 . አንድ ሙስሊም በቀን ስንት ጊዜ የግዴታ ሶላቶችን ይሰግዳል?

6 / 10

Bookmark question icon

6 . ሙስሊሞች ጸሎት (ሶላህ) በሚሰግዱበት ጊዜ ወደ የትኛው አቅጣጫ ይመለከታሉ (ይዞራሉ)?

7 / 10

Bookmark question icon

7 . በጾም (ሰውም) ወቅት ውሃ መጠጣት ይፈቀዳል?

8 / 10

Bookmark question icon

8 . አንድ ሙስሊም በህይወት ዘመኑ/ኗ ስንት ጊዜ ሐጅ ማድረግ አለበት/ባት?

9 / 10

Bookmark question icon

9 . እምነት (ሸሃዳ) ምንድን ነው?

10 / 10

Bookmark question icon

10 . ከምሰሶቹ መካከል በጣም አስፈላጊው ምሰሶ ተብሎ የሚወሰደው የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 30%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share