ተውሂድ (አሃዳዊነት) የአሏህን አንድነት በጌታነቱ (ተውሂደል ሩቡቢያ) ፣ በአምልኮቱ (ተውሂደል ኡሉሂያ) እና ፍፆም አንከን የሌለባቸው ስምና ባህሪያት (ተውሂደል አስማኡ ወሲፋት) መረዳት ማመን እና ማረጋገጥ ነው።
ተውሂድ

ተውሂድ (አሃዳዊነት) የአሏህን አንድነት በጌታነቱ (ተውሂደል ሩቡቢያ) ፣ በአምልኮቱ (ተውሂደል ኡሉሂያ) እና ፍፆም አንከን የሌለባቸው ስምና ባህሪያት (ተውሂደል አስማኡ ወሲፋት) መረዳት ማመን እና ማረጋገጥ ነው።

የተውሂድ አይነቶች

እነዚህ ሶስት የተውሂድ አይነቶች እንደሚከተለው ተገልፀዋል።

  1. ተውሂደል ሩቡቢያ፡

ማለት በዚህ ፍጥረተ አለም ላይ እና በውስጣቸው ያለ ነገር ሁሉ ጌታ አንድ አሏህ ብቻ ነው ብሎ ማመን ነው። የሁሉም ነገር ፈጣሪ እና አስገኝ አንድ አሏህ ብቻ ነው።

  1. ተውሂደል ኡሉሂያ፡

ማለት ከአሏህ በቀር ሊያመልኩት የሚገባ አንድም ነገር አለመኖሩን ማመን ነው። ሁሉም የአምልኮት ተግባራት ለምሳሌ ስግደት ፣ ፆም ፣ ስለት ፣ መሃላ ወ.ዘ.ተ የሚገባው ለእሱ ብቻ ማድረግ ነው።

  1. ተውሂደል አስማኡ ወሲፋት፡

ማለት አሏህ ውብ እና ፍፁም እንከን የሌላቸው ስምና ባህርያት አሉት ብሎ ማመን ሲሆን ትርጉማቸውን ሳይቀይሩና ሳያጣሙ ፣ ከፍጡራኖቹ ጋር ሳያመሳስሉ የእሱ ብቻ መሆናቸውን ማመን እና ማረጋገጥ ነው። ቅዱስ ቁርአን እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሹራ 42፡11)

እሱን የሚመስል ምን ነገር የለም። እሱ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው።

ሽርክ የተውሂድ ተቃራኒ ነው። ሽርክ አሏህ ፈፅሞ የማይምረው ወንጀል ነው።

0%
3
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የእስልምና ምሰሶች

ተውሒድ (የአላህ አንድነት)

በቁርአን መሰረት ወደ ጀሀነም እሳት የሚመራው ምንድነው? በዚህ ፈተና ውስጥ ይወቁ።
ተውሒድ ማለት የአላህ አንድነት ማለት ነው።
"ኢስላም" የሚለው ቃል "ሰላም" ከሚለው የአረብኛ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሰላም ማለት ነው፡፡ እንዲሁም "ሲልም" ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የራስን ፈቃድ ለአላህ ማስገዛት ማለት ነው። እስልምና "ተውሒድ" በሚለው መርህ ላይ ያምናል፤ ይህም በአንድ አምላክ ማመንን ብቻ (monotheism) ሳይሆን ከዚህም የላቀ ትርጉም አለው። ተውሒድ ቀጥተኛ ትርጉሙ "አንድ ማድረግ" ማለት ሲሆን "አንድነትን ማረጋገጥ" ማለት ነው። ይህ ቃል "ወሐደ" ከሚለው የአረብኛ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንድ ማድረግ፣ ማዋሀድ ወይም ማጠናከር ማለት ነው። ተውሒድ በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ሊከፈል ይችላል፡-
ሀ) ተውሒድ አር-ሩቡቢያህ (የጌትነት አንድነትን ማረጋገጥ)
ለ) ተውሒድ አል-አስማእ ወስ-ሲፋት (የአላህን ስሞችና ባህሪያት አንድነት ማረጋገጥ)
ሐ) ተውሒድ አል-ኢባዳህ (የአምልኮ አንድነትን ማረጋገጥ)

1 / 10

Bookmark question icon

1. በብቸኝነት የመመለክ መብት ያለው ማነው?

2 / 10

Bookmark question icon

2. ተውሒድ አል-አስማእ ወስ-ሲፋት ምንድነው?

3 / 10

Bookmark question icon

3. ተውሒድ አል-ኢባዳህ ምንድነው?

4 / 10

Bookmark question icon

4. አላህ ፈጽሞ የማይምረው ትላቁ ኃጢአት ምንድነው?

5 / 10

Bookmark question icon

5. የተውሒድ ትርጉም ምንድነው?

6 / 10

Bookmark question icon

6. ተውሒድ አር-ሩቡቢያህ ምንድነው?

7 / 10

Bookmark question icon

7. ተውሒድ በስንት ክፍሎች ሊከፈል ይችላል?

8 / 10

Bookmark question icon

8. አላህ በቁርኣን ውስጥ የሌሎች ሃይማኖቶችን አማልክት ስለመሳደብ ፣ ስለማዋረድ ወይም ስለማውገዝ ምን ይላል?

9 / 10

Bookmark question icon

9. በቁርአን መሰረት ወደ ጀሐነም እሳት የሚመራው ምንድነው?

10 / 10

Bookmark question icon

10. ሽርክ ማለት ምን ማለት ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 17%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ሽርክ እና ሸሃዳን ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share