የአምልኮት ተግባራት በእስልምና ውስጥ ትልቅ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ ኢባዳ አንድ ሙስሊም ሰው ከአሏህ ጋር ያለውን ቁርኝት ወይም ግኑኝነት የሚያጠነክርበት መንገድ ነው፡፡
እነዚህ ተግባራት ለአሏህ ያለንን ውዴታ እና ታዛዥነት ማሳያዎች ብቻ አይደሉም፤ ሙስሊሞች የተባረከ ህይወት እንዲመሩ የሚያስችሏቸውም ነው፡፡
በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የአምልኮ ተግባራት በእስለምና ውስጥ ያለውን መሠረት እና ለሙስሊሞች መንፈሳዊ ህይወት እድገት ያለውን አስቷፅኦ እንዳስሳለን፡፡
የአምልኮ ተግባራት በእስልምና ውስጥ
በእስልምና ውስጥ የአምልኮ ተግባራት ወደ አሏህ ለመቃረብ እና እምነትን (ኢማንን) ለማጠንከር የሚረዱ መጠነ ሰፊ ተግባራትን አቅፎ የያዘ ነው፡፡
እነዚህ ተግባራት ከፊሉ ግዴታ እና ከፊሉ ደግሞ የተወደዱ የሱና ተግባሮች ሲሆኑ ተግባራቶቹ የእስልምና እምነት ሁለንታ አካል ናቸው፡፡ በእነዚህ የአምልኮ ተግባራት ሙስሊሞች ለአሏህ ያላቸውን ውዴታ እና ታዛዥነት ይገልፃሉ፡፡
አምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች
አምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች በእስልምና እምነት ውስጥ የአምልኮ ተግባራት መሰረቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ምሰሶዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
የእምነት ምስክርነት ቃል (ሸሃዳ)
ሸሃዳ በእስልምና የማመን አዋጅ ወይም የእምነት ምስክርነት ቃል ነው፡፡ የዚህ ፍጥረተ አለም ፈጣሪ እና አስገኝ አምልኮ የሚገባው እሱ አሏህ ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ እና ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የነብያት መደምደሚያ (ማብቂያ) መሆናቸውን መመስከር ነው፡፡
ይህ የእምነት ምስክርነት ቃል ለእስልምና ሃይማኖት እና ለአምልኮ ተግባራቶች ሁሉ ዋና መሰረት ነው፡፡
ሶላት ወይም ስግደት
ሶላት ወይም ስግደት የእስልምና እምነት አንዱ ምሰሶ ነው፡፡
ሙስሊሞች ከከአሏህ ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር እና መመሪያውን በመፈለግ በቀን አምስት ጊዜ ይሰግዳሉ፡፡
ሶላት ወይም ስግደት ሊከተሏቸው የሚገቡ ልዩ ስርአተ ፀሎት እና አደቦች (ስነ-ስርአቶች) አሉት፡፡
እነሱም፡- ውዱዕ (ከፊል ትጥበት) ፣ ወደ ቂብላ (መካ ውስጥ ወዳለው የካዕባ አቅጣጫ) መዞር እና ከቁርአን የተወሰኑ አንቀፆችን ማንበብን ይይዛል፡፡
በሶላት ሙስሊሞች መንፈሳዊ ትስስራቸውን ያጠነክራሉ፤ ረፍት እና ስክነትም ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ተውባ (ንሰሃ) በማድረግ የአሏህን ምህረት ይለምናሉ፡፡
ዘካ (ምፅዋት)
ዘካ በእስልምና ውስጥ ግዴታ የሆነ የምፅዋት (የበጎ አድራጎት) ተግባር ነው፡፡
ይህም አንድ ሰው ዘካ መክፈል ግዴታ ከሚሆንበት ገንዘቡ የሚደርስበትን መጠን በማስላት ለተጨገሩ ሰዎች ማከፋፈልን ይይዛል፡፡
ዘካ በመስጠት ሙስሊሞች ሃብታቸውን ያጠራሉ፤ መተዛዘን ያጎለብታሉ፡፡ እናም በማህበረሰቡ ውስጥ ማህበራዊ ፍትህን ያሰፍናሉ፡፡
ፆም
በረመዷን ወር መፆም በእስልምና ውስጥ አካላዊ እና አዕምሯዊ ጤና ባለው ሙስሊም ላይ ሁሉ ግዴታ የሆነ የአምልኮ ተግባር ነው፡፡
በዚህ ወቅት ሙስሊሞች ከንጋት እስከ ፀሐይ ጥልቀት ድረስ ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ከሌሎች አካላዊ ፍላጎቶች እና ከክፉ ንግግር እና ተግባር ተቆጥበው ቀኑን በዱአ ፣ በዚክር ፣ በቁርአን ንባብ እና በስግደት ያሳልፋሉ፡፡
ፆም ነፍስን የሚያጠሩበት ፣ እራስን በጥሩ ድስፕሊን የሚያንፁበት እና ለተቸገሩት የሚያዝኑበት የሚራሩበት ነው፡፡
ሐጅ
ሐጅ በአካሉ ጤናማ እና የገንዘብ አቅም ያለው ሰው በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ማድረግ ግዴታ የሆነበት የአምልኮ ተግባር ነው፡፡
ሑጃጆች ተከታታይ የሆኑ ስርአተ አምልኮዎችን ይፈፅማሉ፡፡ ይህ ተግባራቸውም አንድነትን ፣ እኩልነትን እና ለአሏህ መታዘዝን ይገልፃል፡፡
ሐጅ ጥልቅ መንፈሳዊ ልምድን ፣ ከሏህ ጋር ሊኖር የሚገባ ትስስርን ማጠንከር እና በአለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊሞች ጋር የአብሮነት ስሜትን ይፈጥራል፡፡
ተጨማሪ የአምልኮ ተግባራት በእስልምና
ከአምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች በተጨማሪ ሙስሊሞች ከአሏህ ጋር ያላቸውን መንፈሳዊ ትስስር ለማጠናከር እና ለማሳደግ የሚረዷቸው ተጨማሪ የአምልኮ ተግባራቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
የሱና ሶላት
የሱና ሶላቶች ግዴታ ከሆኑ ሶላቶች በተጨማሪ የሚፈፀሙ ስግደቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ስግደቶች ትልቅ ሽልማት ወይም ምንዳ ያስገኛሉ፡፡ ከአሏህ ጋር ያለንን ትስስር ያሳድጋሉ፡፡
ዚክር አሏህን ማስታወስ
ይህ የአምልኮ ተግባር የተለያዩ ሐረጎችን ፣ አረፍተነገሮችን ፣ ውዳሴዎችን እና ፀሎት በመጠቀም ዘወትር አሏህን ማስታወስ ነው፡፡ አሏህ በቁርአኑ
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡152)
አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁና›› ብሏል
ዚክር ነፍሳችነን የምናጠራበት እና እድፎቿን የምናስወግድበት ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ እና ሙስሊም)
አሏህን የሚያወሳ በህያው ይመሰላል፡፡ አሏህን የማያወሳ ደግሞ በሙት ይመሰላል›› ብለዋል፡፡
የአምልኮ ተግባራት ውስጥ ኒያ (ማሰብ) ያለው ጥቅም
በእስልምና ውስጥ ከለአምልኮ ተግባራቶች ሁሉ ዋነኛ መሰረቱ ኒያ (ማሰብ) ነው፡፡ የኒያው ኢህላስ (ቅንነት እና ንፅህና) የአሏህን ውዴታ በመፈለግ እና ሽልማቶችን በማግኘት ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና አለው፡፡
ሙስሊሞች ኒያቸውን ሙሉ በሙሉ ለአሏህ ብቻ ሲሉ ማድረግ አለባቸው፡፡ ሆኖም እነዚህ የአምልኮ ተግባራት እና ማንኛውም ስራዎች የአሏህን ውዴታ እና ሽልማት ለማግኘት እንጅ አለማዊ ጥቅም እና ዝና ለማግኘት ተብሎ የሚፈፀሙ መሆን የለበትም፡፡

