ቂብላ ማለት ሁሉም ሙስሊሞች ሶላታቸውን ሲሰግዱ መካ ውስጥ ወደሚገኝ ካዕባ ፊታቸውን አዙረው የሚሰግዱበት አቅጣጫ ነው። ቁርአን እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡144)
ፊታችሁን ወደ መስጅደል ሐረም አቅጣጫ አዙሩ፤ እናም የትም ቦታ ብትሆን ፊታችሁን ወደ እሱ አቅጣጫ አዙሩ።


በይተል መቅዲስ (አል-አቅሷ መስጅድ) ቁድስ እየሩስ አሌም ውስጥ የሚገኝ ከካዕባ በፊት የነበረ የመጀመሪያው የኢስላም ቂብላ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መካ ውስጥ እያሉ ወደ በይተል መቅዲስ ፊታቸውን አዙረው ይሰግዱ ነበር።

ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ ደግሞ ለአስራ ስድስት ወራት በይተል መቅዲስ ቂብላቸው ሆኖ ቆይቷል። መካ ውስጥ ወደ ሚገኘው ካዕባ ዞረው ተማፀኑ።
አሏህ ፀሎታቸውን እንዲህ ሲል ተቀበላቸው፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡144)
በእርግጥ የፊትህን ወደ ሰማይ መዞር አይተናል፤ በእርግጥ ወደ ምትወደው ቂብላ እናዞርሃለን።
ስግደቶች ሁሉ ተቀባይነት አይኖራቸውም ወደ ቂብላ በመዞር ቢሆን እንጅ። ይህ የሙስሊሞች አንድነት ዋልታ፤ የልቦቻቸው እና የነፍሶቻቸው መገናኛ ቦታ ነው።
የቂብላ አቅጣጫ የማያውቅ ሰው መጠየቅ አለበት። ሊጠይቀው የሚችለው አንድም ሰው ከሌለ፤ ሶላቱን ለመስገድ ትክክለኛውን አቅጣጫ ለማግኘት የቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት። ይሁንእንጅ ሶላቱን ከሰገደ በኋላ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ መዞሩን ከተረዳ ሶላቱን መድገም አያስፈልግም። ነገርግን ሶላት ላይ እያለ መሳሳቱን ካወቀ ሶለቱን ሳይተው ወደ ቂብላ አቅጣ መዞር ይችላል።

መስጅደል ሐረም እና በየቱል መቅዲስ ተመልከቱ




Share