በይተል መቅዲስ (ቅዱሱ ቤት) በእየሩስ አሌም ውስጥ የሚገኝ መስጅድ ሲሆን መስጅደል አቅሷ (ሩቁ መስጅድ) ተብሎም ይጠራል።

ይህ መስጅድ በምሽቱ ጉዞ (ኢስራዕ) አሏህ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ).ከመካ ቅዱሱ መስጅድ አንስቶ ይዟቸው የሄደበት ነው።

አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢስራዕ 17፡1)
ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጅድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጀድ በሌሊት ውስጥ ያስሄደው (ጌታ) ጥራት ይገባው። ከተአምራቶቻችን ልናሳየው (አስሄድነው)። እነሆ እሱ (አሏህ) ሰሚው ተመልካቹ ነው።

በይቱል መቅዲስ ጉዞ ሊደረግባቸው ከሚገቡ ሶስት መስጅዶች ውስጥ አንዱ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“ከሶስት መስጅዶች ውጭ ማንኛውንም ቦታ ለመጎብኘት ልዩ ጉዞ መጀመር የለባችሁም። የመካ ቅዱሱ መስጅድ ፣ ይህ የእኔ መስጅድ እና አል-አቅሷ መስጅድ ነው።”
መስጅድ ፣ አል-አቅሷ እና ሚዕራጅ ፣ መስጅደል ሐረም እና መስጅደል ነበውይ ተመልከቱ



Share