የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው። ምግብ እና ለህመም መድሃኒት ነው፡፡
የዘምዘም ውሃ

ነብዩ ኢብራም (ዐ.ሰ) ከሚስታቸው ሐጀር እና ከልጃቸው ነብዩ ኢስማኤል (ዐ.ሰ) ጋር እፅዋትም ውሃም ወደ ሌለው ሸለቆ አሁን ላይ መካ ተብሎ ወደ ሚጠራው ቦታ በተሰደዱ ጊዜ ተምር የያዘ አንድ ከረጢት እና አንድ የውሃ ኳዳ ብቻ ጥሎላቸው ትቷቸው ሄደ።

ውሃው ባለቀ ጊዜ ሐጀር ስለ ልጇ በጣም ተጨነቀች፤ የሶፋን አለታማ ኮረብታ ወጥታ ተመለከተች፤ ምንም ነገር የለም። ተረተሩን ወርዳ ወደ መርዋ ኮረብታ ወጥታ ተመለከተች፤ ምንም ነገር የለም።

በመካከላቸው ሰባት ጊዜ ተመላለሰች። በመጨረሻም መርዋ ላይ በቆመች ጊዜ የሆነ ድምፅ ሰማች፤ መላኢካ የዘምዘም ቦታ ላይ ቆሞ መሬቱን በክንፉ መታው። ውሃይቱ ፊልፊል አለች። ዙሪዋን ከተረች። በእጆቿ የውሃ ኳዳዋን ሞላች።

እናም ጠጣች፤ ልጇንም አጠባች። መልአኩ እንዲህ አላት “መተውን አትፍሪ፤ ይህ በዚህ ልጅ እና በአባቱ የሚገነባ የአሏህ ቤት ነው። አሏህ ሰዎቹን ፈፅሞ አይተውም።” (ቡኻሪ)

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ

የዘምዘም ውሃ ለጠጡበት አላማ ያገለግላል

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ጦበራኒ)

“በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው። ምግብ እና ለህመም መድሃኒት ነው።”

በአንድ ወቅት አቡዘር (ሰ.ዐ.ወ) ለ30 ቀን በዘምዘም ውሃ አካባቢ በቆየ ጊዜ ክብደቱ ጨመረ፤ ሆዱ ላይ የስብ እጥፋት ክምችት ነበር።

ምንም የርሃብ ስሜት አልተሰማውም። ይህን ለነብዩ በነገራቸው ጊዜ እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“የዘምዘም ውሃ የተባረከ (የተቀደሰ) ነው። እንደ ምግብ ያገለግላል።”

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ “የዘምዘም ውሃ ለሚጠጣበት አላማ ያገለግላል።” ኢብን ማጃ ስለዚህ ህክምናን ፈልጎ አስቦ ለጠጣው ሰው በእርግጥ አሏህ ከህመሙ ያሽለዋል።

ለህክምናው ብለው አስበው ይህን የተቀደሰ ውሃ በመጠጣት ከአደገኛ በሽታቸው የተፈወሱ ሰዎች እውነተኛ ታሪኮች አሉ።

አንዱ ታሪክ ከካንሰሰር በሽታ የዳነችው የሞሮኮ ተወላጅ የሆነችው ለይላ አል-ሂለው የተባለች ሴት ታሪክ ነው።

ቤልጂየም ውስጥ ሃኪሞችን ስታማክር ለዚህ ገዳይ በሽታ የሚያሽል መድሃኒት ሊሰጧት እና ሊያክሟት ስላልቻሉ፤ ባሏ ወደ ቤቷ እንዲወስዳትና ሞቷን እንድትጠባበቅ ነገሯት።

ይሁን እንጅ እሷና ባሏ መካ ከተማ ውስጥ ቅዱሱን ቤት ለመጎብኘት ወሰኑ። እዚያም የዘምዘም ውሃ ለሚጠጡበት አላማ እንደሚያገለግል ስለምታውቅ አብዝታ ጠጣችው። በጣም አለቀሰች ፣ ቅዱስ ቁርአን ቀራች፤ ሃያሉ አሏህ እንዲያሽላት ተማፀነች።

ጓደኞቿም የላይኛውን የሰውነቷን ክፍል ማለትም በጡት ካንሰር ምክኒያት ያበጠውን ክፍል እንድታጥበው መከሯት።

አንድ ቀን አሏህ ያሻላት መሆኑን ደረሰችበት። ይህንንም ታሪክ በአንድ መፅሐፍ ላይ አሰፈረች። መጽሐፉ እንግሊዘኛን ጨምሮ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።

ዘምዘም

ኢብራሂም ፣ ኢስማኤል እና ሰኢ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና በኢትዮጵያ፡

እስልምና በኢትዮጵያ፡ ከጥንታዊ ሥረ-መሠረቱ እስከ ዘመናዊ ስርጭቱ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዷ ስትሆን በርካታ እምነቶች ያስተናገደች ምድርም ነች። ከእነዚህም መካከል እስልምና እና ክርስትና ይገኙበታል። እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሃይማኖት

Read More »
የቀናት አቆጣጠር

የእስልምና የቀናት አቆጣጠር

ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀናት አቆጣጠር አልነበራቸውም። ምንም እንኳ አስራ ሁለቱን የጨረቃ ወራቶች ቢያውቁም ጊዜን የሚያሰሉት አንድ ልዩ ክስተት ከፊቱ ወይም ከኋላው የተከሰተበትን ጊዜ

Read More »
መስጅደ ነበውይ

መስጅደ ነበውይ የነብዩ መስጅድ

ነብዩ ያኔ ያስሪብ ተብላ ወደምትጠራው የአሁኗ መዲና በተሰደዱ ጊዜ ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያ ተከታዮቻቸው እና የከተማዋ ሹማምንት ምርጥ ልብሶቻቸውን እና የብረት መከላከያ ልብሶችን እንደለበሱ ተቀበሏቸው።

Read More »
መስጅደል ሐረም

መስጅደል ሐረም

መስጅደል ሐረም መካ ውስጥ የሚገኝ ሐጀረል አስወድን (ጥቁሩ ድንጋይ) እና ካዕባን በውስጡ የያዘ ቅዱስ መስጅድ ነው።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share