የእስልምና የቀናት አቆጣጠር

Author picture
ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀናት አቆጣጠር አልነበራቸውም። ምንም እንኳ አስራ ሁለቱን የጨረቃ ወራቶች ቢያውቁም ጊዜን የሚያሰሉት አንድ ልዩ ክስተት ከፊቱ ወይም ከኋላው የተከሰተበትን ጊዜ በመያዝ ነው
የቀናት አቆጣጠር

ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀናት አቆጣጠር አልነበራቸውም። ምንም እንኳ አስራ ሁለቱን የጨረቃ ወራቶች ቢያውቁም ጊዜን የሚያሰሉት አንድ ልዩ ክስተት ከፊቱ ወይም ከኋላው የተከሰተበትን ጊዜ በመያዝ ነው። ለምሳሌ እንደ “የዝሆኑ አመት” ያለ።

የጨረቃ የቀናት አቆጣጠር

የእስልምና የቀናት አቆጣጠር መሰረቱ ሙሉ በሙሉ የጨረቃ ኡደት ነው። በዚህ ዘመን ይጠቀሟቸው የነበሩ ተፃራሪ የአቆጣጠር ዘዴዎችን ለማስቀረት ይህን የእስልምና የጨረቃ አቆጣጠር ያስተዋወቀው ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ነው። ይህ የሆነው በአንድ ወቅት በሻዕባን ወር የተፃፈ ሰነድ በተቀበለ ጊዜ ነው።

ሂጅራ

ሰነዱ የሚያመለክተው በዛ አመት የሸእባን ወር ይሁን በቀጣዩ አመት እርግጠኛ አልነበረም። እናም በአዲሱ የእስልምና የቀናት አቆጣጠር መጀመሪያ ዙሪያ አማካሪዎቹን አማከረ። ከብዙ ውይይት በኋላ ጥሩ መነሻ ሂጅራ መሆኑን ተስማሙ። ይህ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ወደ መዲና ከተማ ያደረጉትን ስደት እንደ መነሻ ምልክት የተጠቀሙበት ነው።

ምንም እንኳ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በረቢኡል አወል ወር ቢሰደዱም ኡመር (ረ.ዐ) ግን ሙሐረም የጨረቃ ወር መጀመሪያ በመሆኑ ሙሐረምን የእስልምና የጨረቃ የቀናት አቆጣጠር መጀመሪያ አድርገው መርጠውታል።

አንዳንዶች ይህን የቀናት አቆጣጠር ዓ.ሂ ብለው ያሳጥሩታል። ይህ ማለት አመተ ሂጅራ (የስደቱ አመት) ማለት ነው። ሙስሊሞች የእስልምና የቀናት አቆጣጠርን እንዲጠቀሙ ይገደዳሉ። ምክኒያቱም ሁሉም የእስልምና ድንጋጌዎች ከእሱ ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ጊዜውን መከታተል ስለሚያስፈልግ ነው። ለምሳሌ ከረመዷን ፆም እና ከሐጅ ስነስርአቶች ጋር የተያያዙት።

0%
16
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

የእስልምና የቀናት አቆጣጠር

ሙስሊሞች ጊዜን የሚለኩት የእስልምና (ሂጅራ/ሂጅሪ) የቀን መቁጠሪያን በመጠቀም ነው። ይህ የቀን መቁጠሪያ አስራ ሁለት የጨረቃ ወራት ያሉት ሲሆን የወራቱ መጀመሪያና መጨረሻ የሚወሰነው የጨረቃን ወጭት (الهلال) በማየት ነው። እያንዳንዱ ወር 29 ወይም 30 ቀናት አሉት። የእስልምና የቀን መቁጠሪያ ወር የሚጀምረው የጨረቃ ወጭት በዓይን ከታየበት ቀን ጀምሮ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። የጨረቃ ዓመት በግምት 354 ቀናት ርዝመት አለው።
የእስልምና የቀን መቁጠሪያ የተመሰረተው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እና ሰሃቦቻቸው (ባልደረቦቻቸው) ከመካ ወደ መዲና በተሰደዱበት (ሂጅራ) ዓመት ላይ ነው። "ሂጅራ" የሚለው የአረብኛ ቃል ስደት ማለት ነው። ይህ ስደት (ሂጅራ) የመጀመሪያውን የእስልምና መንግስት በመዲና ለመመስረት የመጀመሪያው እርምጃ በመሆኑ ከእስልምና ታሪክ አስፈላጊ ምዕራፎች አንዱ ነው።
የእስልምና የቀናት አቆጣጠር ምን ተብሎ ይሰየማል? በዚህ ፈተና ውስጥ ይወቁ።

1 / 10

Bookmark question icon

1. የእስልምና የቀን መቁጠሪያ ከሚከተሉት ኡደቶች በየትኛው ላይ የተመሰረተ ነው?

2 / 10

Bookmark question icon

2. የዒድ አል-ፊጥር በአል መቼ ነው የሚከበረው?

3 / 10

Bookmark question icon

3. በዙል-ሒጃ ወር ውስጥ የትኛው አስፈላጊ የእስልምና ምሰሶ ይዘከራል?

4 / 10

Bookmark question icon

4. ቁርአን የወረደው በየትኛው ወር ነው?

5 / 10

Bookmark question icon

5. በመላው ዓለም ያሉ ሙስሊሞች ለአንድ ወር ከንጋት እስከ ምሽት የሚጾሙት በየትኛው ወር ነው?

6 / 10

Bookmark question icon

6. የእስልምና የቀን መቁጠሪያ ምን ተብሎ ይሰየማል?

7 / 10

Bookmark question icon

7. ዒድ አል-አድሐ የሚከበረው በየትኛው ወር ነው?

8 / 10

Bookmark question icon

8. በኢስላም ውስጥ ጦርነትና ማንኛውም አይነት ውጊያ የተከለከለባቸው አራቱ የተቀደሱ ወራት የትኞቹ ናቸው?

9 / 10

Bookmark question icon

9. የእስልምና የቀን መቁጠሪያ የመጀመሪያ ወር ምንድነው?

10 / 10

Bookmark question icon

10. አንድ የእስልምና ወር ስንት ቀናትን ያካትታል?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 21%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ፣ አመል ፊል እና ሂጅራ ተመለልከቱ

Related posts

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው።

Read More »
እስልምና በኢትዮጵያ፡

እስልምና በኢትዮጵያ፡ ከጥንታዊ ሥረ-መሠረቱ እስከ ዘመናዊ ስርጭቱ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዷ ስትሆን በርካታ እምነቶች ያስተናገደች ምድርም ነች። ከእነዚህም መካከል እስልምና እና ክርስትና ይገኙበታል። እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሃይማኖት

Read More »
መስጅደ ነበውይ

መስጅደ ነበውይ የነብዩ መስጅድ

ነብዩ ያኔ ያስሪብ ተብላ ወደምትጠራው የአሁኗ መዲና በተሰደዱ ጊዜ ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያ ተከታዮቻቸው እና የከተማዋ ሹማምንት ምርጥ ልብሶቻቸውን እና የብረት መከላከያ ልብሶችን እንደለበሱ ተቀበሏቸው።

Read More »
መስጅደል ሐረም

መስጅደል ሐረም

መስጅደል ሐረም መካ ውስጥ የሚገኝ ሐጀረል አስወድን (ጥቁሩ ድንጋይ) እና ካዕባን በውስጡ የያዘ ቅዱስ መስጅድ ነው።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share