ሂጅራ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና መልእክተኞቹ ከመካ ወደ መዲና ያደረጉት ስደት ነው። ሂጅራ የተካሄደበት የሙስሊሞች አመት የመጀመሪያው የኢስላም የቀን አቆጣጠር ነው፡፡
ሂጅራ

ሂጅራ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና መልእክተኞቹ ከመካ ወደ መዲና ያደረጉት ስደት ነው።

ሂጅራ

በአመታዊ ሐጅ ወቅት ሚና ላይ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባደረጉት ዳዕዋ (ጥሪ) የተወሰኑ ሰዎችን መሳብና እስልምናን እንዲቀበሉ ማድረግ ችለው ነበር። በተከታዩም አመት የታማኝነት መሃላን ወሰዱ።

ይህ ማሃላ የመጀመሪያው የአቀባ ቃልኪዳን ተብሎ ይጠራል።  ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሙስአብ ኢብን ኡመይር (ረ.ዐ) በጣም በፍጥነት የተስፋፋውን እምነት ለሰዎች እንዲያስተምር ወደ መዲና ልከውት ነበር።

የሐጅ ወቅት በድጋሚ በደረሰ ጊዜ ሁለተኛውን የአቀባ ቃልኪዳን ለመፈፀም በጉጉት በሚስጥር በሰልፍ በሄዱ 72 ተከታዮች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን ተከበው አገኙት።

ያኔ እምነቱን ለመቀበል ፣ ምንም እንኳ በህይወታቸው ዋጋ የሚያስከፍላቸው ቢሆንም እምነቱን እና ነብዩን ለመጠበቅ ቃልኪዳናቸውን ሰጡ።

የመዲና ጉዞ

በነብዩ አዛኝነት ሙስሊሞች በቡድን በቡድን ሁነው ቤቶቻቸውን እና ሃብት ንብረታቸውን ለእምነታቸው ሲሉ እዚያው ትተው በሚስጥር ወደ መዲና ጉዞ አድርገዋል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለመሰደድ የአሏህን ትዕዛዝ ከተቀበሉ ቡኋላ ይህንኑ ለማድረግ ወሰኑ።

የሰውር ተራራ ዋሻ

በአቡ በክር (ረ.ዐ) በመታጀብ ለሶስት ቀን ያህል በመካ አቅራቢያ በሚገኘው የሰውር ተራራ ዋሻ ውስጥ ከሃዲያኖች እነሱን ፈልገው ለማግኘት ተስፋቸውን እስኪቆርጡ ድረስ እራሳቸውን ደበቁ።

መዲና በደረሱ ጊዜ ሰዎች በደስታ ፈንጠዝያ አሏሁ አክበር እያሉ እሳቸውን ለማግኘት እየተጣደፉ ተቀበሏቸው።

መዲና ውስጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጊድ ገንብተዋል፤ በአንሷር እና በሙሐጅሮች መካካል የወንድማማችነትን ግኑኝነት መሰረት አስይዘዋል። ሂጅራ የተካሄደበት የሙስሊሞች አመት የመጀመሪያው የኢስላም የቀን አቆጣጠር እንዲሆን በኡመር ኢብን አል-ኸጣብ ተወስኗል።

ሰሃባ ፣ መካ ፣ መዲና እና የእስልምና የቀናት አቆጣጠር እና ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ተመልከቱ

Related posts

የሙዕሚኖች እናት

ኡመሃተል ሙዕሚኒን (የሙዕሚኖች እናት) የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ናቸው። እያንዳንዳቸውም የእናትነት ደረጃ አላቸው። ሆኖም ላቅ ያለ ክብር ይገባቸዋል። ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሞት በኋላ አንዳቸውንም ማግባት የተከለከለ ነው።

Read More »
ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።

Read More »
የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው።

Read More »

Share