አቡበክር በትክክል ከተመሩት ኸሊፋዎች ውስጥ አንዱ ነው። ከነብዩ (ﷺ) በሁለት አመት እድሜ ከፍ ያለ ነበር። ከታላቅ ቤተሰብ የሆነ የመካ ከበርቴ ነጋዴዎች ውስጥ አንዱ ነበር። በምስጉን ባህሪው እና ለእምነት ዘብ በመቆም ይታወቃል።
ታማኝነቱ እና ከቀናነቱ የወጣቱ ሙሐመድን ጓደኝነት እንዲያገኝ አስችሎታል። ይህ ጓደኝነት በወጣትነት ጊዜ የጀመረ ሲሆን እስከ ህይወት ፍፃሜያቸው ድረስ መዝለቅ ችሏል።
አቡ በክር እስልምናን የተቀበለ የመጀመሪያው ሰው ነው። እስልምናን የተቀባለውም ያለምንም ማመንታት ነበር። አንዴ ነብዩ ( ﷺ) “ሰዎችን ወደ ኢስላም እጠራለሁ እናም ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ያህል ያስቡበታል።
ነገርግን ይህ ሁኔታ አቡበክር ጋር አልነበረም። እስልምና ከፊቱ በቀረብኩላት ጊዜ ያለምንም ማመንታት ተቀበለ ብለዋል።
አቡበክር በጣም ደግ ሰው ነበር። የሆነ ሰው ተቸግሮ ባየ ጊዜ እሱን ሊረዳው የሚችልን ነገር ሁሉ ያደርግለት ነበር። ለእምነቱ ሲል የማይከፍለው መስዋእት አልነበረም። አረመኔ የቁረይሽ ገዥዎች (ባላባቶች) ባሪያዎቻቸው እስልምናን እንዲተው አሸዋ ላይ እራቁታቸውን አስተኝተው ይገርፏቸው ነበር።
ልክ ቢላል ኢብን ረባህ ላይ እንዳደረጉበት ማለት ነው። ትልቅ ቋጥኝ ደረታቸው ላይ ያስቀምጡባቸው ነበር። አቡበክር ( ) እንደዚህ ያሉ ረዳት የሌላቸው ሙስሊም ባሪያዎችን ከአረመኔ ባለቤቶቻቸው ለመግዛት ሃብቱን ይጠቀም ነበር። እናም ለአሏህ ሲል ነፃ ያወጣቸዋል።
ነብዩ (ﷺ) በተቡክ ዘመቻ ሰዎች በሚችሉት ነገር ሁሉ እንዲረዷቸው በጠየቁ ጊዜ አቡበክር ( ) ሁሉንም ገንዘቡን እና የቤት ውስጥ እቃዎች በማምጣት የነብዩ እግሮች ላይ ቆለለላቸው። ሁሉንም ማግኘት ቻሉ።
አሲዲቅ (እውነተኛው)
ነብዩ (ﷺ) አሲዲቅ (እውነተኛው) ብለው ይጠሩታል። ምክኒያቱም ነብዩ (ﷺ) ከጅብሪል ( ) ጋር ወደ ሰማይ የምሽቱን ጉዞ ባደረጉ ጊዜ እና ጠላቶቻቻው በቀለዱባቸው (ባሾፉባቸው) ጊዜ አቡበክር
ስለዚህ ክስተት ታዕማኝነት ተጠይቆ ሲመልስ “የአሏህ መልዕክተኛ (ﷺ) ያሉትን ማንኛውንም ነገር አምናለሁ” ሲል መልሷል።
የመዲና ታሪካዊ ጉዞ ሁሉንም ያደራጀው እና ነብዩ (ﷺ) የሸኘው አቡበክር ( ) ነበር። ከሁሉም ሶሃባዎች፤ አቡበክር በዚያ ወሳኝ የህይወቱ ቀናቶች ከነብዩ (ﷺ) ጋር መሆኑ ክብር አለው። ነብዩ (ﷺ) በተሳተፉባቸው ሁሉም ጦርነቶች ተሳትፏል። ሙሉ ህይወቱን በእሱ አርማ ስር ሲፋለም ኑሯል። በእሱ ተቆጣጣሪነትም የቁርአን ራዕይ እንዲሰበሰብና እንዲሰነድ አድርጓል።
ነብዩ (ﷺ) በታመሙበት በመጨረሻዎቹ ጊዜያት ሶላትን መምራት ባለመቻላቸው ለዚህ ተግባር እሱን መርጠዋል።
የመጀመሪያው ኸሊፋ
ከነብዩ ( ) ሞት በኋላ ሙስሊሞች የመጀመሪያው ኸሊፋ አድርገው መርጠውታል። የማይዛነፈው ኢማኑ መሰረቱን ጠብቆ እንዲቆይ ረድቷል። እነዚያ እስልምናን የተውና ሙስሊሞችን መዋጋት የጀመሩትን ይፋለም ይዋጋ ነበር።
ለምሳሌ ሃይለኛ የበኑ በክር ጎሳ። ግዴታ የሆነውን የድሆች መዋጮ (ዘካ) አንከፍልም ባሉት ላይም ጦርነት አውጇል። እንደ ሙሰይሊማ ባሉ ውሸታም አስመሳይ ነብይ ነን ባዮች ላይ ሁሉን አቀፍ ጥቃት ፈፅሟል። አቡበክር ( ) ሁሉም ሽንፈትን አከናንቧቸዋል።
አቡበክር ( ) በኢማኑ ጠንካራ እንደነበረ ሁሉ ቅንም ነበር። እስከ መጨረሻ የህይወቱ እስትንፋስ ድረስ ለኢስላም ኑሯል፤ ሰርቷልም። በስልሳ ሶስት አመቱ በሞተ ጊዜ የተቀበረው በነብዩ (ﷺ) ጎን ነበር።
ነብዩ (ﷺ) በአንድ ወቅት ስለ እሱ እንዲህ ብለዋል፡ “ከኡመቶቼ ኸሊል አድርጌ ብመርጥ ኖሮ አቡበክርን እመርጥ ነበር። ነገርግን ጓደኛየ እና ሶሃባየ ነው።” (ቡኻሪና ሙስሊም)
ኸሊል ማለት ውዴታው ከነፍሱ ጋር የተቀላለቀለ ሰው ነው። በእርግጥ እሱ ከጓደኛም ከወዳጅም በላይ ነው። ነብዩ (ﷺ) አንድ ብቻ ሃሊል ነው የነበራቸው። እሱም ሃያሉ አሏህ ነው። ነገርግን ብዙ ጓደኞች ነበሯቸው።
ሶሃባ ፣ ኹለፋኡ ራሽዱን ፣ ኢስራዕ እና ሚዕራጅ ተመልከቱ ለበለጠ መረጃ