አሊ ኢብን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)

Author picture

አሊ ኢብን አቢ ጧሊብ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አጎት ልጅ ነበር። የተወለደው ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ውልደት ከ30 አመት በኋላ ነው። አቡጧሊብ ደሃና በጣም ትልቅ ቤተሰብ የነበራቸው በመሆኑ አሊ (ረ.ዐ) በተወለደ ጊዜ የአጎታቸውን ሸህም ለማቃለል ሲሉ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤታቸው ወስደው ልክ እንደራሳቸው ልጅ አድርገው አሳድጉት።

አሊ (ረ.ዐ) በጥሩ ሁኔታ በደግነት እና በሃይማኖተኝነት አደገ። እሱ እስልምናን የተቀበለ የመጀመሪያው ልጅ ነው።

አሊ (ረ.ዐ) ፈፅሞ ለጣኦት አልሰገደም። በሃይማኖተኝነቱ እና በትሁትነቱ ፣ በጀግንነቱ እና የአሏህን ሃይማኖት ለማገልገል እና መልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) ለመጠበቅ በነበረው ጥንካሬ በደንብ ይታወቃል። በእርግጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በህይወት በነበሩ ጊዜ የተዋጋባቸው የብዙ ጦርነቶች ጀግና ነው።

ምክኒያቱም አሊ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የፍቅር እንክብካቤ ስር ሆኖ ነው ያደገው። ይህ ደግሞ የኢማን እና የሕይወት እውነታዎችን በጥልቀት እንዲያስተውል እንዲገነዘብ አድርጎታል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጃቸውን ፋጢማን ለእሱ በመዳር የቅርብ የደም ዝምድናቸውን ዳግም አጠናክረዋ። ፋጡማ (ረ.ዐ) ከሁሉም በላይ አብዝተው የሚወዷት የሁሉ ታናሽ ልጅ ናት። ከእሷ ቀጥሎ አሊ ፣ ሐሰን ፣ ሑሴን ፣ ሙህሲን እና ኡሙ ኩልሱም  ናቸው።

አሊ ከተማሩ አዋቂ ሰዎች መካከል አንዱ ነው። የወህዩ (ራዕዩ) ቁም ፀሃፊዎች መካከል አንዱ ነበር። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሚልኳቸውን ደብዳቤዎችም ይፅፍ ነበር። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የጀነት ምንዳ የምስራች ዜና በህይወት እያሉ ከሰጧቸው አስር ሶሃባዎች መካከል አንዱ ነው።

በትክክል የተመሩት ሶስቱ ኸሊፋዎች የእሱ ምክር ላይ ብዙ ይተማመኑ ነበር። ኡመር (ረ.ዐ) እንዲህ ይልነበር። ከኛ መካከል ጥሩ ዳኛ አሊ ነው።

አሊ (ረ.ዐ) የንጋት ስግደቱን ሊፈፅም ጎዞ ላይ በነበረበት ጊዜ በተመረዘ ሰይፍ ከጀርባው በኩል ተወጋ። ከመሞቱ በፊት ገዳዩ አብዱረህማን ኢብን ሙልጅም በፍጥነት ተገርፎ ሳይሆን በሰብአዊነት ተይዞ በስርአት እንዲገደል አዟል። የሞተው ኩፋ ውስጥ ሲሆን የተቀበረውም እዛው ነው። በትክክል ከተመሩት ኸሊፋዎች ውስጥ የመጨረሻው ነው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአንድ ወቅት ልክ ሃሩን ለሙሳ እንደሆነው፤ አንተም ለእኔ በመሆንህ አትደሰትምን? ነገርግን ከእኔ በኋላ ነብይ አይኖርም ብለውታል። (ቡኻሪ)

እንዲሁም አንድ  ወቅት አንተ ከእኔ ነህ፤ እኔም ከአንተ ነኝ ብለውት ነበር።

ኡመር (ሰ.ዐ) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደተደሰቱበት ሞቱ ብሏል። (ቡኻሪ)

ሶሃባና ኹለፋኡ ራሽዱን ተመልከቱ

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top