አሏህ የአንድና ብቸኛ እውነተኛ ሃያል ጌታ ስም ነው። አምልኮ የሚገባው እሱ ብቻ ነው። ቃሉ ፆታ ወይም ብዙ ቁጥር አመልካች የለውም።
አሏህ

አሏህ የአንድና ብቸኛ እውነተኛ ሃያል ጌታ ስም ነው። አምልኮ የሚገባው እሱ ብቻ ነው። ቃሉ ፆታ ወይም ብዙ ቁጥር አመልካች የለውም። ይህ የሚያሳየው ቃሉ በራሱ ልዩ መሆኑን ነው።

አላህ የፍጥረተ አለሙ በሙሉ ፣ የሰማያት ፣ የምድር ፣ የሰው ፣ የጅን ፣ የመለአክቶች ፣ የእንስሳት ፣ ህይወት ያላቸውም የሌላቸውም ነገር ፣ የሚታየውም የማይታየውም ነገር ብቸኛ አምላክ ነው።

መፍጠርም ማዘዝም የእሱ ስልጣን ብቻ ነው። ያሻውን ይፈርዳል፤ ፍርዱንም የሚቀለብስ አንድም ነገር የለም።

የእውቀቶች ሁሉ ቁልፍ እሱ ጋር ነው። እውቀቱ እና ጥበቡ አጥናፍ ወሰን የለውም።

አሏህ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው። ፍጡራኖቹ ሁሉ የሚሰሩትን ያውቃል። በምድርም በባህርም ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል።

አንዲትም ቅጠል አትረግፍም እሱ የሚያውቃት ቢሆን እንጅ። የሰማያት እና የምድር ግዛት የሚገባው ለእሱ ነው።

ያሻውን ይሰራል፤ ሁሉም ስራው በጥበብ የተሞላ ነው። በዚህ ፍጥረተ አለም ውስጥ ያልተከሰተውን እና የሚከሰተውን ማንኛውንም ነገር ያውቃል። እሱ የወሰነውን የደነገገውን ማንም መቀየር አይችልም።

ብቻውን ሊመለክ የሚገባው እውነተኛ አምላክ እሱ ነው። ከእሱ ውጭ የሚመለክ ማንኛውም ነገር የውሸት አማልክት ነው።

አላህ በጣም ውብ ስሞችና ፍፁም እንከን የሌለባቸው ባህሪያት አሉት። እነዚህ ውብ እና ፍፁም እንከን የሌለባቸው ስምና ባህሪያት ትርጉማቸውን ሳያዛቡ ፣ ሳያጣምሙ እና ሳይክዱ በቁርአን እና በሱና እንደተቀመጡት የአሏህን ልቅና በሚስማማ መልኩ ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ቅዱስ ቁርአን እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሹራ 42፡11)

“እሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም፤ እሱ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው።”

ላኢላሃ ኢለሏህ  የእምነት ምስክርነት ቃል

ላኢላሃ ኢለሏህ የእምነት አዋጅ ሲሆን ትርጉሙም በሐቅ ሊመለክ የሚገባው አንድም ነገር የለም፤ አላህ ብቻ ሲቀር ማለት ነው።

ይህ የእምነት ምስክርነት ቃል ከአሏህ ውጭ ያሉ የውሸት አማልክትን እና አምልኮን ውድቅ ያደርጋል።

አሏህ ጥራት ይገባው! ይህ ቃል ሲያነቡ ሁሉንም የአምልኮት ተግባራት ለእሱ ብቻ በማድረግ መሆን አለበት።

አሏህ ብቻ

በመሆኑም የምንለምነው አሏህን ብቻ ፣ ምንፈራው አሏህን ብቻ ፣ የምንመካው በአሏህ ብቻ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ፋቲሃ 1፡4)

“አንተን ብቻ እንገዛለን፤ አንተን ብቻ እርዳታ እንለምናለን።”

የሰው ልጆች እና ጅኖች የተፈጠሩበት ብቸኛው አላማ አሏህን ብቻ እንዲያመለኩ ነው። አሏህ በቅዱስ ቁርአኑ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ዛሪያት 51፡56)

“ጅኖችንም ሆነ ሰዎችን አልፈጠርኳቸውም እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጅ”

ኢባዳ የአምልኮ ተግባራት ፣ ተውሂድ ፣ አስማኡሏህ ሁስና የአሏህ ውብ ስሞች ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Share