እስልምና አካባቢን እንድንከባከብ እና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል።
ይህንንም በሚከተሉት መንገዶች ያስፈጽማል፡-
ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“አንድ ሙስሊም ዛፍ ወይም ሰብል አይተክልም ወፎች ፣ ሰዎች ወይም እንስሳት ከፍሬው በሚበሉ ጊዜ ለእርሱ ምጽዋት ሆኖ የሚመዘገብለት ቢሆን እንጅ።”

ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ማንኛውንም ነገር ማስወገድ ያበረታታል። የእስልምና መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“መንገድ ላይ ጉዳት (ሊያስከትል የሚችል ነገር) ማስወገድ ምጽዋት ነው።”
በሽታ እና ወረርሽኝ ወደ ሌላ ማህበረሰብ እንዳይዛመት ለመከላከል እና የሌሎችን ህይወት ለመጠበቅ የተጠቁ ሰዎች ማግለል ያበረታታል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“በአንድ አካባቢ ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ ወደዚያ አትግቡ፤ በምትገኙበት ቦታ ቢከሰት ደግሞ ከዚያ አትውጡ።”
እንስሳት እና ወፎችን እንዲሁ በዘፈቀደ መግደል የተከለከለ ነው። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ነሳኢ)
“ምንም ምክንያት ሳይኖረው ድንቢጥ የገደለ ሰው በትንሳኤ ቀን ወደ አላህ ይጮኻል ‘አላህ ሆይ! እገሌ ያለ ምክንያት ወይም ጥቅም ገደለኝ!”

ማህበረሰቡን በምንም መልኩ መበከል ይከለክላል። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም)
“ሰዎች ሌሎችን የሚረግሙባቸውን ሁለት ነገሮች ተጠንቀቁ።” [ባልደረቦቻቸው] “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሰዎች ሌሎችን የሚረግሙባቸው ሁለቱ ነገሮች ምንድን ናቸው?” ብለው ጠየቁ። እርሳቸውም “ሰዎች በሚሄዱባቸው ቦታዎች ወይም ጥላ በሚፈልጉባቸው ቦታዎች ሽንት መሽናት ነው” ሲሉ መለሱ።

Share