ኢስራዕ እና ሚዕራጅ

Author picture
ኢስራዕ እና ሚዕራጅ በተመለከተ ኢስራዕ ማለት ነብዩ ከመስጅደል ሐረም ተነስተው ወደ በይተል መቅዲስ ያደረጉት የምሽት ጉዞ ሲሆነ ሚዕራጅ ደግሞ ወደ ሰባቱ ሰማት ያደረጉት ጉዞ ነው።
ኢስራዕ እና ሚዕራጅ
ኢስራዕ እና ሚዕራጅ

ኢስራዕ እና ሚዕራጅ በተመለከተ ኢስራዕ ማለት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መካ ውስጥ ከሚገኘው መስጅደል ሐረም ተነስተው እየሩስ አሌም ውስጥ ወደሚገኘው በይተል መቅዲስ ያደረጉት የምሽት ጉዞ ነው።

በይተል መቅዲስ መስጅደል አቅሷ ተብሎም ይጠራል።

በይተል መቅዲስ መስጅደል አቅሷ

አሏህ አንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራ 17፡1)

“ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጅድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው መስጅደል አቅሷ በሌሊት ውስጥ ያስሄደው ጌታ ጥራት ይገባው። ከተአምታቶቻችን ልናሳየው አስሄድነው። እነሆ እሱ አሏህ ሰሚው ተመልኳቹ ነው።”

በነብዩ ተልዕኮ በአስረኛ አመታቸው ውስጥ መልአኩ ጅብሪል ወደ እሳቸው መጥቶ ወደ ቅዱሱ የመካ መስጅድ ጠርዝ መራቸው። የሚጠብቃቸው ቡራቅ ነበር።

ቡራቅ ከአህያ ከፍ የሚል ፣ ከበቅሎ የሚያንስ እና ኮቴውን ከእይታ አጥናፍ የሚያርቅ በጣም ፈጣን እንቅስቃሴ ያለው ነጭ እንስሳ ነው።

እየሩስ አሌም እንደደረሱ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወርደው ነብያቶች እንደሚጠቀሙበት ባለ ተመሳሳይ ቀለበት ቡራቁን አስረው ወደ መስጅድ ገቡ።

ከዚያም ነብዩ ኢብራሂም ፣ ነብዩ ሙሳ ፣ ነብዩ ኢሳ (እየሱስን) እና ሌሎች ነብያቶችን በሶላት አስከትለው ሰግደዋል።

ከዚያ ቡኋላ ወጡ፤ ጅብሪል (ሰ.ዐ.ወ) ወይንና ወተት ይዞላቸው መጣ። እሳቸውም ወተቱን መጠጣት መረጡ። ጅብሪልም “ፊጥራ (ንፁህ ተፈጥሮን) መርጠሃል” አላቸው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ሰባቱ ሰማያት ሚዕራጅ አደረጉ። ፍጡር ወደማያልፍበት ሲድረቱል ሙንተሃ ተወሰዱ።

ለአንድ ሶላት ሰባ ሽህ መላኢካዎች የሚገቡበት ፣ በጣም የሚዘወተረው ቤት  በይተል መዕሙርን አይተዋል።

በይተል መዕሙር ከሰባት ሰማያት በላይ የሚገኝ የመላኢካዎች የአምልኮ ቤት ነው።

በዚሁ ምሽት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በቀን ሃምሳ ሶላት እንዲፈፅሙ መለኮታዊ ትዕዛዝ ተቀብለው የነበረ ቢሆንም ከስድስተኛው ሰማይ ላይ ያሉት ነብዩ ሙሳ (ሰ.ዐ.ወ) በሰጧቸው ምክር አማካኝነት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሏህን ጥቂት ቁጥር እስኪያደርግላቸው ድረስ ለምነው በቀን አምስት ስግደቶች በሆነላቸው ጊዜ ተቀብለዋል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጀነት እና ጀሐነምን ፣ ልክ እንደ ሪባ እና ዚና ያሉ ከባድ ሃጢያቶች የሚቀጡበትን ቅጣቶች ናሙና ተመልክተዋል።

መስጅደል ሐረም ፣ በይተል መቅዲስ ፣ ሪባ እና ጅብሪል ተመልከቱ

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Share