ነብዩ ኢብራሂም

Author picture

ነብዩ ኢብራሂም (   ) ከአሏህ ነብያቶችና መልዕክተኞች መካከል አንዱ ነው። የትልቅ ስብዕና ባለቤት ሲሆን በሁሉም አጋጣሚ እና ሁኔታ አሏህን ፈሪም ነበር።

አንዳንድ ሰዎች የድንጋይ እና የእንጨት ጣኦቶችን ፣ ሌሎቹ ፈለኮችን ፣ ከዋክብትመን ፣ ፀሐይ እና ጨረቃን ሌሎች ደግሞ ንጉሳቸውን እና ገዥዎቻቸውን ያመልኩ ነበር።

የኢብራሂም (   ) መንፈሳዊ ሃሳብ በጊዜው ከነበሩት ሁሉ በላይ ብዙ ደረጃዎችን ከፍ እንዲል አስችሎታል። እናም እውቀትና ጥበብን ተጠቅሞ ከህዝቦቹ መሃል አሃዳዊነትን በመስበክ ትልቅ ክብርን ተጎናፅፏል። ለአሃዳዊነት እራሱን የሰጠ ነበር።

ህዝቦቹ ትኩረታቸው ልማዳቸውና ባህላቸው ላይ ብቻ ነው። የኢብራሂም አባት ተራ ጣኦት አምላኪ ብቻ አልነበረም። ይልቁንም በእራሱ እጅም ጠርቦ ይሰራቸው ነበር።

በዚህ ክፉ ማህበረሰብ ውስጥ ኢብራሂም (   ) በእራሱ ቤተሰቦች እና በማህበረሰቡ ላይ ተነሳ።

አሏህ    የአብርሃምን ልብና አዕምሮ ከፈተለት። ከልጅነቱ ጀምሮ ጥበብን ሰጠው። እንዴት ሰው ሃውልት ሰርቶ እራሱ የሰራውን እንዴት ያመልካል ሲል ኢብራሂም (   ) አሰበ።

የውሸት አማልክቶቻቸው እንኳን ሰዎችን ሊረዱ እራሳቸውን ከጥፋት የማይከላከሉ መሆኑን ሊያሰያቸው እና ሊያሳምናቸው ፈለገ።

የማይረባ ነፍስ የሌለው ድንጋይ በማምለካቸው ሊያሳፍራቸውም በመሻት ለታላቁ በአል ሁሉም ከተማዋን ለቀው ሲወጡ ወደ ቤተ-መቅደሱ በማቅናት ትልቁን ጣኦት ሳይነካ ጣኦቶቹ እንደተጣሉና ትልቁ ጣኦት ሌሎቹን እንደሰባበራቸው አድርጎ አደቀቃቸው።

ወደ ተረፈው ጣኦት በመዞር ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ይጠይቁት ይሆን?

ሰዎቹ እንደተመለሱ ጣኦቶቻቸው ድቅቅ ማለታቸውን ተመለከቱ። ሆኖም ኢብራሂም ( ) እንዲታሰር ፈለጉ። ጣኦቶቹን ለመሰባበራቸው ተጠያቂ እሱ መሆኑን ሲጠይቁት ትልቁን ጣኦት አልተሰበረም እሱን ጠይቁ፤ ወንጀለኛው እሱ መሆን አለበት አለ።

ጣኦቱ የማይንቀሳቀስ እና የማይናገር መሆኑን ታውቃለህ ሲሉ መለሱለት። በዚህ ምላሽ ነብዩ ኢብራሂም የውሸት ጣኦቶችን ማምለክ ቂልነት መሆኑን የሚያጋልጥበት እድል አገኘ።

ምንም እንኳ የውሸት እምነታቸውን ተቃርኖ ቢረዱም ባቀጣጠሉት ትልቅ እሳት ውስጥ በመወርወር ሊቀጡት ወሰኑ።

ለዚህ አላማ ጥልቅ ጉድጓድ ተቆፍሮ በማገዶ እንጨት ተሞላ፤ እናም አነደዱት። ነብዩ ኢብራሂም (  ) ወደ ውስጥ ተወረወረ። በአሏህም ትዕዛዝ ብቻ ዳነ። አንች እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛና ሰላም ሁኝ አልን። (አል-ቁርአን 21፡69)

ነብዩ ኢብራሂም (   ) ሰዎች በአሏህ እንዲያምኑ መጥራቱን ቀጠለ። ህዝቦቹን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ለመምራት ትልቅ ጥረት አደረገ። እነሱን ለማሳመንም የሚችለውን ሁሉ ሞከረ።

በተጓዘበት ቦታ ሁሉ ሰዎች አንድ እና ብጨኛ እውነተኛ አምላክ የሆነውን አሏህ እንዲያመልኩ አስተማራቸው።

የነብዩ ኢብራሂም ሚስት ሳራ ልጅ ልትፀንስ ማትችል በመሆኗ ሳራ እራሷ የፈቀደችለትን አገልጋዩን ሐጀርን አገባ። ከእሷም ኢስማኤል ( ) ተወለደ። በማስከተልም ሳራ ኢስሃቅን ወለደች።

ሐጀር እና የዘምዘም ውሃ

ኢብራሂም ( ) ከሚስቱ ሐጀር እና ከልጁ ኢስማኤል ጋር የእርሻ ማሳ እና ውሃ ወደለለበት ዛሬ መካ ተብሎ ወደ ሚታወቀው ሸለቆ ተሰደዱ። ነገርግን አሏህ ለእሷና ለልጇ የዘምዘምን ምንጭ አፈለቀላቸው።

ኢብራሂም እና ኢስማኤል ቅዱሱን ቤት ካዕባን ገነቡ። ሁለቱም ለረዥም ጊዜ ሰገዱ፤ ይህን አገልግሎታቸውን እንዲቀበላቸው እና ለፈቃዱ ያጎበደዱ ሙስሊሞች እንዲያደርጋቸው ፣ ከዘሮቻቸው ሙስሊም ህዝቦች ለፈቃዱ ያጎበደዱ እንዲሆኑ ለመኑ።

እንዲሁም ኢብራሂም ( ) መካን የሰላም ከተማ እንዲያደርጋት ፣ ዘሮቹ የዘወትር ሶላት የሚሰግዱ እንዲሆኑና አመስጋኞች እንዲሆኑ ፍሬዎችንም እንዲሰጣቸው አሏህን ለመኑ።

አሏህ (   ) ለዚህ ዱአ ምላሸ ሰጠ፤ ካዕባን እና የመካን ከተማ ባረከ። ምንም እንኳ የመካ ዳርድንበር ጠፍ እና ድንጋያማ ቢሆንም ለሃብት እና ለቁሳዊ ህይወት ጥሩ ነገሮችንም ይዟል።

እንዲሁም እስካሁን ጊዜ ድረስ በአራቱም የአለም ማዕዘናት ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች በካዕባ አቅጣጫ ይሰግዳሉ፤ ሐጅ ወይም ኡምራ ለማድረግም ይችን የሰላም ከተማ ይጎበኛሉ።

ኢስማኤል ፣ መካ እና ዘምዘምን ተመልከቱ

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top